WE NEED FREEDOM!

WE NEED FREEDOM!

Wednesday, February 26, 2014

‘‘ፋሽዝም’’ በኢትዮጵያ!


ኢትዮጵያ በወያኔ ፈላጭ ቆራጭ ቡድናዊ አገዛዝ ስር ከወደቀችበት እነሆ ሁለት አስርተ ዓመታት ነጐዱ። ወያኔ ስልጣን ላይ ሲወጣ ካለፈው የተሻለ የዲሞክራሲ ለውጥ ይመጣል የሚል በብዙ ሰዎች ዘንድ የተስፋ ጭላንጭል ተጥሎለት ቢኖርም “ጅብ እስኪነክስ ያነክስ” እንዲሉ ስልጣናቸውን ካደላደሉ በኋላ ግን ተስፋ የተጣለለትን ዲሞክራሲ ደብዛውን በማጥፋት “ከፋፍለህ፣ በሆዱ ይዘህ፣ አሸብረህ፣ አደናግረህ፣ አናቁረህና አደንዝዘህ ግዛ” የሚለውን ሌሎች አምባገነን መንግስታት የሚከተሉትን የጡንቻ አገዛዝ ዘይቤ የዲሞክራሲ ሽፋን በመስጠት ዘላለማዊ ስልጣናቸውን ለማጠናክር ሲሉ በበለጠ ሲጠቀሙበት መቆየታቸው የአደባባይ ሚስጢር ሆኖ ቆይቷል።
በአገራችን ኢትዮጵያ በሥልጣን ላይ ያለው የወያኔ አገዛዝ በዓለም ዙሪያ በተለያየ ዘመን ወደ ሥልጣን ከመጡት መሰል ፀረ-ሕዝብ መንግሥታት ቢብስ እንጂ በምንም መልኩ የተሻለ አይደለም። ፋሽዝምን እንቃወማለን፣ እናወግዛለን እያለ በጫካ ያናፋ የነበረው ወያኔ ዛሬ በዲሞክራሲ ድባብ ሥር እየተገበረው ያለ አገርና ሕዝብን ማዋረድና መዝረፍ፣ መቀጣጫ እያለ በግፍ ማሰርና መግደል ምን ተብሎ ሊጠራ ነው? በአዲስ አበባ ፣ በጋምቤላ ፣ በአዋሳ ፣ በወለጋ ፣ በሰሜን እና በአራቱም ማእዘን የኢትዮጵያ ክልሎች በየእለቱ በወያኔ ታጣቂዎች እየተካሄደ ያለውን የጅምላ ጭፍጨፋ ምን ብለው ይጠሩታል?
ወያኔ ኢትዮጵያን ሲቆጣጠር ተሸክሞት የመጣውን በቀል አማራው፣ ኦሮሞው፣ ጋምቤላው፣ አፋሩ፣ ኦጋዴኑ ወዘተ. ዘር የማጥፋት ተግባሩን ፈጽሞታል፤ አሁንም እያጠፋ፣ እየገደለ በየወህኒ ቤቶቹ እየማገደው ነው። ይዞት የመጣው ድህነትና በሽታን ብቻ ነው። ፖሊሲው የኢትዮጵያን ሕዝብ ከዓለም ሃገሮች በድህነት ከወለል በታች ያደረገ ስርዓት ነው። የኢትዮጵያ ገበሬ የመሬቱ ባለቤት በነበረበት ወቅት እራሱን እና ቤተሰቡን አብልቶ ቀሪውን ለገበያ በማቅረብ ሕዝቧ እንደ አቅሙ በልቶና ጠጥቶ ያድር ነበር። የወያኔ መንግስት መሬት የመንግሥት ነው ብሎ በማወጁ የኢትዮጵያ ሕዝብ በገጠሩም በከተማም መሬት አልባ ሆኗል። የኢትዮጵያ ሕዝብ በገዛ ሃገሩ ሁለተኛ ዜጋ ከመሆኑ የተነሳ ሲሞት እንኳን የሚቀበርበት ቦታ ያጣ ሕዝብ ሆኗል። የዚህ ጽሁፌ ዋና አላማ የወያኔ መንግስት የፋሽስት አገዛዝ ስለመሆኑ ምሳሌዎችን አንድ ሁለት በማለት ነቅሸ በማሳየት ማስረገጥ ሲሆን ወያኔ ከምስረታው ጀምሮ ያካሂድ የነበረውን የንፁሃን ወገኖቻችንን ጭፍጨፋ ለማስረጃነት በማንሳት ለማሳየት እሞክራሉ።
• ወያኔ በ1969 መጀመሪያ በትግራይ ሰላማዊ ዜጋ ላይ ግድያ በመፈፀም ፋሽስታዊ ጉዞውን ሀ ብሎ ጀመረ። ግድያው ሳያንሰው የንፁሃን ዜጐችን ሃብትና ንብረትም ወረሰ። ከደደቢት በረሃ የጀመረውን አማራ የትግራይ ሕዝብ ጠላት ነው በማለት በተለያዩ ጊዜያትና ቦታዎች አማራውን በመጨፍጨፍ የዘር ማጥፋት ወንጀልም ፈጽመዋል። ለሴቶች በግዳጅ የማምከኛ መድሃኒት በመስጠት የአማራው ቁጥር እንዳይጨመር አድርገዋል። ከኖረበት ቀየውና መሬቱ በግዳጅ እንዲፈናቀል አድርገዋል።
• ወያኔ ኢትዮጵያን እንደተቆጣጠረ በ1984/5 መጀመሪያ ጀምሮ በኦሮሞ ሕዝብ ላይ መጠነ ሰፊ የጥቃት ዘመቻ በመክፈት የግድያ፣ የቤት ማቃጠል፣ ንብረቱን መዝረፍና ከፍ ያለ ሰቆቃ አደረሰ። እንደ አማራው ሁሉ ከመኖሪያ ቦታውና ከመሬቱ ላይ ተፈናቅሏል። የኦነግ አባል ናችሁ እየተባሉ በሺዎች የሚቆጠሩ ያለምንም የፍርድ ውሳኔ ወደ ወህኒ ወርደዋል። በየቦታው በከፍተኛ ትምህርት ተቋሟት የሚማሩት የኦሮም ልጆች ከትምህርታቸው ተባረዋል። የተባረሩትም፣ መባረራቸው አልበቃ ብሎ ለእስር ተዳርገዋል፤ የተገደሉትንም ቤት ይቁጠራቸው። ደጉና ሩህሩሁ የኦሮሞ ሕዝብ ከእርሻው ተፈናቅሎ የረሃብና የበሽታ ሰለባ በመሆን የፋሽስቱ ወያኔ የግፍ ፅዋ ገፈት ቀማሽ ከመሆን አላለፈም።
• ወያኔ በጋምቤላ አኝዋኮች ላይ የፈጸመው የዘር ማጥፋት ወንጀልን ማንም ይረሳልዋል ብየ አላስብም? ሕዝቡ ከመሬቱ ተፈናቅሎ አብዛኛው በጎረቤት ሃገሮች ስደተኛ ሆነው በየሃገሩ እየተንከራተተ በችግር ላይም ይገኛሉ።
• የኦጋዴን ሕዝብም የዘር ማጥፋት ወንጀል ተፈጽሞበታል። ቤት ንብረቱ በወያኔ ወታደሮች ተቃጥሎበታል፤ ሴት ልጆቹና ሚስቶቹ ተደፍረውበታል። በተጨማሪም ከመሬቱ ላይ ተፈናቅሎ ለስደት ተዳርጓል።
• የአፋር ሕዝብም በሌሎቹ የኢትዮጵያ ጎሳዎች የደረሰው ደርሶበታል፣ እየደረሰበትም ይገኛል። የኢትዮጵያን ሕዝብ ከማሰቃየት ባለፈ ደግሞ የኢትዮጵያን ዳር ድንበር ለሱዳን መንግሥት ሸጠዋል። ሃገሪቱን ካለባህር በር አስቀርተዋል። የሃገር ሃብትና ታሪካዊ ቅርሶችን አውደመዋል፣ ሸጠዋል።
እንደው በደፈናው በአገራችን ታሪክ ውስጥ በሕዝባችን ከቶም እንደ አሁኑ ሳንጃ በአንገቱ ላይ ተወድሮ ጦር ተሰብቆበት የሚገኝበት የፋሽስታዊ አገዛዝ ጊዜ የለም። ፋሽዝም ዛሬ በወያኔ/ህወሃት ጊዜ ነግሷል ሥርም ሰዷል። በሥልጣን ላይ ለመቆት፣ ሃብቷን በዝብዞና ሽጦ ለማፈራረስ በታቀደው የአገዛዝ ሽብር ተግባር፣ ፋሽዝም በዴሞክራሲ ታዛ ሥር ወያኔ በኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት ላይ እየፈጸመው ያለ ለመሆኑ ሁሉም አገር ወዳድ ዜጋ ይረዳውል ብየ አምናለሁ። ፋሽስት ሕዝብ ይጨፈጭፋል፣ ያስፈራራል፤ ፋሽስት የማደናገሪያ ፕሮፓጋንዳን ያስፋፋል፣ ውሽት ይዋሻል፤ ፋሽስት ትምክህተኛና ጦርነት ፈላጊ ነው። ፋሽስት ራስ ወዳዶችን፣ ሆዳሞችን፣ ግብዞችን፣ ዱርየዎችን መሳሪያ ያደርጋል፤ ፋሽስት ድርጅቶችን ያስፋፋል፣ ተለጣፊ ያበዛል ወዘተ። እንግዲህ የፋሽስት አገዛዝ ባህርያትን ማንሳቴ ወያኔን በነዚህ ባህሪያትም መዝነን ፍረጃችንን ለማጠናከር ይረዳን ዘንድ በማሰብ ነውና መዝኖ ፍርድ መስጠቱን ለእናንተው ትቻለሁ።
ወደ ሥልጣን ከመጣበት ጊዜ ጀምሮ እጁን በንፁኃን ዜጎች ደም የታጠበው የወያኔ አገዛዝ ሕጋዊ የአምልኮት ነፃነታቸው ያለምንም የአገዛዙ ጣልቃገብነት እንዲከበር የጠየቁ የእስልምና ሃይማኖት ተከታይ ኢትዮጵያውያንን በጅምላ በሃይማኖት አክራሪነትና አሸባሪነት ወንጅሎ የግድያ ወንጀል ፈጽሟል። በክርስቲያን እምነት ተከታይ ወገኖቻችንም ተመሳሳይ ግፍ ሲፈፀምባቸው ተመልክተናል። ገዳማትን ማፍረስና መነኮሳትን ማሳደድና መግደል የወያኔ መለዮው ሆኗል። ወያኔ ንፁኃን ዜጎችን ከማሰቃየት፣ ከማሰርና ከመግደል የታቀበበት ወቅት ከቶውንም የለም፤ አልታየምም። ድብደባው፣ ማሰሩና ግድያው እየተፈጸመ ያለው በሁሉም የሃገሪቷ ክፍሎች በሚኖሩ ንፁሃን ዜጐች ሲሆን በግፍና በገፍ ወደ እሥር ቤት የማጎር እርምጃዎች ያልርኅራሄ ተፈጽመዋል፤ እየተፈጸሙም ነው።
ውድ የኢትዮጵያ ሕዝብ ሆይ በኢትዮጵያዊ ትዕግሥትና አርቆ አስተዋይነት በፋሽስቱ ወያኔ ወገን ሲደበደብ፣ ሲባረር፣ ሲገደል፣ ሃብት ንብረቱ ሲዘረፍ፣ ዳር ድንበሩ ሲወሰድ፣ በቋንቋ ልዩነት ሲመደብ፣ የተማረ ወገን ሲገደልና ሲሰደድ፣ አገር ለውጭ ባለሃብት ስትሽጥ፣ ይህ ሁሉ ሲሆን እስከ አሁን በደልን ተሸክመህ በዝምታ ታግሰሃል። ዛሬ በፋሽስቱ ወያኔ ኢትዮጵያ ተደፍራለች፣ ሕዝቧ ተዋርዷል፣ የታሪክ ክብሯ ተንቋል። ለብዙ ሺህ አመታት የኛ ቀደምት ትውልዶች አጥንትና ደማቸውን በማፍስስ ታፍራና ተፈርታ የኖረች አገር ዛሬ በዚህ ወቅት የትውልድ መካን ሆና ጥቃቱና ጥፋቱ እጅግ ተነባብሯል። ኢትዮጵያዊ ወገኔ ሆይ! ፍርሃት ከአደጋ የመከላከያ ባህሪ እንጂ እየሸሹ ለመጥፋትና ለመሞት አይደለም። ይህ ጭቆናና ጥቃት ሊያበሳጭ፣ ሊያናድድህና ሊያስቆጣህ ይገባል። ሰው ነህና ለመብትና ለነፃነት መታግልና ለመጭውም ትውልድ ለልጆችህ አገር ማቆየት ይኖርብሃል። የኛ ቀደምት አባቶችና እናቶች እኛ ሞተን አገር ትኑር ብለው ለኢትዮጵያ ታላቅ መስዋዕትነት ከፍለዋል። ታሪክ ምስክርነትዋን መዝግባለች። ዛሬም የኢትዮጵያዊያን ወኔና ጀብዱ፣ አትንኩኝ ባይነት ይደገም። ወያኔ ኢትዮጵያዊነት የሌለው አረመኔ ፋሽስት ነውና፤ መወገድ አለበት። ስለዚህ ለትዕግሥት ገደብ እንስጥ፣ አንዋረድ ፣ ትውልድ እንጠብቅ፣ አገርና ሕዝብ እናድን።
ድል ለጭቁኑ የኢትዮጵያ ህዝብ!

http://www.ethiofreedom.com/

Monday, February 24, 2014

ወያኔን ተሸክሞ መኖር ይብቃን!

የሰው ልጅ ካመረረ ቀጥሎ ምን እንደሚመጣ ማሰብ አይችልም፡፡ ለነፍሱም ፈጽሞ አይሳሳም፡፡ ወቅቱ 1998 ዓ.ም ነው፡፡ የ97 ሰባቱን ምርጫ ተከትሎ በተነሳው ብጥብጥ ባህር ዳር ከተማ ውስጥ ይኖር የነበረ ስሙን  ለጊዜው የማላስታውሰውን ወጣት ሁኔታ ላካፍላችሁ፡፡ በእለቱ ከተማ ውስጥ ከፍተኛ ረባሻ ነበር፡፡ በባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ብጥብጡ ተዛምቱዋል፡፡ ቀደም ብሎ ተማሪዎች ወደ ክፍል እንዳይገቡ ስጋት ተፈጥሩዋል፡፡ ግቢው በፌዴራል ፖሊስ ተከቡዋል፡፡ የከተማው ወጣቶች  ወደ ዩኒቨርሲቲው ገብተው ተማሪዎችን ይዘው መውጣት ያፈልጋሉ፡፡ ተማሪዎችም ከህብረተሰቡ ጋር ተቀላቅለው ድምጻቸውን ማስማት እና ተቃዉሞአቸውን መግለጽ ይፈልጋሉ፡፡ በመሀል ዙሪያውን የከበበው የፌዴራል ፖሊስ በታጠቀው መሳሪያ በማስፈራራት እየተከላከለ ያገኛል፡፡ ከውጪ ወደውስጥ እንዳይገቡ ሲከላከሉ ከውስጥያ ያለው ደግሞ ወደ ውጪ እንዳይወጣ በመሀል ሆነው  ይከላከላሉ፡፡ ማሪዎች ያሳደባሉ፤ ይጮሀሉ፡፡ በዚህ መሀል በአዲሱ የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ አስተዳደር ህንጻ በኩል አንድ ረዘም ያለ  መልካማ ወጣት መሳሪያ ደግነው ለግዳይ የሚጠባበቁትን ወታደሮች ከምንም ሳይቆጥር ከወደ ስላሴ ቤተክርስቲያን አቅጣጫ በከፍተኛ ፍጥነት እየሮጠ መጣ፡፡ ወታደሮች ተመለስ! ተመለስ! ትሞታለህ እያሉ ይጮሀሉ፡፡ በለው! በለው! ያባባላሉ፡፡ ይህ ሁሉ ሲሆን ያ ነፍሱ ፍትህ የተጠማች ወጣት ግቡ ወደ ግቢው በመምጣት ድምጹን ማስማት  በመሆኑ  የወታደሮችንም ጩኸት ሆነ የተደቀነውን መሳሪያ ከምንም አልቆጠረውም፡፡
የወጣቱን ድፍረት ላየ ሰው ሞት የሚባል ነገር ከምድር  እንደሌለው የተረዳው ይመስል ነበር፡፡ ሩጫውን ቀጠለ፡፡ መግደል የተካኑት ወታደሮችም በሁለት ጥይት አከታትለው መቱት፡፡ እንደኛው ጥይት ትክሻውን የመታው ሲሆን ሁለተኛው ጥይት ኩላሊቱን አካባቢ ነው የመታው፡፡ እንደዚህም ሁኖ ወጣቱ አሁንም እየሮጠ በሸቦ ከታጠረው የዩኒቨርሲቱው አጥር ሲደርስ አጥሩን አልፎ መግባት አልቻለም፡፡ ሽቦው እጥር ስር ወደቅ፡፡ በዚህ ጊዜ ተማሪዎች የወደቀውን ወጣት ለማንሳት ከያሉበት  ሮሩዋጡ፡፡ የሽቦውን አጥርም ፈልቅቀው ወደ ውስጥ ይዘውት ገቡ፡፡ወደያው ወደተማሪዎች ክሊኒክ ይዘውት ሄዱ፡፡ በዩኒቨርሲቲው ክሊኒክ  የሚሰሩት ዶ/ር ታጀበ አለሙ እና ነርስ በላይነሽ እርዳታ ቢያደርጉለትም ማትረፍ አልቻሉም፡፡ ወጣቱ ህይወቱ አልፋለች፡፡ ግቢው ታመሰ፡፡ ለቂሶ ዋይታ እየዩ ሆነ፡፡ በመሀል የምሳ ሰሀት ስለደረሰ  የተወሰኑ ተማሪዎች ምግብ እንብላ ሲሉ ሌሎች ደግሞ እሬሳ አጋድመን መብላት የለብንም ሲሉ እንብላ የሚሉት ከላይ ትእዛዝ ተላለፎላቸው ኑሮዋል እናንተ ምን ትሰራላችሁ ለምን ዝም ብላችሁ ታያላችሁ ስለተባሉ ጉዳዩ ወደ ብሄር ጠብ ተቀይሮ  ተማሪዎች ጎራ ለይተው ድብድብ ተጀመረ፡፡ ከዚያም ግቢው ሙሉ በሙሉ በፌዴራል ፖሊስ ቁጥጥር ስር ዋለ፡፡ ለተወሰኑ ቀናት ሽንት ቤት እንኩዋን ለመውጣት የወታደሮችን ፈቃድ ተጠይቆ ነው፡፡ ከዶርም እንዳይወጣ ተከለከለ፡፡ ትምህርትም ተቁዋረጠ፡፡ ከሳምንት በላይ በዚህ መልኩ ቀጥሎ ቀስ በቀስ ተረጋጋ፡፡
እንግዲህ እንድትረዱልኝ የፈለግሁት የሰው ልጅ ትግስቱ ገበድ እንዳለው ነው፡፡ ከዚያ ገደብ በላይ ማለፍ እንደማይቻል በዚህ ወጣት ታሪክ ይነግረናል፡፡ ማናኛውም ነገር ገደብ (tolerance limit) አለው፡፡ ለምሳሌ አንድ ላስቲክ ስንስበው እስከተወሰነ ደረጃ ይለጠጣል፡፡ ከዚያ ደረጃ በኃላ ይበጠሳል፡፡ ውኃ በፈሳሽነት ደረጃ የተወሰነ ሙቀትን ወይም ቅዝቃዜን ተቁቁም ይቆያል፡፡ ከዚያ ደረጃ ሲያልፍ ወይ  ይተናል ወይ ወደ በረዶነት ይለወጣል፡፡ የአንድ ብረት ጥንካሬው የተወሰነ ሀይልን ለመቁዋቋም ነው፡፡ የሀይል መጠኑ ሲበዛ ይጣመማል ወይም ይሰበራል፡፡ የወያኔ አፈና እስከተወሰነ ደረጃ ህዝቡን ለማስጊንበስ ረድቶታል፡፡ የወያኔ የመከላከያ ሰራዊት ያለፉትን ጊዜያት በስልጣን ተደላድሎ የሀገርን ሀብት እየዘረፈ እንዲቆያ አግዞታል፡፡ ነገር ግን ዘላልም ስልጣን ላይ እንዲቆይ አያደርገውም፡፡ ማናኛውም ነገር ከገደቡ ማለፍ ስለማይችል፡፡
የኢትዮጵያ ህዝብ ወያኔን መሸከም የሚችለውን  ያክል ታክሻው እስኪጎብጥ ግፍ እና በደሉን ችሎ ተሸክሞትል፡፡ ላለፉት 23 አመታት ሲያነቋሽሹት፤ ሲገድሉት፤ ሲዘርፉት፤ ከመኖሪያው፣ ከቤቱ ፣ከስራው ሲያፈናቅሉት፤ ከሀገር ሲያስወጡት፤ በእምነት በጎሳ እየከፋፈሉ ሲያጫርሱት ብዙ ብዙ ታግሷቸዋል፡፡ አሁን  ህዝቡ መሸከም ከሚችለው በላይ ስለሆነበት ከራሱ አሽቀንጥሮ መጣል ያፈልጋል፡፡ ዛሬ አንድነት እና መኢአድ  በጠሩት ሰልፍ የታየው የህዘብ ስሜት ምን ያክል እየገነፈለ እንደሆነ ነው፡፡ ሰላማዊ ሰልፍ የሚነግረን ህዝቡ ምን ያልክ ለውጥ እንደሚፈልግ ነው፡፡ እንግዲህ አወዳደቁ እንዳይከፋ ቀስ ብሎ ትንሸራቶ መውረድ ከቻሉ ለወያኔ እና ለደጋፊዎች እሰየው ነው፡፡ ካለሆነ ግን ህዝቡ በግድም ቢሆን አንኮታኩቶ ጥሎ መሰባባሩ የማይቀር ሀቅ ነው፡፡ ስለዚህ ወያኔ ወይ በራሳቸው ጊዜ ቀስ ብለው ይውረዱ ወይ  በግድ ይወገዱ፡፡
ድል ለኢትዮጵያ ህዝቦች!http://ecadforum.com/Amharic/archives/11204/

Saturday, February 22, 2014

የመከላከያ ተቋም ተግባር አገርን መጠበቅ ነዉ ወይስ አገርን መዝረፍ?

February 22, 2014
Ginbot 7 weekly editorialየአዉሮፓ ቅኝ ገዢዎች አፍሪካን ሲቀራመቱ ባህር ተሻግረዉ በመጡ የነጭ ባዕዳን ኃይሎች መገዛትን መርጦ የአዉሮፓን ወራሪዎች በሰላም በሩን ከፍቶ ወደ አገሩ ያስገባ እንድም የአፍሪካ አገር አልነበረም፤ የኋላ ኋላ ተሸንፈዉ በቅኝ አገዛዝ ቀንበር ስር ቢወድቁም ሁሉም የአፍሪካ አገሮች እንደ አቅማቸዉ ከወራሪ ኃይሎች ጋር ተፋልመዋል። በአንድ ወቅት የቅርብ ጎረቤቶቻችንን ጨምሮ ብዙዎቹ የአፍሪካ አገሮች በወራሪ ኃይሎች ተሸንፈዉ የቅኝ ገዢዎች ቀንበር ጀርባቸዉ ላይ ሲጫን አገራችን ኢትዮጵያ ብቻዋን የአለም ጥቁር ህዝቦች የነፃነት ተምሳሌት ሆና የኖረችዉ ጣሊያኖች፤ እንንግሊዞችና ፈረንሳዮች ከሌሎች የአፍሪካ አገሮች ለይተዉ ስለወደዷት ወይም ስላከበሯት አይደለም። ይልቁንም ነፃነታችንና የግዛት አንድነታችን ተከብሮ የኖረዉ ኢትዮጵያ እናት አገሩ በጠላት ስትደፈር ከሚያይ ምትክ የሌላት ህይወቱ ብታልፍ ደስ የሚለዉ የኩሩና የጀግና ህዝብ አገር በመሆኗ ነዉ። የሚገርመዉ ይህ ኩሩና ጀግና ህዝብ ጣሊያንን የመሰለ በዘመናዊ መሳሪያ የታጀበ ኃይል ዉርደቱን ተከናንቦ ወደመጣበት እንዲመለስ ሲያስገድድ እንደ ዛሬዉ የተደራጀ ዘመናዊ የመከላከያ ሰራዊት አልነበረዉም። ዛሬ አራት ኪሎና ስድስት ኪሎ ላይ የተተከሉት ሁለቱ ታሪካዊ ሀዉልቶቻችን የሚነግሩንም ይሀንኑ የኢትዮጵያ ህዝብ በዘመናዊ መልክ የተደራጀ ሠራዊት ሳይኖረዉ የጎበዝ አለቃ እየመረጠ በጣሊያን ፋሺስቶች ላይ የተጎናጸፈዉን አኩሪ ድል ነዉ።
ኢትዮጵያ ዉስጥ ዘመናዊና የተደራጀ መከላከያ ሠራዊት ጥንስስ የተጣለዉ በዳግማዊ ሚኒልክ ዘመነ መንግስት ሲሆን እሱም ቢሆን ከአድዋ ድል በኋላ ቆይቶ የመጣ ክስተት ነዉ። በአፄ ኃ/ሥላሤና በደርግ ዘመነ መንግስት ኢትዮጵያ ለአንድ ፓርቲና ይህ ፓርቲ እወክለዋለሁ ለሚለዉ ህዝብ ብቻ ሳይሆን ሙያዊ ብቃት የነበረዉ፤ሙያዉን የሚያከብርና ለአገሩና ለወገኑ ታማኝ የሆነ የመከላከያ ሠራዊት ነበራት። የወያኔ ዘረኞች አዲስ አበባን ሲቆጣጠሩ የመጀመሪያ ኢላማቸዉ አድርገዉ ካወደሟቸዉ ዋና ዋና የአገራቸን ተቋሞች ዉስጥ የመጀመሪያዉ ይሄዉ የአገርና የህዝብ ደጀን የነበረዉ ተቋም ነበር። ዛሬ ኢትዮጵያ ዉስጥ የአገር መከላከያ ሠራዊት እየተባለ የሚጠራዉ ተቋም ለጎጠኞች ጥቅምና የስልጣን መራዘም የቆመ፤ በዘረኝነት የተካፋፈለ፤ ይህ ነዉ ተብሎ የሚጠቀስ ሙያዊ ብቃት የሌለዉና የወገንና የአገር ፍቅር እንዳይኖረዉ ተደርጎ የተደራጀ ሰራዊት ነዉ። ይህንን ሠራዊት የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ሳይሆን የወያኔ ሠራዊት እያልን የምንጠራዉም በዚሁ ምክንያት ነዉ።
ዛሬ ሙሉ በሙሉ በወያኔ ዘረኞች ቁጥጥር ስር የወደቀዉ የአገር መከላከያ ተቋም የሚታማዉ በዘረኝነት፤ በሙያ ብቃት ማነስና የአንድ ፓርቲ ጥቅም አስከባሪ በመሆኑ ብቻ አይደለም፤ ተቋሙ ከእነዚህ ዋና ዋና ጉድለቶቹ በተጨማሪ በቀድሞዉ የኢትዮጵያ መከላከያ ተቋም ላይ በፍጹም ያልታዩ ሌሎች ትላልቅ ጉድለቶች አሉበት። ከእነዚህ ጉድለቶች ዉስጥ አንዱ የወያኔ የመከላከያ ተቋም ህገ መንግስቱ ከሰጠዉ ኃላፊነት ዉጭ በንግድና በንብረት ይዞታ ላይ ላይ መሰማራቱ ሲሆን ሁለተኛዉ ደግሞ ከዚህ ፀባዩ ጋር ተያይዞ በመከላከያ ሠራዊት ተቋም ዉስጥ ከላይ እስከታች የሰፈነዉ ቅጥ ያጣ ሙሰኝነት ነዉ። ዛሬ የወያኔን የመከላከያ ተቋም፤ የህወሀትን ፓርቲና ኤፎርት በሚል ምህጻረቃል የሚታወቀዉን የወያኔን የገንዝብ ማምረቻ ድርጅት ነጣጥለን ወይም አንዱን ከሌላዉ ለይተን ማየት የማንችልበት ደረጃ ላይ ደርሰናል።
በላፈዉ አመት ወያኔ እራሱ ያቋቋመዉ ፀረ ሙስና ኮሚሺን የገንዘብ ዝርፊያን፤የንብረት መባከንንና መዝረክረክን አስመልክቶ ለፓርላማዉ ባቀረበዉ ሪፖርት ላይ ከጠቀሳቸዉ መንግስታዊ ተቋሞች ዉስጥ ቀዳሚዉን ደረጃ የያዘዉ የመከላከያ ተቋም ነዉ። ሆኖም ፓርላማዉም ሆነ የወያኔ አገዛዝ ለዚህ ሪፖርት የሰጡት ምላሽ የመከላከያና የደህንነት ተቋሞች ከአሁን በኋላ ያሻቸዉን ያክል ገንዝብ ቢዘርፉ የሂሳብ መዝገባቸዉ “ለአገር ደህንነት” ሲባል በኦዲት ኮሚሺን አይመረመርም የሚል ምላሽ ነበር። እንግዲህ ይህ በሙሰኝነት የተጨማለቀ፤ ለህግ የማይገዛና መጠበቅና መንከባከብ የሚገባዉን የአገር ኃብትና ንብረት የሚዘርፍ ተቋም ነዉ ባለፈዉ ሳምንት “የመከላከያ ቀን” ተብሎ አመታዊ በዐል የተከበረለት።
መናገሻ ከተማችን አዲስ አበባ ዉስጥ በየቦታዉ የሚታዩትን ሰማይ ጠቀስ ህንፃዎች ሰርተዉ የሚያከራዩት የወር ደሞዛቸዉ ከ2500 ብር የማይበልጥ መከላከያ ሠራዊት ዉስጥ የተሰገሰጉ የወያኔ ጄኔራሎች ናቸዉ፤ኢትዮጵያ ዉስጥ ትርፋማ በሆኑ ቦታዎች ሁሉ ትላልቅ ሆቴሎች፤ የአገልግሎት ተቋሞችና የንግድ ድርጅቶች ከፍተዉ ቁጥር ስፍር የሌለዉ ኃብት የሚያጋብሱት የወያኔ ጄኔራሎች ናቸዉ፤ ድሃዉና የወያኔ ዘረኝነት ሰለባ የሆነዉ ኢትዮጵያ ሰራዊት ለተመድ ተልዕኮ በተሰማራባቸዉ ቦታዎች ሁሉ ተመድ የሚከፍለዉን የቀን አበል ኪሳቸዉ ዉስጥ እየከተቱ ሚሊዮነሮች የሆኑትና በየዉጭ አገሩ ዉድ መኖሪያ ቤቶችንና የንግድ ተቋሞችን የሚገዙት የወያኔ ጄኔራሎች ናቸዉ። የወያኔ መከላከያ ተቋም ጉድ በዚህ ብቻ አያበቃም፤ ይህንን ወንጀለኛ ተቋም ቃላት እየደረደሩ ለመግለጽ ከመሞከር ይልቅ በጥቅሉ ወያኔ የኢትዮጵያን ህዝብ ኃብትና ንብረት እንዳሻዉ መዝረፍ እንዲችል የኃይል ሽፋን የሚሰጥ ተቋም ነዉ ማለት የሚበቃ ይመስለናል።
ወያኔና ስር የሰደደዉ ዘረኛ ስርዐቱ ከኢትዮጵያ ምድር ላይ እስካልተነቀሉ ድረስ ወያኔ ዝርፊያዉን የወያኔ መከላከያ ተቋምም የወያኔንና የደገፊዎቹን ዝርፊያ በመሳሪያ ማጀቡ አይቆምም። የወያኔን ዝርፊያ ለማስቆምና አገራችንን ከተጋረጠባት አሳሳቢ አደጋ ለመታደግ ብቸኛዉ መንገድ ወያኔን ከሥልጣን ማስወገድ ብቻ ነዉ። ግንቦት 7 የፍትህ፤የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ የጀመረዉ ህዝባዊ ትግል እንደ አገር መከላያከያ አይነቶቹ ቁልፍ የአገር ተቋሞች በሚሰሯቸዉ ስራዎች ሁሉ የአገርንና የህዝብን ጥቅም እንዲያስጠብቁ ለማድረግ ነዉ። የግንቦት 7 ትግል አላማ የመከላከያ፤ የደህንነት፤ የፖሊስና የፍትህ ተቋሞች የአንድ ፓርቲ ጥቅም ማስከበሪያ መሳሪያዎች መሆናቸዉ አብቅቶ የአገርና የህዝብ አለኝታ እንዲሆኑ ነዉ፤ ሆኖም ይህንን ቅዱስ አላማ ወያኔ በስልጣን ላይ እስካለ ድረስ ተግባራዊ ማድረግ ስለማይቻል ነፃነት፤ ፍትህ፤ዲሞክራሲ፤ ሠላምና እኩልነት የናፈቀዉ ኢትዮጵያዊ ሁሉ ወያኔን በፍጥነት እናስወግድ ከሚለዉ የአገር አድን አላማ ጎን እንዲሰለፍ ግንቦት 7 የትግል ጥሪዉን ያስተላልፋል።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!http://ecadforum.com/Amharic/archives/11144/

Thursday, February 20, 2014

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በራሱ ረዳት ካፕቴን መጠለፍ የአገራችንን የአመራር ችግሮችና የሃሣብ ድህነት ክፉኛ አጋልጧል!

የካቲት 17 በጥዋት የጠለፋውን ዜና እንደስማሁ፡ የቅድምያ ተግባሬ ያደረግሁት ለማዘጋጀው ድህረ ገጽ መረጃዎችን ማሰባስብና መረጃዎቹን መመዘን ነበር። ለዚህም ስል: ያሰባስብኩት መረጃ ምን ያህል ለእውነተኝው ሁኒታ ቅርበት አለው የሚለውን በመመዘን ጥቂት ጊዜ አሳለፍሁ።
Ethiopian Airlines was absorbed by the TPLF mafia
አንዳንዶቹ ለጊዜው ትክክል ባይሆኑም፡ እንዳለ ማቅረቡ ምክንያታዊ እስከሆኑ ድረስ: ዛሬ ያለውን የመረጃ ጥማት ማርካት ብቻ ስይሆን፡ ለወደፊትም አንድ ሁኔታ በዓለም አቀፍ የዜና አውታሮች እንዴት ተዘገበ ለሚለው በምስክርነት ሊረዳ ይችላል።
በወቅቱ በአንድ ጊዜ፡ በተከታታይ በገጼ ላይ እንዳቀረብኩት ሁሉ፡ ብዙ የውጭ ምንጮችን ቃኝሁኝ። ጠቃሚ መረጃዎችንም አገኝሁኝ። በዚያን ወቅት አንድ ነገር ያላድረግሁት ነገር፡ መረጃ ከኢትዮጵያ ለማግኝት መሞከር ነበር። አንደኛ መረጃ ቢኖራቸውም፡ ቀዳሚው መንፈሳቸው የሚቀናው መረጃውን ማፈን ነው!
በሌላ በኩል ደግሞ፡ አውሮፕላኑ ከተጠለፈበት አገር በመጀመርያ ደረጃ መረጃ ማግኘቱ ጠቃሚነቱ ቢታወቅም፡ እንደ ኢትዮጵያ ዐይነት መረጃ መጀመርያ በባልሥልጣኖች መወሰን ባለበት ሃገር ውስጥ፡ ሲተሻሹ ጀምበር ስለሚጠልቅባቸው፡ የሃገር ውስጥ ሚዲያ ዜናውን እንዲያወራ ቢፈቀድለት እንኳ፡ እነርሱም እኛ ገና በማለዳው ያየናቸውን የሮየተርስ፡ ቢቢስ፣ ሲኤኔአንን ወዘተ ነው መልሰው የሚደጋግሙት።
ለማንኛውም፡ አቶ ረድዋን ሁሴን ወደሚዲያ ከቀረቡበት ክረፋዱ በኋላ የነበረው ሁኔታ ግን ክፉኛ ተሳከረ።
አንድኛ፡ ሥዕል ውስጥ ጠላፊው ረዳት ካፒቴን አንድ መሆኑ ቀርቶ ክአንድ በላይ የሆኑ ጠላፊዎች አውሮፕላኑ ውስጥ መግባታቸውን አስሙን።
ሁለተኛ፡ አውሮፕላኑን የጠለፊው ሰው እኔነኝ ብሎ ጠላፌው እጁን ለስዊስ መንግሥት ከሰጠ በኋል: አቶ ረድዋን ጠላፊዎቹ እያሉ በሕዝበ መገናኛ ላይ መንዛታቸውን ቀጠሉ።
ሶስተኛ፡ የዚህ ዐይነት አጣዳፊ ሁኔታ፡ በየፈጣን ደቂቃዎች የሚለዋወጡበት በመሆኑ አስቸጋሪነቱ ግልጽ ነው። ቢሆንም፡ አቶ ረድዋን የተለመደውን የመንግሥታቸውን ቀጣፊነት ባህሪ ማንጸባረቅ ስለነበረባቸው፡ ትኩረታቸው ያረፈው፣ የራሳቸው ዕውነታ (realty) ላይ ሆኖ ዜና ፈጠራ ላይ ነበሩ። ይህም እርሳቸውን እንደግለሰብ ቀባጣሪ ከማድረጉም በላይ፡ ሀገራችንን አሳፋሪ ሁነታ ላይ ጥሏታል።
በእዲህ ያለሁኒታ ውስጥ፡ ማንኛውም ባለሥልጣን ተረት ተረት (fiction) ከመፍጠር ይልቅ፡ በሠለጠነው ዓክም እንድሚደረገው፡ “ለጊዜው መረጃ የለኝም፡ እስካገኝ ጠብቁኝ” ማለቱ ያስከብራል እንጂ አያስንቅም – ባልሥልጣኑ ቃሉን ጠብቆ ያ መረጃ ካለበት ቦታ ቆፍሮ ለጠያቂዎቹ የማቅርብ ቁም ነገርኝነቱን እስካስመስከረ ድረስ!
መንግሥታቸው ለሥልጣኔ አስጊ ናቸው ብሎ የሚጠራጠራቸውን ንጹሃን “አሽባሪዎች” እንደሚላቸው ሁሉ፡ ከዚህ የአውሮፕላን ጠላፍ ጋር በተያያዘ አቶ ረድዋን ዋናዋ ተጠራጣሪ ሱዳን መሆኗን የራሳችውን ውንጀላ ሠነዘሩ።
እኔ የሱዳን ባለሥልጣን ብሆን አንድ ትልቅ የዲፕሎማቲክ የቅሬታ ማስታወሻ (demarche) ለአዲስ አበባ ሳይውል ሳይድር እንዲቀርብ አደርግ ነበር። ለማንኝውም እነዚያም እጆቻቸው ብዙም ጻዳ ባለመሆናቸው፡ ብዙም ላይረበሹ ይችሉ ይሆናል። እንዲያውም፣ የተባበሩት መንግሥታት የራሱንና የአፍሪቃ አንድነት ድርጅትን ስላም አስከባሪ ሃይል ዳርፉር ውስጥ በሥውር በመውጋት ላይ የምተገኘው ራሷ ሱዳን ናት የሚለው የእሁዱ ክስ በቂ ምስክርነት ይሰጣል። (UN report points finger at Sudan over UNAMID attacks)
ሌላው አስገራሚው ነገር፡ የኢትዮጵያ ቴሊቪዥን ቅጥፈት ነው። የአውሮፕላኑ ጠላፊ ረዳት ካፒቴን “ኃይለመድህን አበራ” (ክአህራም የተገኝ) ክሲቪል አብቭዬሽን ሠራተኞች ጋር ተደጋጋሚ የአየር ላይ ግኑኝነት አድርጎ በመስኮት ወጥቼ መጣለሁ ማለቱን እየስሙና: እጁን በሰላማዊ መንገድ ለስዊስ ፖሊሶች መስጠቱ እየተስማ፡ “ሊያመልጥ ሲል ተይዞ በቁጥጥር ሥር ዋለ” በማለት ያቀረቡት ሀስት ዜ ለአንዴና ለመጭረሻ ጊዜ አገራችን ምን ያህል በወበዴዎች ቁጥጥር ሥር መሆኗን አረጋግጦልኛል።
ይህ ደግሞ የሚመነጨው – በቅርቡ በረከት ስምኦን እንዳለው – ከሕዝብ ንቀት ነው። የፈለግነውን ብንቀባጥርለት የኢትዮጵያ ሕዝብ ያምነናል ከሚል የዋህ አስተሳሰብ ነው። በዚህ ሁኔታ ውስጥ ራስቸውን ብቻ ነው ያዋረዱት!
በራሱ ካፕቴን የተጠለፈው አየር መንገድ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በራሱ ረዳት ካፕቴን መጠለፍ፡ በዓለም ታሪከ ውስጥ ውሱንና ጥቂት ተጠቃሽ ምሳሌዎች ያሉት ውርደት ነው። በባለሙያ ደረጃ ግለስቡ ደህና ደሞዝ ያገኛል (በአንጻራዊ ደረጃ ከኅብረተስቡ ጋር ሲወዳደር – ከሕወሃት ባልሥላጥኖችና ካድሬዎች ጋር ባይሆንም)። ስለዚህ ይህ ሰው የኢኮኖሚ ጉዳይ ነው እንዲሰደድ ወይንም አውሮፕላን ጠልፎ ስደት እንዲጠይቅ ያስገደደው ለማለት አይቻልም።
ይህ ሁኔታ ደግሞ አገራችንን ወደተጠናወታት፡ የመብት ረገጣና የስብአዊ መብቶች ገፈፋ እያመለከተ ነው። ጤንነቱን መጠራጥር አይቻልም – የመንግሥት የፕሮፓጋንዳው ሹም፡ ፓይለቱ የወንጀል ሪኮርድ የለበትም፡ ጤንነቱንም በተለመከተ “was medically sane until otherwise proven” ሲሉ መናገራቸውን ቢቢሲ ስኞ ከቀትር በኋላ ዘግቦታል
ይህ ደግሞ ወደዋነኛው ሀቅ ይመልስናል – ይህም የኢትዮጵያ ችግር የመንግሥትና የአስተዳደር እንጂ፡ ሌላ እንዳልሆነ ነው!
በሕወሃት አመራር ወዳዘቅቱ
የኢትዮጵያ ችግር ከቀን ወደቀን እየከፋ የመጣው በዘረኛው መንግሥት ፓሊሲዎች ምክንያት ነው። ሲሻው አማራ፡ ኦሮሞ፡ ሶማሌ … ብሎ ከፋፍሎ ሊያባላን የተነሳ መንግስት ነው ያለን። በቅርቡ ሆድ አደር አዝማሪ በፓለቲካ አመራር አማክይነት በብአዴን ድሕፈት ቤት ሃላፊ የተሰነዘረው – በዓለም አቀፍ ሕግ በሰው ዘር ላይ የተፈጸመ ወንጅል ተደርጎ የሚወስደው – ጸረ አማራ ወራዳ የስድብ ጋጋታ ሥርዐቱ ከነሥረ መሠርቱ ያለውን ብልሹነትና ወንጀልኝነት የሚያሳይ ነው።
ባልሥልጣኖቹ ይህን ባስተጋቡ መጠን ተለክቶ የፓሊቲካ ጽዋቸው ይሠፈራል! መዘንጋት የሌለበት፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባለፈው ዓመት በስመ ኦሮሞ ነጻ አውጭ ውንጀላ ፓርላማ ውስጥ ያስሙት/ያሰማው ጸረ-ኦሮሞ አነጋገር፡ በዘፈቀደ የመጣ አይደለም – ሕወሃት ሀገራችን ውስጥ የዘራው ቫይረስ ውጤት ነው!
በቅርቡ የአገሪቱን ዳር ድንበር በመሽረፍ ለሱዳን የአርሻ መሬት ለመስጠት የተደረገው ምሥጢራዊ ስምምነት፡ ለኢትዮጵያም ሆነ ለሕወሃት ትልቅ የጥፋት ምንጭ ይሆናል። ጸጥ በለው ክርመው፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ፡ ስሞኑን ይህንን ለማስተባበል ሞክሩ። ሆኖም፡ ሃይማኖተኛ ነኝ የሚል መልዕክት ለማስተላለፍ ብዙ ጊዜ ሞክረዋል። ሥልጣን ከያዙበት ጊዜ ጅምረው ባሉት 18 ወራት ግን ሃይማኖታቸው ሃስት መናገርን ሲከለክላቸው አልተመለክትንም።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ መሸርሸር
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ኩራታቸን ክሆነባቸው ምክንያቶች አንዱ የፓይለቶቻችንና የመካኒኮቻችን ብቃት፡ እስከቅርብ ጊዜ ድረስ የኩባንያውያን ኢትዮጵያውያንነት ለማሳደግና ለማበልጸግ ማስቻሉ ነበር።
ዛሬ ግን ኢትዮጵያዊ ፓይለቶች በዘር ልዩነት ምክንያት እየተገፉ፡ የሚወዱትን ኩባንያ እየተዉ ወደመካከለኛው ምሥራቅና በየአህጉሩ እይተበተኑ ናቸው። ዛሬ በጣሊያን አብራሪ የሚመራው አውሮፕላን – ኢትዮጵያዊ ሳይሆን – መጠለፍ፡ በዘረኛው ሕወሃት መዳፍ ሥር አገራችን በየፊናው የምታመራበትን አዘቅት የሚያመላክት ነው!
ኢትዮጵያውያን ለአገራችን ቀናተኞች ነን- አገርን አሳልፎ መሽጥ ባህላችን አይደለም። አልጨበጥ ባይነት፡ ቀባጣሪነትነና በዜጎች ጉስቅልና ላይ የፕሮፓጋንዳ ድራማ መሥራት (ሳኡዲ በነበሩት ላይ እንደተፈጸምው ሁሉ)፡ ኃይልን ተገን አድርጎ መክናፈስ ፍጻሜው መጥፎ ነው – ታሪክ እንደሚያሳየን!
ታዲያ በጥቂቶች ጠባቦችና የሥልጣን ባለጌዎች መጥፎነት ለምን መላው ሃገር ይታመሳል? ህገርስ ዐይናችን እያየ ለምን አገር ወደአዘቅት ታምራ?
ይህንን የመገንዘቡ አዝማሚያ በማይታይበት በዚህ ሁኔታ ውስጥ እንዴት ነው ዜጎች በየቀኑ እየተገፉ እየተረገጡ ሊቀጥሉ የሚችሉት? በመንግሥት ሥልጣን ላይ መንግሥታዊ ባህሪ የሌላቸው ስዎች በመቀመጣችው፡ የባሱ ዜጎችን የሚያሽማቅቁ፡ አገር ሊያውርዱ የሚችሉ፡ ትውልድን የሚያሳፍሩ ገና ብዙ ነግሮች ሊመጡ ይችላሉ – በመንግሥት ላይ የሠፈሩት ሆድ አደሮች ቆም ብለው ከአሁኑ አሳፋሪ ነገር አንዳችም መማር ካልቻሉ።
በነገራችን ላይ፡ ገና ከማለዳው አውሮፕላኑ እንደተጠለፈ የብዙዎቹ ዓለም አቀፍ የዜና አውታሮች ገለጻ: ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው የስብአዊ መብቶች ላይ ማተኮራቻው በቂ ምልክት ተደርጎ ሊወስድ ይገባል!http://ecadforum.com/Amharic/archives/11047/

Tuesday, February 18, 2014

ኢህአዴግ ራሱ ባወጣው አፋኝ ሕግ ታፈነ

ለተፈጥሮ ሃብት የጠየቀው ዓለምዓቀፋዊ እውቅና ውድቅ ሆነ
eiti


ኢህአዴግ የተፈጥሮ ሃብትን በትክክለኛ መንገድ ለሕዝብ ጥቅም መዋሉን በመከታተል ለአገራት እውቅና የሚሰጠው The Extractive Industries Transparency Initiative (EITI) ለተሰኘ ዓለም ዓቀፋዊ ተቋም ያቀረበው የእውቅና ጥያቄ ማመልከቻ ከተገመገመ በኋላ መመዘኛዎቹን ማሟላት ባለመቻሉ መውደቁ ተሰማ። ኢህአዴግ የእውቅና ማመልከቻ በድጋሚ ማስገባቱን አስቀድሞ ያወቀው ዓለምአቀፉ የሰብዓዊ መብት ጥበቃ ድርጅት (Human Rights Watch) ጉዳዩን ከሚከታተሉ ጋር ባገኘው መረጃ ኢህአዴግ የEITI መስፈርት የማያሟላና በሰብአዊ መብት ጥሰት የተወነጀለ ድርጅት መሆኑንን ማስረጃ አስደግፎ በመጥቀስ መሟገቻ ደብዳቤ ለድርጅቱ አስገብቶ ነበር።
EITI የዛሬ 11ዓመት አካባቢ የተቋቋመ በተፈጥሮ ሃብት ዙሪያ ዕውቅና የሚሰጥ ድርጅት ነው፡፡ ድርጅቱ የተፈጥሮ ሃብት የህዝብ መሆኑን የሚያምን ሲሆን ማንኛውም የተፈጥሮ ሃብት – ማዕድን፣ ዘይት፣ ብረታብረትና ጋዝ – ከመሬት በሚወጣበት ጊዜ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ የሚኖረውን ያህል ግልጽነትና ተጠያቂነት በሌለባቸው አገራት ድርጊቱ ለሙስና እና ግጭት በር እንደሚከፍት ይናገራል፡፡ በመሆኑንም ድርጅቱ አገራት ለሚያቀርቡት የዕውቅና ጥያቄ ማሟላት ያለባቸውን መስፈርት በዝርዝር አስቀምጧል፡፡ ልማትና እድገት በሚል ሰበብ የሕዝብ ሃብት የሆነውን የተፈጥሮ ሃብት በማውጣት የህዝባቸውን መብት ለሚረግጡ አገራት የሚያቀርቡትን የዕውቅና ማመልከቻ ውድቅ ያደርጋል፡፡
የጎልጉል የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ምንጭ እንደጠቆሙት ኢህአዴግ ያቀረበው የእውቅና ጥያቄ ውድቅ መደረጉ እውነት ነው። ምንጩ እንዳሉት ኢህአዴግ በውሳኔው በመበሳጨት ይግባኝ ለመጠየቅ በዝግጅት ላይ ነው። ድርጅቱ (EITI) አንድ አገር ለሚያቀርበው የእውቅና ማመልከቻ በመስፈርቱ መሰረት ግምገማ ካካሄደ በኋላ እውቅና እንዲሰጥ ሲያምን በራሱ ድረገጽ ላይ የዚያን አገር ስም በመመዝገብ ተጠቃሹ አገር ከተፈጥሮ ሃብት ጋር በተያያዙ ኢንቨስትመንቶች የሚገኘው ትርፍ ለህዝብ ጥቅም እንዲውል ያደርጋል የሚል እውቅና በመስጠት ምስክርነቱን ያሰፍራል፡፡
ኢህአዴግ የመጀመሪያው የማመልከቻ ጥያቄ ያቀረበው በአውሮጳውያኑ አቆጣጠር በ2009 አካባቢ ነበር፡፡ ከEITI አምስት መስፈርቶች መካከል አንዱ፤ ማመልከቻ የሚያቀርቡ አገራት ከመያዶች (መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች) ጋር ለመስራት ያላቸው ፍላጎት ተጠቃሽ ነው፡፡ በወቅቱ ኢህአዴግ በመያዶች ላይ አፋኝ ሕግ አውጥቶ የነበረ በመሆኑ እውቅና ሰጪው ድርጅት – EITI – የኢህአዴግን ማመልከቻ ውድቅ አድርጎታል፡፡ የEITI ቦርድ ይህን ዓይነት ውሳኔ ሲያስተላልፍ ያሰፈረው ነገር ኢትዮጵያ በእጩ አባልነት ለመመዝገብ በመጀመሪያ በመያዶች ላይ ያወጣችውን ሕግ ማስወገድ አለባት የሚል እንደነበር የሰብዓዊ መብት ጥበቃ ድርጅት በድረገጹ ላይ አስቀምጦታል፡፡ በወቅቱ የተሰጠው ይህ ብያኔ በEITI እውቅና አሰጣጥ ታሪክ ውስጥ የመጀመሪያ እንደሆነ ተጠቁሞም ነበር፡፡
የEITI ዕውቅናን ለማግኘት ቋምጦ የነበረው ኢህአዴግ በድርጅቱ ውሳኔ ባለመደሰት ጥቂት ዓመታትን ቆጥሮ ከአቶ መለስ ሞት በኋላ በአቶ ሃይለማርያም በመመራት በድጋሚ ዕውቅና የማግኘት ዘመቻውን ማጠናከር ጀመረ፤ በይፋም እንቅስቃሴውን ቀጠለ፡፡ የማዕድን ሚ/ር መ/ቤትም ዕውቅና ማግኘቱ በጣም የሚያስፈልግ እንደሆነ በይፋ በመናገር ዘመቻውን አጧጡፎ ነበር፡፡ ከዚህም አልፎ ለዓመታት ሲጠቀምበት የነበረውን አሠራር በዓለምአቀፉ ድርጅት ላይ ተግባራዊ በማድረግ ኢህአዴግ Ethiopia Revenue Transparency Initiative (ERTI) የሚባል “ተለጣፊ” ተቋም በመመሥረት እንቅስቃሴ ሲያደርግ እንደቆየ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቱ ለEITI በጻፈው ደብዳቤ ላይ ገልጾዋል፡፡
ጉዳዩን በቅርብ ይከታተሉ የነበሩ የዲፕሎማቲክ ምንጮች ኢህአዴግ በአውሮጳውያኑ አቆጣጠር 2013ዓም በድጋሚ ማመልከቻ የማቅረብ ዓላማ እንዳለው ለዓለምአቀፉ የሰብዓዊ መብት ድርጅት አሳወቁ፡፡ በወቅቱ ኢህአዴግ ማሻሻያ እያደረጉ ነኝ የሚል ማስመሰያ ለማቅረብ የሞከረ ቢሆንም የመያዶችና የጸረ አሻባሪነት አፋኝ ሕጎቹ በተጨማሪ በቴሌኮሙኒኬሽን በኩል በስልክና ኢንተርኔት የሚያደርውን ህዝብን የመሰለል ተግባር አጠናክሮ የቀጠለበት እንደሆነ በመጥቀስ ጉዳዩን በቅርብ የሚከታተሉ ክፍሎች EITI ዕውቅና እንዳይሰጥ መወትወታቸውን ተያያዙ፡፡
እነዚሁ ወገኖች በተደጋጋሚ ያደረጉት “የወረቀትና የፔቲሽን ትግል” እየተባለ የሚቃለለው ትግል ውጤት በማምጣት ኢህአዴግ በደጋሚ ያስገባው የአባልነት ማመልከቻ ሰሞኑን ውድቅ መደረጉ ተሰምቷል፡፡ እንደ መረጃው ከሆነ EITI ማመልከቻ በሚመዝንበት በሁሉም መስፈርቶች ኢህአዴግ ወድቋል፡፡
አነስተኛ ደረጃ ላይ የሚገኙና ኢህአዴግ “ልማታዊ” የሚላቸው ኢንቨስተሮች ሳይሆኑ በከፍተኛ ደረጃ የሚመደብ መዋዕለ ንዋይ የሚያፈሱ ባለሃብቶች ኢንቨስት የሚያደርጉበትን አገር ለመምረጥ የመጀመሪያው መለያቸው የEITI ድረገጽ የአባል አገራት ዝርዝር እንደሆነ ስለ አሰራሩ የሚያውቁ ይናገራሉ። ኢህአዴግም አስፈላጊውን የምዝገባና የማመልከቻ መስፈርት በማሟላት የተቋሙን እውቅና የጠየቀው በድርጅቱ ድረገጽ ላይ ለመመዝገብ ነበር። የሁለት ጊዜ ሙከራው መክሸፉ ኢህአዴግ ራሱ ባወጣው አፋኝ ህግ መታፈኑ የሚያመላክት እንደሆነ የሚጠቅሱ ክፍሎች፤ ከኢህአዴግ ከፍተኛ ፍላጎት አኳያና ሰሞኑን በተለያየ አቅጣጫ እየተወጠረ ከመምጣቱ አንጻር ሁኔታው አጣዳፊና ፋታ የማይሰጥ በሽታ ምልክት እንደሆነ በምጸት ይናገራሉ፡፡
ስለEITI ውሳኔ ባጭሩ እንዲያብራሩልን የጠየቅናቸው ባለሙያ እንዳሉት “አንድ ዩኒቨርሲቲ ህንጻ በማስገንባቱና አስተማሪዎችን በመቅጠሩ ብቻ ዩኒቨርስቲ ተብሎ ሊጠራ አይችልም። ዩኒቨርስቲው ዓለም ዓቀፍ ደረጃውን የጠበቀ ስለመሆኑ በዓለም አቀፍ መስፈርት መሰረት ተገምግሞ እውቅና የሚሰጠው መስፈርቶቹን በሙሉ አሟልቶ ስለመገኘቱ ምርመራ ተደርጎበት ፈተናውን ሲያልፍ ብቻ ነው። በዚሁ መሰረት አልፎ እውቅና ያላገኘ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ገብቶ መማር የተሳትፎ ያህል ነው። መስፈርቱን አሟልተው እውቅና ካገኙት ጋር መወዳደር ስለማይችል ተመራጭ አይሆንም። በተመሳሳይ Extractive Industries Transparency Initiative (EITI) የተባለው ድርጅትም ከየአገራቱ እውቅና እንዲሰጥ የሚቀርብለትን ጥያቄ /ማመልከቻ/ የሚመዝንበት መስፈርቶች አሉት። ኢህአዴግ የተፈተነው በዚሁ አቅልጦና አንጥሮ በሚያወጣው መመዘኛ ነው ብለዋል፡፡”
ስለጉዳዩ የተጠየቀው የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ /አኢጋን/ የህዝብ ግንኙነት ግብረ ኃይል ጉዳዩን በጥልቀት የሚያውቀውና ገና ከጅምሩ ሲከታተል የቆየው መሆኑን በመግለጽ በበርካታ ፈርጆች ከሚያካሂደው ትግል አንጻር በዕቅድ ሲያከናውነው የቆየ መሆኑን አመልክቷል። የህዝብ ግንኙነት ክፍሉ ለጎልጉል እንዳለው ከሆነ “የEITI ውሳኔ ኢትዮጵያን እንደ አገር የሚጎዳ መሆኑ ግልጽ ነው፤ ሆኖም ውሳኔው ኢህአዴግ በራሱ ግትረኝነትና እብሪት ያመጣው ጣጣ በመሆኑ የራሱን ተግባር ተከትሎ የተወሰነው ውሳኔ በአገሪቱ ላይ በማንኛውም መልኩ ለሚያደርሰው ኪሳራ ተጠያቂው ኢህአዴግና ህወሃት ናቸው” ብሏል። በማያያዝም የጋራ ንቅናቄው ይህንኑ ጉዳይ አስመልክቶ መግለጫ በማውጣት አስፈላጊ ናቸው ለሚላቸው ወገኖች እንደሚበትንና ተቋሙ በውሳኔው እንዲጸና የሚቻለውን ሁሉ በማድረግ ላይ ለተሰማሩ መልዕክት እንደሚያስተላልፍ አመልክቷል።http://www.goolgule.com/

Monday, February 17, 2014

እየተዋረዱ መገዛት እስከመቼ!?

አለምነው መኮነን የተባለ የብአዴን ወኪልና የባንዳ አስፈፃሚ የአለቆቹን የዘወትር አባባል በማስረገጥእመራዋለሁ የሚለውን የአማራ ህዝብ <<ሰንፋጭ የሆነ ትምክህተኝነት የተጠናወተው፤ ትምክህተኝነቱንያልተው፤ በባዶ እግሩ እየሄደ መርዝ ንግግር የሚናገር ወዘተ>> ካለ በኋላ <<የትምክህት ልጋጉን ማራገፍአለበት>> በማለት እንደሌሎች ብሄረሰቦች ሁሉ ደከመኝ፡ ሰለቸኝ ሳይል ዋጋ የከፈለውን የአማራ ህዝብ ዋጋበማሳጣት የሌሎቹ ጠላት አድርጐ በማቅረብ፡ የዘረኞች ተባባሪነቱን አስመስክሯል። 
የአማራው ህዝብ የወያኔ ዘረኞች ዋነኛ ዒላማ ሆኖ የአገዛዙን የግፍ ፅዋ ያለማቋረጥ መጋት ከጀመረ ድፍን 23 አመታት ተቆጠሩ። ፋሽስቱ ወያኔ የኢትዮጵያን ህዝብ ብሔራዊ ስሜት በማምከን ፣ የዘመናት ተገዥነቱን ለማረጋገጥ በቅድሚያ የአማራን ሕዝብ ማንነት ማጥፋት ፣ የአማራን ሕዝብ ስነ ልቦናዊ ጥንካሬ መስለብ እና አንገቱን ማስደፋት አስፈላጊ መሆኑን በጽናት ያምናል። ይህ በመሆኑም ፣ በአማራ ህዝብ ላይ በወያኔ የሚፈፀመው ግፍ እና በደል ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ ስር እየሰደደና እየከፋ በግልፅም በስውርም በተቀነባበረ መንገድ ቀጥሏል።
ይህ የህወሀት የጸረ አማራ ፕሮፓጋንዳ ማሽን የሚመራው በዋና ዋናዎቹ የወያኔ  ሹሞች ቢሆንም ወያኔ የአማራን ህዝብ የሚገድለዉ፤ የሚያዋርደዉና የሚያሳደድዉ አማራ ነን በሚሉ ነገር ግን የአማራን ህዝብ በጅምላ በሚሰድቡና አማራዉ ሲገደል፤ ሲታሰርና ሲፈናቀል ይበልህ በሚሉ በእነ አለምነው መኮንን አይነት ወፍ ዘራሽ ካድሬዎች ነው። አንበሳ ሲያረጅ የዝንብ መጫወቻ ይሆናል እንዲሉ፡ የአማራው ህዝብ ዛሬ ቀን ጣለውና፣ በጠላቶቹ እጅ ወደቀ፣ የድፍን ስድና መረን ያደገ ዋልጌ ሁሉ የስድብና የዘለፋ አፍ ማሟሻ የመሆን ዕጣ ደረሰው። አለምነው መኮነን የተባለ የብአዴን ወኪልና የባንዳ አስፈፃሚ የአለቆቹን የዘወትር አባባል በማስረገጥ እመራዋለሁ የሚለውን የአማራ ህዝብ <<ሰንፋጭ የሆነ ትምክህተኝነት የተጠናወተው፤ ትምክህተኝነቱን ያልተው፤ በባዶ እግሩ እየሄደ መርዝ ንግግር የሚናገር ወዘተ>> ካለ በኋላ <<የትምክህት ልጋጉን ማራገፍ አለበት>> በማለት እንደሌሎች ብሄረሰቦች ሁሉ ደከመኝ፡ ሰለቸኝ ሳይል ዋጋ የከፈለውን የአማራ ህዝብ ዋጋ በማሳጣት የሌሎቹ ጠላት አድርጐ በማቅረብ፡ የዘረኞች ተባባሪነቱን አስመስክሯል።
በርግጥ ወያኔ እንደፈረስ የሚጋልበው ብአዴን በታሪኩ አንድም ለህዝቡ የቆመ መሪ ሲያፈራ አልታየም። የአማራ ህዝብ ብአዴንን የመሰለ አሳፋሪ ድርጅት በታሪኩ ገጥሞት አያውቅም። በባዕድ ወረራ ጊዜ ለጣልያን ያደሩ ባንዶች እንኳን ከዛሬዎቹ ብአዴኖች የተሻለ ክብር ነበራቸው። ከዛሬዎቹም በተሻለ በጌቶቻቸው ጣሊያኖችን ይሰሙ ነበር። ብአዴን ግን ራሱን ከባንዳነትም አውርዶ ባርነት ደረጃ ላይ የጣለ ከመሆንም አልፎ  በባርነቱ የሚደሰት ድርጅት ነው። ብአዴን የህወሓት ወያኔ ወኪል እንጅ የአማራው ህዝብ ወኪል አይደለም፡፡ ብአዴን ሁሌም የአማራውን ህዝብ እንደ ሰደበ፣ እንዳዋረደ፤ እንዳስገዛ ነው፡፡ የብአዴን ፍሬ የሆነው አለምነው የተባለው የእናት ጡት ነካሽም በድጋሚ ያረጋገጠልን ይንኑ ነው። አለምነዉ እነዚያን እጅግ አሳፋሪና ከፋፋይ ንግግሮች የተናገረዉ ፀረ አማራና ፀረ-ኢትየዮጵያ ጌቶቹን ያስደሰተ መስሎት ወይም የሥልጣን ቆይታውን ያመቻቸና በሥልጣን መሰላል ሽቅብ የተወነጨፈ መስሎት ሊሆን ይችላል፤ ሆኖም የአማራ ህዝብና ወገኑ የሆነዉ ሌላዉ የኢትዮጵያ ህዝብ ይህንን የአንድን ህዝብ ስብእናና ክብር የሚያጎድፍ  ንግግር በምንም መልኩ ችላ ብሎ ሊያልፈዉ አይገባም፡፡
እንደሚታወቀው ዘረኛው ወያኔ የጸረ አማራነት አቋሙ እጅግ የከፋ ፣ ስር የሰደደ እና በድርጅት የታቀፈ ነዉ፤ እኛም በድርጅት ታቅፈን በድርጅት ካልገጠምነዉና ካልደመሰስነዉ በቀር የወያኔ ዘረኝነት መቆሚያና ማለቂያ የለዉም። ለምሳሌ ፋሽስቱ ወያኔ በቅርቡ በቤኒሻንጉልና በቤንች ማጅ ዞን ጉራፈርዳ ወረዳ ዉስጥ አማራውን በማፈናቀል አማሮች ከአማራ ክልል ዉጭ መኖር አትችሉም ብሏል። የወያኔ ዘረኞች እነሱ በዘጠኙም ክልል እንዳሻቸዉ እየዞሩና ኃብት እያጋበሱ አማራዉን ግን እንደ ውጭ ዜጋ በማየት በገዛ አገሩ ውስጥ ከቦታ ወደ ቦታ እንዳይንቀሳቀስ በማድረግ አማራዉ ሳይወድ በግዱ የስደት ገፈት ቀማሽ እንዲሆን አድርገዉታል። ኧረ ለመሆኑ ይህ የግፍ ፅዋ ሂትለር በጀርመን በይሁዳዎች ላይ ከፈፀመው በምን ይለያል? እንደምናስታውሰው በሽግግሩ ወቅት ጠቅላይ ሚንስትር በነበረው ታምራት ላይኔና በወቅቱ ፕረዜዳንት በነበረው ሟቹ መለስ ዜናዊ በተፈራ ዋልዋ አቀናባሪነት በተሰጠ ትእዛዝ በወተር፤ አርባ ጉጉና በበደኖ ኦህዴድና ኦነግን በየፊናው አስማርተው የኋላ ድጋፍ እየሰጡ ውድ ወገኖቻችን ህይወታቸው ስታልፍ እንደ እንሰሳ ቆዳቸው መገፈፉ፤ ሳይሞቱ በገደል ሲጣሉና ሕጻን ሽማግሌ ሴት ወንድ ሳይለይ በጅምላ የማለቃቸውን ሃዘን ሳንረሳው ዛሬ ደግሞ ዳግም የጠብ አጫሪነቱን፡ በምን ታደርጉኛላችሁ እብሪት ተወጥሮ በባንዳው አለምነው መኮነን አስፈፃሚነት ለክልሉ ህዝብ ያለውን ከፍተኛ ንቀት ሬት ሬት በሚሉና አጥንትን የሚሰረስሩ ስድቦችን በመጠቀም አንካችሁ አሉ። አለምነው መኮነን የረጨውን መርዝ እስኪ አስቡት ወገን? ማንን ተማምኖ፡ የልብ ልብ ተሰምቶት ይመስላችኋል ይህ የመርገምት ልጅ ይህን ያህል ልሃጩን በጨዋው የአማራ ህዝብ ላይ የሚተፋበት? አረመኔውን የፋሽስት አገዛዝ አደለምን። ኧረ ግን አማራው እስከመቼ በዚህ የፋሽስት ስርአት እየተገደለ፡ እየተሰደደና እየተዋረደ መኖርን መረጠ? ኧረ ዝምታው ምንድነው? ግን እስከመቼስ ይሆን?
ውድ የኢትዮጵያ ህዝብ ሆይ!
ፋሽስቱ ወያኔ በአማራ ህዝብ ላይ በተከታታይ በማድረስ ላይ ያለዉ በደል፤ ግፍና ዉርደት የወያኔ ዘረኞች ሊነግሩን አንደሚፈልጉት የአማራዉ ጉዳይ ነዉ ተብሎ የሚታለፍ ጉዳይ አይደለም።ይህ ዛሬ በአማራዉ ላይ እየፈጸመው ያለው ዘርን የማዋረድና የማጥፋት ርካሽ ስራ ነገ በእያንዳንዳችን ላይ የሚደርስ መሆኑን ልንረዳ ይገባል። የወያኔ ወንጀል አሁን የተጠነሰሰ ሳይሆን ወያኔ ገና ደደቢት በረሃ ላይ ሲጠነሰስ አብሮት የተጠነሰሰ ሴራ ነዉ። ወያኔና ዘረኛ ስርአቱ እስካልተወገዱ ድረስ ይህ የተጀመረው አማራን የማዋረድ፡ የመጨፍጨፋ፣ የማፈናቀልና የማሳደድ ዘመቻ፣ ተጠናክሮ መቀጠሉ አይቀርም። ወያኔ አማራዉን ካዳከምኩ ሌላዉ አያቅተኝም በሚል ዘረኛ ስሌቱ ዛሬ አማራዉ ላይ አተኮረ እንጂ በወያኔ የተደበደ ፣ የታሰረ፣ የተሰደደ፤ የተፈናቀለ ፤እንዲራብ የተደረገ፤ የተዋረደና የተገደለ ኢትዮጵያዊ ስፍር ቁጥር የለዉም። ዛሬ  የአማራው ህዝብ ብቻ ሳይሆን ድፍን የኢትዮጵያ ህዝብ በወያኔ ጨካኝ ስርአት አማካኝነት በጨለማ ሂዎት ውስጥ እየማቀቀ ነው። ስለዚህ ችግሩ የአገርና የወገን የህልውና ጉዳይ እንጅ  የፖለቲካ ጨዋታ ባለመሆኑ የወጣት፣ አዋቂ፣ ጎልማሳ፣ ሽማግሌ፣ ጾታ ሳይለየን ወያኔን ለማስወገድ በሚደረገው ትግል ምላሽ በመስጠት አለበት ባይ ነኝ። በአማራው ህዝብ ላይ የጠቆረውን ጨለማ በብርሃን መተኪያ ጊዜው አሁን ነው። ይህ ትውልድ የታሪክ ባለእዳ አይሁን።
በወያኔ ዙሪያ ተሰብስባችሁ የሥርዓቱ ጠባቂና ተጠቃሚዎች የሆናችሁ በሙሉ ባሳለፋችሁት የግዛት ዘመናችሁ የአማራውን ዘር ብትሰድቡትም፡ ብትገድሉትም፡ ብታስሩትና ብታስርቡትም፤ ብታሰድዱትም፤ ሀብት ንብረቱን ብትዘርፉትም፤ በአገሩ በኢትዮጵያ የመኖር መብቱን ብትገፉትም ሕዝቡ መሃሪ ነውና ዛሬውኑ የሕዝቡን ትግል ብትደግፉና ብትቀላቀሉ ይሻላል።  በተለይ አማራ ሆናችሁ ብአዴን የሚባል የፋሽስቱ ወያኔን የጥፋት ክንፍ ስታገለግሉ፡ እስከ ዛሬ በሆዳችሁ ስትገዙ የኖራችሁ እንደ አለምነው መኮንን አይነት የእፉኝት ልጆች ሕዝባችሁን የማዋረድና፤ የማድማት ተልኮዋችሁን አቁማችሁ፤ ወያኔ በወገኖቻችሁ ላይ እየፈጠረ ያለው ችግር ተሰምቷችሁ፤ ህዝባችሁን ይቅርታ ጠይቃችሁ፤ አሁኑኑ ለትግሉ ምላሽ በመስጠት መከታ በመሆን አዝሎ ያሳደጋችሁን ህብረተሰብ ከባርነት ቀንበር ታላቅቁት ዘንድ ወገናዊ ጥሪየን አቀርባለሁ። ለውሳኔው አለማርፈዳችሁን በዚሁ አጋጣሚ ላረጋግጥላችሁ ጭምር እወዳለሁ።
ድል ለጭቁኑ የኢትዮጵያ ህዝብ!http://ecadforum.com/Amharic/archives/11040/

Saturday, February 15, 2014

የመኖሪያ ፈቃድ – ከራስ ወዳድነት ያልራቀው የስደተኞች የመጨረሻ ግብ

February 15, 2014

በሳዑዲ ለተፈናቀሉና ለተጎዱ ዜጎች የእንድረስ ምክክር በኦስሎ

ከራሳቸው አልፎ ባህር ውስጥ ቢደፉት የማይጎድል ሃብት አላቸው። ከሃብታቸው ብዛት የተነሳ ተጨማሪ የነዳጅ ክምችት አግኝተው ጉድጓድ ለመቆፈር ተቃውሞ በመነሳቱ ሪፈረደም አካሂደዋል። ከነዳጅ ይልቅ ውሃ ውስጥ ያለው ህይወት አንደሚብስባቸው በማስታወቅ ድምጽ የሰጡ በመብዛታቸው ነዳጁ ባለበት እንዲቆይ ተወስኗል። ይህ ዜና በተሰማበት ሰሞን ያልተገረመ አልነበረም። ሃብት ካለ ምን ችግር አለ? አንግዲህ እንደዚህ “ብር ይብቃን፤ አሳና የባህር ውስጥ ፍጡራን እንቁራሪትን ጨምሮ ይበልጡብናል” የተባለባት አገር ኖርዌይ ናት።
Ethiopians in Oslo, Norway for Saudi Arabia victims
በተቃራኒው ደግሞ ብር ካየ የሚገባበትን ጉድጓድ፣ የሚፈጽመውን ጥፋት የማይለካው ኢህአዴግ የሚመራት ኢትዮጵያ ያፈራቻቸው ስደተኞች ኖርዌይን ተጠልለዋል። ከአራት ሺህ በላይ ወገኖች ኖርዌይ በጡረታ መልክ እየቆረሰችላቸው ወይም ስራ እየሰሩ ህይወታቸውን ይመራሉ። በኖርዌይ መወልወያና መጥረጊያ ይዘው ቀን የሚገፉ “ራፐሮች”፣ አዛውንቶችን የሚንከባከቡ ሞግዚቶች፣ በከፍተኛ የትምህርት ተቋማትና የስራ እርከን የሚሰሩ ባለሙያዎች አንዲሁም በስደተኞች ካምፕ ተጠልለው የመኖሪያ ፈቃድ የሌላቸው ወገኖች በየዘርፉ በብዙ መልክ ተመድበው ይኖራሉ።
አብዛኞቹ የመኖሪያ ፈቃድ ባለቤቶች ከፖለቲካ ድርጅቶችና ከሲቪክ ማህበራት በተሰጣቸው የአገልግሎት የድጋፍ ደብዳቤና ክትትል ቢሆንም መልስ ካገኙ በኋላ ወገናቸውን መልሶ ከመርዳት የውሃ ሽታ ሆነው እንደሚቀሩ ይነገራል። “በኢትዮጵያ አምላክ ያዙኝ ልቀቁኝ” በማለት የትግል ችቦ ለኳሽ፣ አቀጣጣይ፣ መሪና አስተናባሪ መስለው የሚፈልጉትን እስኪያገኙ በርተው ስለሚጠፉ በድፍረት የሚነሳ ጉዳይ ባይሆንም አቶ ኦባንግ ሜቶ አምርረው የተናገሩበት ጉዳይ ነበር። እዚህ ላይ ሊሰመርበት የሚገባው ትልቅ ጉዳይ የመኖሪያ ፈቃድ በነበራቸውም ሆነ ባልነበራቸው ወቅት ወገኖቻቸውን፣ አገራቸውን እንዲሁም ቃል ኪዳናቸውን ሳይዘነጉ ባሉበት የዓላማ አለት ላይ ሆነው ስራቸውን የሚሰሩ ምርጦችም የመኖራቸው እውነት ይሆናል።
እንቁራሪትን ጨምሮ ለውሃ ውስጥ ነዋሪዎች በመቆረቆር እኛ ለዘመናት አልከፈትም ያለንን የነዳጅ ጉድጓድ በዘጋችው ኖርዌይ ውስጥ የስደት ማመልከቻቸው ተቀባይነት በማጣቱ እድሜያቸውን በካምፕ ውስጥ የሚያሳልፉ የሰው ልጆች ቁጥር ቀላል አይደለም። ከእጅ ወደ አፍ በሆነች የኪስ ገንዘብ ካምፕ ውስጥ ከሚኖሩትን ወገኖች መካካል ለስነልቦና ችግር የተጋለጡ፣ በችግር ምክንያት በቴዲ አፍሮ “ምን ይዤ ልመለስ…” ዘፈን እያለቀሱ ኑሯቸውን የሚገፉትን ወገኖች ጥቂት አይደሉም። እኒህን ወገኖች አሰባስቦ ለመርዳትም ሆነ ለማወያየት ቢችግርም፣ ችግሩ ሳውዲ እንደደረሰው አይነት ባይሆንም ቸል ሊባል የሚገባው አይሆንም። አቶ ኦባንግ ይህንን ጉዳይ ያነሱት “ራሳችንን አስቀድመን እናክብር” በሚል ነበር። እንደ እሳቸው አባባል ራስን የማክበርና ለራስ የመታመን ችግር የዛሬው የፖለቲካ ቀውስ ውጤትም ነው። ኢህአዴግ ራሳቸውን የማያከብሩትን በመሰብሰብ 22 ዓመት የገዛው ጠንካራ ሆኖ ሳይሆን ራሳቸውን ማክበር ያቃታቸውን በሆዳቸው በመደለል ነው። ዛሬም በስደት ምድር ራስን የማክበርና በነበሩበት ቦታ ያለመገኝት ተራ ብላጣ ብልጥነት አገር ቤት ካሉት ኦህዴድ፣ ብአዴን፣ ደህዴን … በተለየ ቦታ የሚያስቀምጥ አይሆንም።
ባለፈው ቅዳሜ ኦስሎ በተካሄደው ታላቅ ስብሰባ ዋናው ጉዳይ በሳዑዲ አረቢያ አገዛዝ አንጋቾችና አክራሪ ጽንፈኞች አማካይነት ዘግናኝ በደል ለተፈጸመባቸውና ለተፈናቀሉ ወገኖች የእርዳታ ገንዘብና ቁስ ማሰባሰብ ነበር። በዚሁ ስብሰባ ላይ ከኦነግና ከኦጋዴን ነጻ አውጪ ተወካዮች በስተቀር ሁሉም ተገኝተዋል። የተለያዩ የክርስትና ሃይማኖት ተቋማት፣ የእስልምና እምነት ተወካይ፣ የኢህአፓ፣ የኖርዌይ ድጋፍ ሰጪ ፎረም፣ የኖርዌይ የስደተኞች ማህበር፣ ተወካዮች በየተራ ንግግር አድርገዋል። ስብሰባውንና ሃሳቡን በማራመድ ግንባር ቀደሙን ሚና የተጫወተው የዝግጅቱ ባለቤት በኖርዌይ የኢትዮጵያ ስደተኞች ማህበር ሰብሳቢ አቶ ፋሲካ ባደረጉት ንግግር የተጀመረው ስብሰባ ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ዋና ዳይሬክትር አቶ ኦባንግ ሜቶ ነበሩ።
አቶ ፋሲካ የኖርዌይ ማህበረሰብ ዘወትር ለሚቀርብለት ጥያቄ አፋጣኝ መልስ እንደሚሰጥ በመጥቀስ አመስግነው የወቅቱን አሳሳቢ ሁኔታ በሚገባ አብራርተዋል። ስቅላት፣ አስገድዶ መድፈር፣ እስር፣ ግድያና ስቃይ እጣ ፈንታቸው ለሆኑት ወገኖች ድምጽ ከመሆን ጀምሮ የተለያዩ የአጋርነት መገለጫ ዝግጅቶች ላይ ማህበራቸው መገኘቱን ያመለከቱት አቶ ፋሲል “ድምጽ ለሌላቸው ድምጽ ከመሆን አልፈን በቁስና በገንዘብ ልንደጉም፣ አለን ልንል፣ አለንታነታችንን ለመግለጽ ስንነሳ ሰፊ ስራ ሰርተን ነው” በማለት በዕለቱ የተገኙትን የተለያዩ ተቋማት ወኪሎችን አወድሰዋል። የሚሰበሰበውንም ገንዝብ ለግሎባል አሊያንስ በማስረከብ እርዳታው ለወገኖች እንዲደርስ ሰፊ ውይይት መደረጉን ጠቁመዋል። ይሁን እንጂ ገንዘቡ የተለያዩ ተቋማትና ግለሰቦች በመሆኑ የገንዘቡን ባለቤቶች ውሳኔ የሚጠይቅ በመሆኑ ውሳኔውን አክብረው አፈጻጸሙን ተግባራዊ እንደሚያደርጉ በሚመሩት ማህበር ስም አመልክተዋል። በስብሳበው ላይ የተገኙት የፖለቲካ ድርጅቶች “ስለ ኢትዮጵያዊነት የሚያገባቸው ብቻ ናቸው” ሲሉም ገልጸዋል።
በይፋ ለመቋቋም አዲስ 22 ዓመት የፈጀበትና የዛሬ ሁለት ዓመት በይፋ የተመሰረተው የቃል ኪዳን ታቦት የፈውስ አገልግሎት አገልጋይና መሪ የሆኑት ወ/ሮ ሰዋሰው “ዓላማችን የታረዘን ማልበስ፣ የተጠማን ማጠጣት፣ የተራበን መመገብ፣ የታሰረን መጠየቅ በመሆኑ እንደ አንድ ኢትዮጵያዊ ምን ማድረግ ይገባኛል በማለት አስብ በነበረበት ጊዜ እንዲህ ያለው ስራ መሰራቱን ሰማሁ። አዲስ ከምንጀምር የተጀመረውን ለምን አንረዳም? በማለት መጣሁ” በማለት መልዕክታቸውን ጀመሩ። መጽሃፍ ቅዱስ እንደሚለው በማለት ወገኖችን ስለመርዳት ያስተማሩት ወ/ሮ ሰዋሰው፣ “ጌታ ኢየሱስ ሲመጣ ይህንን ያህል ጉባኤ ተሳትፌያለሁ። በብዙ ሱባኤ ተግኝቻለሁ … የሚል መልስ አያረካውም” ሲሉ መረዳዳት አስፈላጊ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል። በማያያዝም ዛሬ ቤተ ክርስቲያን ወገኖቿን ለመርዳት ስትነሳ፣ የፖለቲካ ተቋማት ወገኖቻቸውን ለመርዳት ሲነሱ እየተከታተሉ ማውገዝ አግባብ እንዳልሆነም አመልክተዋል።
ባለፉት 22 ዓመታት የክፋት መንፈስ አገራችንን እንደጎዳት ያመለከቱት ወ/ሮ ሰዋሰው፣ “የጻድቅ አይን ወደ ራሱ ይመለከታል” ተብሎ እንደተጻፈው አሁን ያለው ችግር ሲነጋ በእኛም ላይ መልኩን ቀይሮም ቢሆን ሊከሰት እንደሚችል አመልክተዋል። ሲጨርሱም “በሰው አገር ላይ ነን እኛም ላይ የሚደርሰው አይታወቅም። የቆመ የሚመስለው እንዳይወድቅ ይጠንቀቅ” በማለት ለቀረበላቸው አስፈላጊውን ሁሉ ለማድረግ ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል።
የቅዱስ ገብርኤልና አቡነ ተ/ሃይማኖት ቤተክርስቲያንን በመወከል የተናገሩት ወ/ሮ ሂሩት ወርቁ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ሁሌም ከልጆቿ ጋር ተለይታ እንደማታውቅ የቀደመው ታሪኳ እንደሚመሰክር አስምረውበታል። አሁንም በተመሳሳይ ይህንኑ በጎ ስራ እንደሚገፉበትና የርዳታው ማሰባበሰብ በቤተክርስቲያን ደረጃ እየተሰራ እንደሆነና የተሰበሰበውንም ገንዘብ በወቅቱ እንደሚያስረክቡ አመልክተዋል። በመጨረሻም ለዚህ በጎ ስራ የተሰማሩትንና ፈቃደኛ የሆኑትን በሙሉ በረከትን ተመኝተውላቸዋል።
ከኢትዮጵያ የ7ኛው ቀን አድቬንቲስት ቤ/ክ ህብረት የተወከሉት ዶ/ር ዙፋን አግደው በበኩላቸው ወገኖችን ለመርዳት በተጠራው ስብሰባ ላይ መገኘታቸው እንዳስደሰታቸው አመልክተዋል። በተለያዩ የበጎ ተግባራት ቤተ ክርስቲያናቸው ስትሳተፍ እንደቆየች ያወሱት ዶ/ር ዙፋን “ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሔር ታነሳለች በሚል እንደተጻፈው ጸሎታችን አንዲሰማ አንድ መሆን ያስፈልጋል” በማለት በህብረት የመሰባሰቡ ቁልፍ የልብ አንድነት መፍጠር ላይ እንደሆነ ገልጸዋል። “የእግዚአብሔር ቃል ሁለት ያለው ምንም ለሌለው እንዲሰጥ ያዛልና በርዳታው በኩል ነቅተን እንሳተፋለን” ሲሉ የወከሉትን ቤ/ክ አቋም አንጸባርቀዋል።
የኢህአፓ ተወካይ አቶ ምናሴ “ለዚህ ሁሉ አሳፋሪና አንገት የሚያስደፋ የወገኖቻችን ስቃይ ተጠያቂ ወያኔ ነው” ሲሉ የችግሩን ግዝፈት አመልክተዋል። የዲሞክራሲ ለውጥ ድጋፍ በኖርዌይ ተወካይ አቶ አቢ አማረ በተመሳሳይ የችግሩን አሳሳቢነትና አገር ቤት ስልጣንን በሃይል ያዘውን የኢህአዴግ አገዛዝ እጅ ለእጅ በመያያዝ መታገል በዋናነት አስፈላጊ መሆኑንን ጠቁመው በሳዑዲ አረቢያ ለተፈናቀሉ በሚደረገው ድጋፍ ላይ ድርጅታቸው የዘወትር ድጋፉን እንደሚገፋበት አረጋግጠዋል። በድርጅት ያልታቀፉ በድርጅት ጥላ ስር እንዲደራጁ ጥሪ አቅርበዋል። የኢትዮጵያ ስደተኞች ማህበር ተወካይ አቶ ሃምሳሉ በበኩላቸው ተመሳሳይ የትብብር ማረጋገጫ ሰጥተዋል።
የኢትዮጵያ የጋራ መድረክ ፎረም በኖርዌይን በመወከል ወ/ሮ ዙፋን አማረ ሲናገሩ “አንዳንዴ  ምነው በአባቶቼና በአያቶቼ ዘመን ምነው በተፈጠርኩ እላለሁ” በማለት የቀድሞው ዘመን ኢትዮጵያዊነትን ከአሁኑ ዘመን አንገት አስደፊው ማንነታችን ጋር አዛምደው ተናግረዋል። ይህ ትውልድ እጣው ውርደት እንደሆነ ያመለከቱት ወ/ሮ ዙፋን፣ ከዚህ ውድቀትና ሃፍረት ላይ ከጣለን ስርዓት እስከወዲያኛው ነጻ ለመውጣት እሳቸው ወከሉት ድርጅት እየሰራ መሀኑንና የሁሉም ህብረት አስፈላጊ መሆኑንን አስታውሰዋል።
“የቁርጥ ቀን ልጅ፤ የኢትዮጵያ እውነተኛ ልጅ፣ ንጹህ ኢትዮጵያዊ፣ ኢትዮጵያዊያን በተቸገሩበት ቦታ ሁሉ ቀድሞ የሚደርስ፣ …”፤ “የጥቁሩ ሰው” ስም ኦባንግ ሜቶ ተባለ። ኦባንግ ተነሱ። አስቀድመው ንግግር አድርገው የነበሩትን ሴት እህቶች “አከብራለሁ” አሉ። በመቀጠል በሳዑዲ ወገኖቻችን ላይ የደረሰውን ጉዳይ አስረዱ። በመቀጠልም ንግግራቸውን ወደ ስደተኛው አዞሩት “ፎቶ ከኔ ጋር ትነሳላችሁ፤ መልስ ስታገኙና የመኖሪያ ፈቃድ ስታገኙ አትታዩም፤ ትጠፋላችሁ” በማለት ፊት ለፊት ወቀሳቸውን ሰነዘሩ። በመሪነትና አቅጣጫን በሚያመላክት ሞገስ አጽንኦት ሰጥተው የተናገሩት አቶ ኦባንግ “ድክመት አለባችሁ” ብለዋል።
በኖርዌይ የመኖሪያ ፈቃድ ተከልክለው በስደት ካምፕ ውስጥ ያሉት ወገኖች በምን ደረጃ እንዳሉ አስታወቁ። የአእምሮ፣ የስነልቦናና የኢኮኖሚ ችግር እየተፈራረቀባቸው ዓመታት አንድ ቦታ ተቀምጠው መኖራቸው “እንዴት እረፍት ይሰጣል” ሲሉም ጠየቁ። “እናንተ ትናንት በተመሳሳይ ችግር ላይ የነበራችሁ፤ ዛሬ ወረቀት ስላገኛችሁ የቀድሞውን ማንነታችሁን ረሳችሁ” ሲሉ ሲሳካላቸው የሚሸሹትንና ወገኖቻቸውን የሚዘነጉትን አወገዙ። ከአጠቃላይ የወቅቱ ችግር ጋር በማያያዝ ‘ሰዎች ንን ራሳችንን እናክብር። አሁን የሚታዩት ችግሮች በሙሉ ራስን የማክበር ችግር ነው። እባካችሁን ራሳችሁን አክብሩ” ሲሉ መከሩ።
“ወያኔዎች ስራቸውን ያወቃሉ። እኛ ግን ስራችንን አናውቅም። በረሃ ሲገቡ ትግራይን ነጻ ለማውጣት ነበር ። እኔንና እናንተን የሚመስሉት ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ራሳቸውን ማክበር ባለመቻላቸው ለትንሽ ዳቦ ጫካ ውስጥ የገቡት ወያኔዎች ትልቁን ዳቦ አገኙት” ሲሉ ከላይ ያነሱትን ሃሳብ አብራሩ። በስደት ኖርዌይ ከመጡ በኋላ ኦስሎን አንኳ የማያውቁ ወገኖችን ጉዳይ ደጋግመው ያነሱት አቶ ኦባንግ “እኔ ብለን ስንጀምር ነገር ይበላሻልና እኛ ብለን እንጀምር” ሲሉ ስለ ብሔር መከፋፈል ጣጣ መልዕክት ሰጥተዋል።
“አዲሲቷን ኢትዮጵያ ስንገነባ ሁሉን አስረን አንችልም። ዓለማችንም አይደለም” ያሉት ጥቁሩ ሰው፣ የስደት ምድር ጊዚያዊ ማረፊያ እንጂ የዘላለም አገር አይደለምና የራሳችን አገር ባለቤት ለመሆን በውስጣችን ያለውን ተንኮል እናስወግድ ብለዋል። በነጻነት እቅዳችን ውስጥ የሚበድሉንን ጨምሮ ሁሉንም ነጻ የማውጣት ስራ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት እየተሰራ መሆኑንን ያወሱት ኦባንግ ሜቶ “በሳዑዲ የሌሎች አገራት ዜጎች መንግሥታቸው ሲሰበስባቸው የእኛ ዜጎች ግን እንደ ቅያሪ ጎማ በሌላ ይተካሉ በሚል ወገንና አገር አልባ እንደሆኑ ተቆጥረዋል። ከዚህ በላይ የከፋ ውርደት የለምና አሁንም በድጋሚ የምነግራችሁ ራሳችሁን በማክበር ለወገናችሁ ምላሽ ስጡ” በማለት የፊልም ምሳሌ በመስጠት ንግግራቸውን አጠቃለዋል።
“ይህ ፊልም የወኖቻችን ስቃይ የተቀረጸበት ነው። ፊልሙ ብርሃን የያዘውን ምስል ለመመልከት ብርሃን ይፈልጋል። ፊልሙ ብርሃን ካላገኘ ምስሉ ሊታይ አይችልም። ብርሃን ከላገኘ በጨለማ ውስጥ እንዳለ ይቀራል። እናንተም በጭለማ ውስጥ ላሉት ወገኖቻችሁ ብርሃን መሆን አለባችሁ። አገራችን ብርሃን የሚሆኑላት ትፈልጋለችና!!” አቶ ኦባንግ የስደተኞችን ጉዳይ በመያዝ አግባብ ካላቸው የኖርዌይ ባለስልጣናት ጋር ተነጋግረዋል። አቶ ኦባንግ በሚቀጥለው ወር ከኖርዌይ ጠቅላይ ሚኒስትር በቀረበላቸው የውይይት ጥያቄ መነሻነት ወደ ኖርዌይ ተመልሰው ይመጣሉ ። አቶ ኦባንግ ባለፉት ስድስት ወራት በድርጅታቸው አማካይነት ስለሰሩት ስራና አጠቃላይ እንቅስቃሴ አስመልክቶ ከጎልጉል ጋር ሰፊ ቃለ ምልልስ እንደሚያደርጉ ቃል በመግባት የሚከተለውን ተናግረዋል። “አሁን ነገሮች መልክ የያዙበት ወቅት ላይ እየተቃረብን ነው። ዜጎች ራሳችሁን በማክበርና ከክፋት ልቡናቸውን በማጽዳት ይደግፉን። የተቀረውን እኛ እንሰራዋለን፡፡”http://ecadforum.com/Amharic/archives/11003/

Friday, February 14, 2014

የጤፍ ምርትን ለውጭ ገበያ፣ ይቁም ሊባል የሚገባ!

ሰሞኑን ስለጤፍ ምርታችን የባዕዳኑ ብዙሃን መገናኛ አጀብ እያሉን ነው፤ ለዘመናት የተደበቀው የዘሩ ገመና መጋለጡን እየነገሩን ነው፤ ስለያዘው ንጥረ ነገር፣ ስለጤናማነቱ፣ በምዕራቡ ገበያ ስለመፈለጉ፣ ከሁለም በላይ ስለ ውጭ ምንዛሪ ምንጭነቱ። ምግብነቱ ተትረፍርፎ የኢትዮጵያ ህዝብ ማስቀመጫ – ቦታ ያጣ ይመስል፣ የወንዙ ልጆች ጭምር ፣ ጤፍ-የጤፍ ዘር፣ እንጀራ ፣ ብሰኩት፣ ኬክ ሆኖ ምግብ በዝቶበት ለሚቀናጣው ለውጭ ገበያ እንዲነጉድ ከምዕራባውያኑ ጋር አብረን ከበሮ እየደለቅን ነው፤ አደብ ልንገዛ ይገባል።
Ethiopian unique grain Teff
ባለሙያዎቹ ወቅታዊና በቂ መረጃ እሰካላስጨበጡን ድረስ፣ በዚህ ፁሁፍ አቅራቢ ዕምነት፣ ምርታማነቱ ባለህበት እርገጥ የሆነውንና – በደሃው ገበሬ ማሳ ዛሬም ሆነ የዛሬ 100 ዓመት በሄክታር ከዘጠኝ ኩንታል ያልዘለለውን ፣ ተገቢ የምርምርና ጥናት እገዛ በዙሪያዉ ያላንዣበበውን ይህን ብቸኛ የኢትዮጵያ ልጅ – ጤፍ ፣ አሁን ባለበት ደረጃ ለዉጭ ገበያ በውጭ ምንዛሪ ምንጭነት በሰፊው ለማቅረብ የተያዘው እንቅስቃሴ የምርቱንም ሆነ የህብረተስቡን የኑሮ ዕውነታ ያላገናዝበ ፣ከፈረሱ ኮርቻው ዓይነት ነው። በምርቱ ህልውናና በሸማቹ የዕለት ተዕለት ኑሮ ላይ ያልተፈለገ ጦርነት ክተት የማለት ያህል ነው። በመንግስት በኩል ቆም ተብሎ እነደገና ሊፈተሽ የሚገባ አብይ ብሔራዊ ጉዳይ ነው።
ጤፋችን በመሰረቱ የማንነታችን መግለጫ፣ ረሃብን ተዋጊ – ብሄራዊ ጦራችን ነው፤ ድንበር አስከባሪያችን ነዉ። “የዕለት እንጀራችንን አታሳጣን” እያልን ለፈጣሪ ቢያንስ በቀን አንዴ፣ ከሆነልንም ሶስቴ የምንጸልይለት የጤናችን ምሰሶ ነው፤ ከሚያመጣው ዶላር ይልቅ የሚያስታግሰው የሚሊዮን ረሃብተኛ ሆድ ሚዛን የደፋ ነው፤ በየሶስትና አራት ዓመቱ አንገት አስደፊና ብሄራዊ ውርደት የሆነውን የልመና እጅ ከመዘርጋት የሚያድን ነው። ለእኛ ለዜጎቿ ምርቱ ከቡናና ከወርቃችንም በላይ ነው፤የሱስ ማርኪያ ወይም ሠርግና በዓል እየተጠበቀ ብቅ የሚል ማጌጫ አይደለም፤ ሳይተርፈን ቡናና ወርቅ ለውጭ ገበያ ብንልክ በሕብረተሰባችን ማህበራዊ ህይወት ውስጥ የሚያመጣው ቀውስ የለም፣የሚበጅ እንጂ። ሳይተርፈን የጤፍ ዘርን በጥሬውም ሆነ በእንጀራ ለውጭ ገበያ መስደድ ግን ሀገራዊ ጥቃት ነው። እኛነታችንን ሳያስከብር ከሀገር እንዳይወጣ፣ ለባዕዳን ሲሳያ እንዳይሆን በያለንበት ዘብ ልንቆምለት ያስፈልጋል፤ የመስኩ ባለሙያዎች ከምርምር ጣቢያችው ወደ ህብረተስቡ መድረክ ወጣ ብለው ስለ ጤፍ ልዩ ባህርይ፣ ኢትዮጵያዊነት፣ ሊነግሩንና ጥብቅና ሊቆሙ ይገባል፤ የጤፍ ምርት ያለበትን የምርታማነት ደረጃ ሊተነትኑልን ፣ ለውጭ ምንዛሪ የመዋልን ብሄራዊ ጠቀሜታና ጉዳት ግንዛቤ ሊያስጨብጡን ያሻል፤ብሄራዊ ጉዳቱ ከመድረሱ በፊት ከመከላከሉ ላይ ኢትዮጵያዊ ሃይላችንን ማሳረፉ ላለውና ለመጪው ትውልድ ባለውለታ ያደርገናል።
በመሰረቱ ፣ የጤፍ ዘርን ህለውና የተፈታተነ የክተት ጥሪ ሲደረግ ይህ የመጀመሪያው አይደለም፤ በደርግ ዘመነ መንግስት የገበሬው የጤፍ ማሳ ምርታማነታቸው ከፍ ባሉ አዝዕርቶች እንዲተካ የሚያደርግና በመንግስት የተደገፈ “ጥናት” ቀርቦ ለአፈጻጸሙ በተወሰኑ የሀገሪቱ ክልሎች ሸብ-ረብ ተብሎ ነበር። ጥናቱ ምርታማዎቹ በቆሎ፣ ስነዴና ድንች ምርታማ ያልሆነውን የጤፍ ዘር ቢተኩ፣ የሀገሪቱን ዓመታዊ የምርት እጥርት ከመሸፈን አለፈው ለመጪው አመት የሚሻገር ምርት ለማከመቸት እንደሚቻል ያስረገጠ ነበር። ተግባራዊነቱ ከአንድ ዓመት አልተሻገረም። በይዘቱ ከዛሬው ጥሪ ቢለይም በገበሬው ኑሮና በጤፍ ህልውና ላይ ጥሎት የነበረው አደጋ ተመሳሳይ ተፅእኖ ነበረው። ውሳኔውንም ሆነ አፈጻፀሙን የተቃወሙ ጥቂት ወገኖች ነበሩ፤ መድረኩም ወቅቱም ባለመፍቀዱ አልተደመጡም። ውሳኔው ከማዕከል ወጥቶ ወደ ገጠሩ – ከገበሬው ማሳ አመራ፤ ገበሬው ጤፉን ወደ ጓዳው መልሶ፣ እንደታዘዘው ማሳውን በምርታማዎቹ በቆሎና ድንች አርመሰመሰው። መሰብሰብ ከሚችለው በላይ ማረስ ልምዱም ባህሉም ያልነበረው ገበሬ አቅሙና ጎተራው የሚችለውን ያህል ሰብስቦ የቀረውን ከማሳው ላይ ተወው፤ ወድሞ ቀረ። በጎተራ ያከማቸው ስንዴም በነቀዝ ተጠቃ፤ በቆሎና ድንች የከተሜውን ገበያ ቢያጥለቀልቀውም ዋጋው በመውደቁ ገበሬውን ከኪሳራ ዳረገው፤በአርሲና ባሌ በሰፊው የታረሰው የመንግስት እርሻ ምርትም ለተመሳሳይ አደጋ ተጋለጠ፤ አቅምን ያላገናዘበ ውሳኔ፣ በበቂ ጊዜ፣ ገንዘብ ባለሙያ ያልተደገፈ ምርትና ምርታማነትን የማሳደጉ ዘመቻ አባዜ፣ ለሌላ አስከፊ ችግር ገበሬውንም፣ ሸማቹንም መንግስትንም ጭምር አጋልጦ አለፈ።
ከስህተት ያለመማር ባህል የተፀናወታቸው ገዥዎቻችን በመጪው የዕቅድ አመትም መሰረታዊ ችግሩን ባልፈታና ስሙን ብቻ በቀየረ እቅድ እንዲቀጥል ተቃጥቶ ነበር፤ በዚህ ጊዜ ጥቂት ቆራጥ የሆኑ የጤፍ ምርት ተመራማሪዎች ድምጸ-አልባ የነበረውን የገበሬውን ድምጽ ከፍ አርገው በማስተጋባታቸውና በቁጥር ከሁለት ያልበለጡ የጊዜው ባለስልጣናትን ግንዛቤ ሊያገኙ በመቻላቸው፣ ከገበሬው ጉያ ተደብቆ የሰነበተው የጤፍ ዘር በግላጭ ወጥቶ ከማሳው ሊመለስ በቃ። ዛሬ ኢትዮጵያናችን እነዚያን የመሰሉ ለገንዘብና ለግል ስልጣን ያላደሩ ተመራማሪዎቿንና የመንግስት ሃላፊዎቿን በባትሪ የምትፈልግበት ወቅት ላይ ነች። አሁን በምን ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ የዚህ ፁሁፍ አቅራቢ ለማረጋገጥ መረጃ ባይኖረውም፣ በዚያን ወቅት በጤፍ ዘርና ምርታማነት ጥናትና ምርምር ዙሪያ ከተሰለፉት ሳይንቲስቶቻችን መሀከል እነ ዶ/ር ሰይፉ ከተማና ባልደረቦቻቸው ለአብነት የሚጠቀሱ የሀገሪቱ ባለውለታ ናቸው። ዶ/ር ሰይፉ የጤፍ ዘር ለዘመናት አላነዳች የቴክኖሎጂና የመንግስት ድጋፍ የመቆየት ሚስጥርን አበክሮ የሚገልጽ የምርምር ስራ (Tef ፤ Eragrostis tef , 1993) ለተነባቢነት አብቅተዋል፤ በዚያ ጥናታዊ ስራቸው ገበሬዉን ጭምር እማኝ በማድረግ እንደነገሩን፣ የጤፍ ዘር ከማንኛውም ምርት በተሻለ ድርቅንም ሆነ ከባድ ዝናብን የመቋቋም ልዩ ባህርይ የገበሬውን ቀልብ የሳበ ነው።
ጤፍ በምግብነቱ እንዲህ እንደዛሬው የሀብታሙ አልነበረም፤ ደሀው ችግር ሲጋፈጠው እየደበቀ፣ እየቆጠበ የሚበላው ሳር ነበረ። የዘሩን ዘርፈ-ብዙ ጠቀሜታ ደሀውም ሀብታሙም ገበሬ በእጅጉ ከተረዱት በሗላ ከትውልድ ትውልድ እየተቀባበሉት እዚህ ለመድረስ በቅቷል። በተዘራበት ማሳ እንደ ስንዴና በቆሎ በዝናም እጥረትም ሆነ ብዛት ወድሞ አይቀርም፤ ገበሬውን አመድ አፋሽ አያደርግም፤ የጠበቀውን ያህል ባያገኝም ለዘር ያህል አያሳጣውም። በጎተራ ሲከማች እንደተቀሩት ምርቶች በነቀዝ አይደፈርም፣ ጭዱ የእንስሳቱ ተወዳጅ ምግብ፣ የጎጆው ግድግዳ ማገር መመረጊያ ነው። በገቢ ምንጭነቱም አንጀት አራሽ ነው። የጤፍ ዘር የሸማቹም ልዩ ወዳጅ ነው፤ በረከት ያለው እህል ነው፤ ግማሽ ኩንታል ጤፍ ከወፍጮ ቤት ወስዶ ሙሉ ኩንታል ዱቄት ተሸክሞ የሚመለስበት ነው፤ ለዚህም ነው ሸማቹ የዋጋ ውድነቱን አጠብቆ የሚያማርር። በምግብነቱም ቢሆን ተወዳጅና ሁለገብ ነው፤ ችግር ከመጣ አለማባያ፣ አለዚያም በወተት ተምጎ ፣ በሚጥምጣ ተረምዶ ይበላል። ማባያዎቹ ሳይደመሩ የጤፍ ዘር በራሱ አይነታቸውና መጠናቸው የተለያዩ በርካታ ለሰውነታችን ጤና ግንባታ የሚረዱ ንጥረነገሮችን(ፕሮቲን፣ አይረን፣ ካልስየም፤ ፋይበር እና የተለያዩ ቫይታሚኖችን) አዝሎ የሚገኝ ነው። ዜናው ከምዕራቡ ዓለም የወሬ ማሰራጫ ጣቢያ ካልመጣ ጆሯችን አልሰማ ብሎ እንጂ፣ አዲስ አይደለም። የደብረዘይቱ የግብርና ምርምር ሳይንቲስቶቻችን የዛሬ 25 ዓመት አስረግጠው ነግረውን ነበር። ኢትዮጵያውያኑ ተመራማሪዎች ይህን የጤፍ ዘር ባላቸው ውስን አቅም ምርታማ ለማደረግ ጥረታቸው የመቀጠሉ ተቀዳሚ ምክንያት ለምዕራባውያን የጤፍ ብስኩትና ትኩስ እንጀራ ለመሸጥ አልነበረም፤ አይደለመም። ዋና ግባቸው በሚሊዮን የሚቆጠረው የሀገሪቱ ጤፍ አምራች ገበሬ ለዘመናት ከያዘው አድካሚ አሰራር ተላቆና የዘመናዊ ቴክኖሎጂ ተጠቃሚ ሆኖ ምርቱን በስፋትና በተመጣጣኝ ዋጋ ለበላተኛው እንዲያቀርብ ማስቻል ነው። በሀገር ውስጥ ምርቱን የማስተዋወቅ ስራ ሳይሆን፣ ምርቱ የያዘው ንጥረ-ነገር ምን ያህል ለጤናችን አስፈላጊ እንደሆነ አግባብ በላቸው ተቋማት በኩል ለህብረተሰቡ ግንዛቤ መስጠት ነው።
በጥናታዊ ጹሁፋቸው፣ የጤፍ ተመራማሪው ዶ/ር ሰይፉ እንደሚነግሩን፣ በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ በጤፍ ምርቱ ላይ ያተኮረ ሳይንሳዊ ምርምር የተጀመረው እንደ አውሮጳ አቆጣጠር በ 1950 ዎቹ መጨረሻ ግድም ሲሆን፣ የመጀማሪያው ኢትዮጵያዊው የጤፍ ሳይንቲስት ዶ/ር መላክ-ሃይለ መንገሻ ይባላሉ። እኒህ ሙሁር ስለጤፍ ዘር ባህሪ ጥናትና ምርምር ከማድረግ ጀምሮ በግብርና ኮሌጆችና የእርሻ ምርምር ጣቢያዎች ተገቢውን ትኩረት አግኝቶ ምርምሩ እንዲቀጥል በማድረግ ከፍተኛ አስተዋፅኦ አድርገዋል። በመቀጠለም ሌላው ሳይንቲስት ዶ/ር ታረቀ በርሄ የተሰኙ በጤፍ ምርት ምርምር ሂደት ግኝቱ እጅግ አስቸጋሪ የሆነውንና በምርታማነቱ ልዩ ሚና የሚጫወተውን የጤፍ ባህርይ (The Pollination Habit of Tef) ግኝት በተጨባጭ በማሳየት በሙያ አጋሮቻቸው አድናቆትን ያተረፉ የመስኩ ባልደረባ ናቸው። በእነዚህ ግኝቶች ላይ በመንተራሰ ዶ/ር ሰይፉና ባልደረቦቻቸው በደብረዘይት የግብርና ምርምር ማዕከል በጀመሩት የናሙና እርሻ፣ በሄክታር 8 እና 9 ኩንታል ላይ የቆመው የጤፍ ምርት ከ 20 ኩንታል በላይ ለማምረት የሚቻልበት ሁኔታ እንዳለ ሊያስመዘግቡ በቅተዋል። ይህ ድንቅና ተስፋ ፈንጣቂ ውጤት፣ ዛሬ ስለደረሰበት ሁኔታ ወቅታዊ መረጃ ለማግኘት የዚህ ፁሁፍ አቅራቢ ምቹ ሁኔታ ባይኖረውም ፣ ከተጨባጩ የሀገሪቱ ሁኔታ መገንዘብ እንደሚቻለው የምርታማንቱ ማነቆ አሁንም ድረስ እነዳልተፈታ ነው፤ በአብዛኛው ገበሬ ማሳ ላይ የጤፍ ምርትና ምርታማነት ባለህበት እርገጥ ላይ ነው። በየክልሉ በደብቅና በገሀድ የረሀብ አለንጋ እየተቀጣ ያለው ህብረተሰብም በእማኝነቱ የሚያወለዳ አይደለም።
በሌላ በኩል – የተለያዩ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት – የጤፍ ምርት ከሀገር ውጭም በአሜሪካ፣በካናዳ፣ በአውሮጳ፣ በአውስትራሊያና በአፍሪካም ጭምር ለማብቀል ጥረቱ ተይዟል፤ በኢትዮጵያ አየርና አፈር የሚበቅለውን የጤፍ ዘር ሊተካ ባይችልም፣ ለጤፍ ምርታችን የሚበጁ ሁለት እገዛዎችን ለማድረግ ዕደሉ የሰፋ ነው። የመጀመሪያው፣ የጤፍን ምርታማነት ለማሳደግ ከበቃ፣ ለግብርናቸው የተጠቀሙበትን ቴክኖሎጂ በጥንቃቄ አጢኖ ለሀገራችን ጤፍ ምርታማነት በአጋዥነት ለማሰለፍ መቻሉ ነው። ሁለተኛው፣ የሀገሪቱን የምግብ ፍላጎት ሳያሟላ፣ ባልተመጣጠነ ዋጋ ከደሃው ገበሬ ተዘርፎና ከበላተኛው አፍ ተነጠቆ ወደ ውጭ በቀላሉ እየወጣ ያለውን ጤፍ ጊዚያዊ እፎይታ ለማሰጠት አቅሙ መኖሩ ነው። በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የጥቂት ባለጊዜ ባለስልጣናትንና ነጋዴዎችን ኪስ ከመሙላት ባለፈ ብሔራዊ ፋይዳ እነደሌለው በይፋ የሚነገረለት ይህ የሀገሪቱ ጤፍ፣ ለውጭ ገበያ እንዳይውል ጥሪ የመደረጉ አንዱም መልዕክት የሀገር ቤቱን ጤፍ ለሃገር ፤የውጭውን ለውጭ የሚል ነው። በዋና ዋና ያሜሪካ ከተሞች ነዋሪ የሆኑ ትውልደ ኢትዮጵያውያንና ወዳጆቻቸው ከሀገር ቤት በኢትዮጵያ አየር መንገድ ጭምር ተጭኖ የሚመጣውን ትኩስ እንጀራና ጥሬ ጤፍ ሸማቹ እንዳይገዛ ድምጻቸውን እያሰሙ ነው፤ በተሳታፊ ነጋዼዎችም ላይ ማዕቀብ እንዲጣል ግፊት እያደረጉ ነው፤ ምላሹ ግን አጥጋቢ ሆኖ አይታይም። ምዕራባውያኑ ጤፍን እንደ ጣሊያኑ ፒሳ እስከሚለምዱት ድረስ እኛ በውጭው አለም ነዋሪ የሆንን ዜጎቿ የፈረጠመ ክንድ አለን፤ ከደሀው አፍ ተነጥቆ ማዕዳችንን እያጣበበ ያለውን የኢትዮጵያ እንጀራ – የጤፍ ዘር – ለማስቆም ትግሉን መቀላቀል ይጠበቅብናል፤ የይቁም ጥሪውም ቅዱስ ጥሪ በመሆኑ፤ ከጎናቸው ልንቆም ያስፈልጋል።
ጤናማውን ኦርጋኒክ ጤፍ ወደ ባዕድ ሃገር ሰደን በኬሚካል ያበደውንና ለበሽታ መራቢያነት ምቹ የሆነውን የባዕድ እህል ወደ ሀገር ከማስገባት ፣ ወይም የጤፍን ኦርጋኒካዊ ይዘት ለሚያቃውሱ ባዕዳን ነጋዴዎችና ሳይንቲስቶቻቸው አጋልጠን ከመስጠት፤ ልንድን የምንችለው፣ ዜጎቿ በአንድ ሆነን ለምርቱ ደህንነትና ምርታማነት ዘብ ስንቆም ብቻ ነው።ሀገሪቱ ወጣት የጤፍ ሳይንቲስቶች በጥራትና በብዛት እንድታፈራ ፣ የምርምርና ጥናት ዘርፉ ሀገራዊና አለም ዓቀፋዊ ትኩረት እንዲያገኝና፤ በቂ የመዋዕለ ነዋይ ፈሰስ ለዘርፉ እንዲደረግለት የሚደረጉ ተከታታይ ጥረቶች ለጤፍ ምርታችን አይነተኛ ለውጥ መምጣት መሠረት የሚጥሉ ብቻ ሳይሆኑ፣ ኢትዮጵያ እንደ ሀገር አንገቷን ቀና አድርጋ እንድትሄድ የሚያስቸላት ነው። ይህን ለመሆን ካበቃን፣ ከክረሰቶስ ልደት በፊት ጀምሮ የገበሬው ችግር ደራሽና አለኝታ ሆኖ እዛሬ ድረስ እስተንፋሱ የቆየው የጤፍ ዘራችን፣ ምርታማነቱ ከፍ ብሎና ከጥቂቶች ማዕድ ወጥቶ በተመጣጣኝ ዋጋ በሚሊዮን ህዘብ ማዕድ በመደበኛም ሆነ በአማራጭ ምግብነት የምናስተናግድበት ይሆናል። ከተጠነከረም፣ ሀገሪቱ ለጤፍ ምርት በሚውል መጠነ-ሰፊ መሬት የታደለች በመሆኗ፤ ዛሬ ከኢትዮጵያ አይውጣ እያልን የምንጮህለት ጤፍ – ያኔ ለውጭ ገበያ ጭምር በመዋል- ቡናና ወርቃችን ተደምረው ከሚያገቡት የውጭ ምንዛሪ በተሻለ ገቢ አስገኚና የሀገሪቱ የልማት ገንቢ ሆኖ እንደሚቀጠል ተስፋችን በእጅጉ የፀና ነው።http://ecadforum.com/Amharic/archives/10987/

Thursday, February 13, 2014

መንታ መንገድ – የኢህአዴግና የአሜሪካ ወዳጅነት ወዴት?

ቻይና ኢህአዴግን ትታደጋለች? ወይስ ኢህአዴግ ይታዘዛል?
eprdf china usa

አሜሪካኖች ነጻ እንድታወጡን አንጠይቃችሁም። የኢትዮጵያ ህዝብ እንዴት ነጻ እንደሚወጣ ያውቃል። እናንተግን በነጻነት መንገዱን ላይ ዕንቅፋት አትሁኑበት ዶናልድ ያማሞቶ                                         ከዛሬ ስምንት ዓመት በፊት ኢትዮጵያበመንታ መንገድ ላይ ነች ብለኸን ነበር መቼ ነው መንገዱን የምናቋርጠውከመንገዱ ላይ ገለል በሉልን” አቶኦባንግ ሜቶ
እንዴት እዚህ ተደረሰ?
የኢህአዴግን የአገዛዝ ዘመን ተቃዋሚዎችን አጃቢ አድርጎ የህግ ሽፋን በመስጠት የሚያራዝመው ዋና ተቋም ምርጫ ቦርድ፣ የፕሬስ ነጻነት፣ የመናገርና የመሰብሰብ ነጻነት፣ የህግ የበላይነት፣ ሕግን የማክበርና የማስከበር ሃላፊነት፤ ወዘተ በኢትዮጵያ ነጻ ከሆኑ ኢህአዴግ ከፊትለፊቱ ካለው ምርጫ የመዝለል አቅም እንደሌለው ይታመናል። ስለዚህም እነዚህን ጉዳዮች ለድርድር አያቀርባቸውም። ኢህአዴግ ከጅምሩ በህዝብ የማይታመነውና እውቅና የሚነፈገው ራሱን በነጻ አውጪ ስም (ህወሃት) የሰየመ መንግስት ስለሆነ ነው። ነጻ አውጪ እየተባለ አገር መምራቱም አቅዶ፤ ተልሞና መድረሻውን አስልቶ የሚጓዝ ስለመሆኑ ያሳብቅበታል። ለዚህም ይመስላል ስርዓቱ በሙስና የሸተተ፣ በግፍ የገለማ፣ የሚመራውን ህዝብ የሚገል፣ የሚያስር፣ የሚያሰቃ፣ መንግስት ሆኖ የሚሰርቅ፣ ብሔራዊ ክብርን የሚጠላ፣ ህብረትንና አንድነትን የሚጠየፍ፣ ጎሳና ጠባብ አመለካከት ላይ የተቀረጸ፣ በተራና በወረደ ተግባሩ ለመንግስትነት የማይመጥን መሆኑን የተረዱት አጋሮቹ አሁን ያመረሩበት ደረጃ ስለመዳረሳቸው ምልክቶች እንዳሉ አቶ ኦባንግ ሜቶ ለጎልጉል ተናግረው ነበር።
ኢህአዴግ ከአሜሪካ ጋር የመሰረተው ግንኙነት ከቶውንም ንፋስ እንደማይገባው ተከታዮቹ ሙሉ በሙሉ ያምናሉ። በተለይም የህወሃት ሰዎች አሜሪካ ከህወሃት ጋር ያሰረችው ቀለበት የሚወይብ አይመስላቸውም። የአሜሪካና የ”ህወሃት ፍቅር” ትምክህት የሆነባቸው የአሜሪካን ባለስልጣናት ህወሃት ኢትዮጵያን እስከ ዘላለም እንዲመራ ልዩ ቅባት እንደቀቡት የሚናገሩም አሉ። አሜሪካ ለህወሃት/ኢህአዴግ የምትሰጠው ጭፍን ድጋፍ ሊጤን እንደሚገባው በማሳሰብ ተስፋ ሳይቆርጡ የታገሉና የሚታገሉ ደግሞ ይህ ትምክህት አንድ ቀን እንደሚተነፍስ በእምነት ሲናገሩ ቆይተዋል።
ኦባንግ ሜቶ
ኦባንግ ሜቶ
ኢህአዴግን በዲፕሎማሲና በሰከነ የትግል ስልት መታገል ይበልጥ አዋጪ እንደሆነ ከሚያምኑት ወገኖች መካከል አቶ ኦባንግ ሜቶ ቅድሚያውን ይይዛሉ። አቶ ኦባንግ የሚመሩት ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ (አኢጋን) የሚያራምደውን እምነት አስመልክቶ “ከወረቀትና ፒቴሽን ከማስፈረም ያልዘለለ” በማለት የሚቃወሙና የሚተቹ የመኖራቸውን ያህል ልብና ቀልብ ሰብስበው የሚከተሏቸው ወገኖች ቁጥር ከቀን ቀን እየጨመረ ነው። እምነትም እየተጣለባቸው ነው።
በወገኖቻቸው ብቻ ሳይሆን በውጪው ዓለም ያላቸው ተቀባይነት፣ ብሎም አመኔታ እንዲሁ ከፍተኛ ነው። የኢትዮጵያ ወኪል ተደርገው እየተወሰዱም ነው። አቶ ኦባንግ ኢትዮጵያን በመወከል በተለያዩ ታላላቅ መድረኮች ሲሳተፉ የሚያቀርቧቸው ንግግሮችም ቀልብ የሚገዙና መልዕክታቸው የሰፋ በመሆኑ ሰፊ አድማጭ አላቸው። ሰሞኑንን በአሜሪካ ምክርቤት (ኮንግረስ) የጸደቀውን ድንገተኛ ውሳኔ አስመልከቶ “ኢህአዴግ ሳይወድ በግዱ በሩን በርግዶ ይከፍታል” ባይ ናቸው። ውሳኔውንና የውሳኔውን አካሄድ ከአነሳሱ ጀምሮ ጠንቅቀው እንደሚያውቁት ያመለከቱት አቶ ኦባንግ “አሜሪካ እዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰችው እንዲሁ ከመሬት ተነስታ ሳይሆን በከፍተኛ ትግል ነው። ትግሉ ተጠናክሮ ይቀጥላል የአውሮፓ አገሮችም የአሜሪካን ፈለግ እንዲከተሉ ሥራችንን አጠናክረን ጀምረናል” ብለዋል።
አዲሱ ውሳኔ ሕግ እና የኢህአዴግ ህልውና!
እያነጋገረ ያለው የእርዳታን አጠቃቀም አስመልክቶ ጥር 31 ቀን 2014 በአሜሪካን ኮንግረስ የፀደቀው አዲስ ውሳኔ ሕግ ነው። ውሳኔው አሜሪካ የምትሰጠው ርዳታ በትክክል ህዝብን ሳይጎዳ በስራ ላይ መዋሉንና አለመዋሉን እንዲቆጣጠር ለአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር መ/ቤት (State Department) ትዕዛዝ የተላለፈበት ነው። እንግዲህ ይህ ትዕዛዝ ይፋ ከሆነበት ጊዜ ጀምሮ የሚነሱት መከራከሪያዎች በርካታ ቢሆኑም በምላስ “ነጻ ነኝ” የሚለውና በግብር “ለጌቶቹ ጥሩ ባሪያ” በመሆን 22 ዓመት የዘለቀው ኢህአዴግና ከአሜሪካ ግንኙነታቸው በነበረበት መንገድ ስለመዝለቁ ጥያቄ የሚያስነሳ እንደሆነ አብዛኞች ይስማማሉ። አሜሪካ ከዚህ ውሳኔ የደረሰችው በወፍ ዘራሽ ሳይሆን በሂደት እንደሆነ በመጥቀስ አቶ ኦባንግ ሜቶ ከሚያቀርቡት ሃሳብ ጋር ይስማማሉ።
የሰብዓዊ መብት ተቆርቋሪ ድርጅቶች መረጃ ላይ ተንተርሰው ለሚያወጡት ሪፖርት “ተራ የማበሻቀጪያና የማጣጣያ” መልስ በመስጠት፣ ሲለውም ተቃዋሚዎችን የሚደግፉና የኢህአዴግ የኢኮኖሚና የፖለቲካ እምነት /የአብዮታዊ ዴሞክራሲ ጎዳና/ “ቅንቅን” የሆነባቸው የምዕራብ አገራት “ተላላኪ” በማስመሰል አሁን ድረስ ሲዘልፋቸው መቆየቱ አይዘነጋም። ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑ እንደሚሉት አሁን አዲስ ለጸደቀው የአሜሪካ ቅድመ ሁኔታ ላይ ያተኮረ የርዳታ መርሃ ግብር እነዚህ ክፍሎች በቁጥጥርና በክትትል በኩል ሪፖርታቸው ዋና ግብዓት ስለሚሆን ኢህአዴግ መንታ ፈተና ውስጥ እንደሚወድቅ ቅድመ ትንበያዎች አሉ።
በዚሁ መነሻ ኢህአዴግ የህልውናው መሰረት የሆነውን እርዳታ ለማግኘት “የፖለቲካ አመለ ሸጋ ሆኖ የዘጋቸውን በሮች ከፍቶ የሚመጣውን የህዝብ ወሳኝነት መቀበል፣ አሊያም በሂደት ሰልሎና ተሽመድምዶ መክሰም የመጨረሻው እድል ፈንታው ይሆናል” የሚሉ ወገኖች ጥቂት አይደሉም።
ኢህአዴግ በመንታ መንገድ ላይ – የህጉ ተጽዕኖ ከፖለቲካና ኢኮኖሚ አንጻር
ውሳኔውን ከፖለቲካው እንደምታና ከኢኮኖሚው ጣጣ ጋር በማያያዝ አስተያየት የሰጡን እንደሚሉት ከሆነ ጉዳዩ አደጋ አለው። እንደሚታወቀው የኢህአዴግ አገዛዝ ከጠቅላላው የምዕራብ መንግስታት ከሶስት ቢሊዮን ዶላር በላይ ዕርዳታ በየዓመቱ ያገኛል። ይህ ከፍተኛ መጠን ያለው ዕርዳታ ከአጠቃላይ አመታዊ በጀቱ 50% የሚሆነውን ይሸፍንለታል። ከአሜሪካን ብቻ አንድ ነጥብ ስምንት ቢሊዮን ዶላር በየዓመቱ በዕርዳታ መልክ ያገኛል። ይህም ከአሜሪካ የሚገኘው ርዳታ ብቻውን የበጀቱን አንድ ሶስተኛውን ይሸፍንለታል።
በዚህ መነሻ የኮንግረሱ ውሳኔ በኢህአዴግ አገዛዝ ላይ ያልጠበቀው ዱብ ዕዳ እንደሆነ በጀርመን የልማት ኢኮኖሚክስ ባለሙያው (Development Economist) ዶ/ር ፈቃዱ በቀለ ይናገራሉ። ይህ እሳቸው “ዱብዕዳ” ያሉት ውሳኔ የፖለቲካ ውዝግብ ማስነሳቱ የማይካድ ነው። ኢህአዴግ ከአውሮፓና ከአሜሪካ የሚያገኘውን ድጎማና ርዳታ ለምን ተግባር ሲያውለው እንደነበር ከማንም በላይ ጠንቅቆ ስለሚያውቀው ከቅድመ ሁኔታ ጋር የተያያዘ የዕርዳታ አሰጣጥ ከኢኮኖሚ ይልቅ የፖለቲካና የስነልቦናው ተፅዕኖው እንደሚያስከትልበት እኚሁ ምሁር ያስረዳሉ።
ከአጠቃላዩ የማክሮ ኢኮኖሚ አንጻር ውሳኔው ሊያስከትል የሚችለውን ተጽዕኖ በዝርዝር በማስቀመጥ አስቀድሞ መናገር ባይቻልም አሉታዊ ተጽዕኖ ሊኖረው እንደሚችል መገመት እንደማያዳግት ዶ/ር ፈቃዱ ከጎልጉል ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽ ሰጥተዋል። “ከአጭርና ከመካከለኛ ጊዜ አንፃር ስንመለከተው የአገዛዙን የኢኮኖሚ አካሄድ ጥያቄ ውስጥ ሊያስገባ ይችላል” ያሉት ባለሙያው፣ “… ወደፊት አዳዲስ የስራ መስክ መክፈት፣ በኢኮኖሚው ዕድገት፣ በውጭ ምንዛሪ ግኝትና በውጭ ሚዛን ዕድገት ላይ ሊኖረው የሚችለው ተፆዕኖም ቢሆን ይህ ነው ብሎ መናገር አይቻልም። ይሁንና የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ እርስ በርሱ የተያያዘ ስላልሆነና፣ አብዛኛው ህዝብም በኢንፎርማልና ከእጅ ወደ አፍ በሚገኝ ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ውስጥ የሚተዳደርና የሚሳተፍ ስለሆነ ሊጎዳ የሚችለው በዘመናዊ መስክ የተሰማራውን ሰራተኛና ሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎች ነው” በማለት ቅድመ ግምታቸውን ያስቀምጣሉ።
ሲያብራሩም ከቅድመ-ሁኔታና ከጥብቅ ቁጥጥር ጋር የተያያዘ በዕድገት ስም የሚፈስ ዕርዳታ በአጠቃላይ ሲታይ በህዝቡ ኑሮ መዛነፍ ላይ የሚኖረው ተፅዕኖ ዝቅተኛ መሆኑንን የሚያመለክቱት ዶ/ር ፈቃዱ፣ ከ10-11በመቶ “ያለማቋረጥ” አደገ በሚባለው የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ከኢትዮጵያ ህዝብ ኑሮ መሻሻል ጋር ተያያዥነት እንደሌለው ይናገራሉ። ቅድመ ሁኔታ የተቀመጠለት እርዳታ  ቢቀነስ ወይም እንዳለ ቢታገድ በተመሳሳይ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ የሚያመጣው አሉታዊ ውጤት ምን ሊሆን እንደሚችል ከወዲሁ በቁርጥ ማስቀመጥ እንደሚያዳግትም ባለሙያው ይጠቁማሉ።  በዚህ ዓይነቱ የዕርዳታ አካሄድ እስካሁን የተጎዳው ህዝብ በመሆኑ የዕርዳታው መቀነስ ወይም መታገድ አገዛዙን እንጂ በዚያ አካባቢ የሚኖረውን ህዝብ በቀጥታ የሚመለከት አይሆንም። በህዝብ ኑሮ ላይ የሚከተለውን ማህበራዊ ኪሳራ ተምኖ ማስቀመት ቢችግርም “ወያኔ ቅድመ ሁኔታውን  ተግባራዊ የሚያደርግ ከሆነ በተለይም በቀጥታ በኗሪው ህዝብ ህይወት ላይ አዎንታዊ ውጤት ማሳየቱ ግን የማይቀር ነገር ነው” ሲሉ ግርድፍ ምልከታቸውን ያኖራሉ። በሴፍቲኔት፣ በአነስተኛና ጥቃቅን፣ ወዘተ የህዝቡን ኑሮ እየቀየርኩ ነው የሚለው “ልማታዊው” ኢህአዴግ እንዲህ ዓይነት በቅድመ ሁኔታ የተወጠረ ዕርዳታ በሕዝቡ ኑሮ ላይ ቀውስ ያመጣል በማለት የራሱን ቅንብር እንደሚሰራ የሚከራከሩም አሉ፡፡
ዶ/ር ፈቃዱ በቀለ
ዶ/ር ፈቃዱ በቀለ
ፖለቲካዊ ይዘቱን የዳሰሱት ዶ/ር ፈቃዱ ሁለት መሰረታዊ ጉዳዮችን በመጠቆም ለውይይት የሚጋብዝ ፍንጭ ሰጥተዋል። “ውሳኔ ሕጉ ያካተታቸው ቅድመ ሁኔታዎች ከረዥሙ አጠቃላዩ የማክሮ ኢኮኖሚ ሁኔታ አንፃር ስናየው ግን በዕውነቱ እንደዚህ ዓይነቱ ከቅድመ-ሁኔታ ጋር የተያያዘ ዕርዳታ ላይጎዳው ይችላል። አገዛዙ ከምዕራቡ አገራት የሚመጣበትን ግፊት የሚቋቋም መስሎት የሚታየው ከሆነ ፊቱን ወደ ቻይናና ወደ ሌሎች ቅድመ ሁኔታን ከማያሰቀድሙ አገሮች ዕርዳታ በማግኘት ከአሜሪካን የሚሰጠውን ዕርዳታ ሊያካክስና በነበረበት ሁኔታ ለመቀጠል መንፈራገጡ” አንደማይቀርም አመላክተዋል። ይህ ግምታቸው ግን ጥርጣሬያቸው እንዳለ ሆኖ ነው።
“ኢትዮጵያ ካለችበት የጂኦ ፖለቲካ፣ የአፍሪካ ህብረት ዕምብርትና መቀመጫም ስለሆነች ቻይናዎች ከራሳቸው የንግድ መርህ አንጻር ዕርዳታውን ከመስጠት ወደኋላ ሊሉ አይችሉም” ሲሉ የጉዳዩን ሌላ መልክ ያሳዩት ዶ/ር ፈቃዱ፣ አማራጩ ከአሜሪካንም ሆነ ከተቀረው የምዕራቡ ዓለም ጋር ተላትሞ ወደ ቻይና ፊትን በማዞር የሚደመደም ከሆነ አገዛዙ ዕድሜውን ለማሳጠር ራሱ እንደወሰነ የሚቆጠርበት ይሆናል። ኢህአዴግ አምርሮና የመጣው ይምጣ በሚል ቅድመ ሁኔታዎችን አላሟላም፣ ዕርዳታችሁንም አንፈልግም የሚል ከሆነ አሜሪካን አማራጭ ለመፈለግ ልትሞክርና ይህንንም እንደማስፈራሪያ ተጠቅማ ልትለሳለስ” እንደምትችል ዶ/ር ፈቃዱ አመላክተዋል።
እንደወያኔ የሚታዘዝላት ድርጅትና መሪ እስካላገኘ ድረስ ኢህአዴግ ላይ አደጋ እንዲነግስ ወይም ከነጭራሹ እንዲወገድ አሜሪካ ትሰራለች ብለው እንደማያምኑም ገልጸዋል። “እንዲያውም” አሉ ዶ/ር ፈቃዱ “በኮንግረሱ የፀደቀው ህግና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር (State Department) እንዲቆጣጠረው የተደረገው የዕርዳታ አሰጣጥ ዘዴ፣ የኦባማ አስተዳደር ሌላ መንገድ ፈልጎ ኮንግረሱን በማለፍ፣ በቀጥታ ከአሜሪካን የውጭ ዕርዳታ አሰጣጥ ጋር ባልተያያዘ መንገድ የኢህአዴግን አገዛዝ በተዘዋዋሪ ሊረዳበት የሚችልበት መንገድ እንደሚኖር መጠራጠር ይቻላል” ሲሉ ሃሳባቸውን ያጠናክራሉ። ገደቡ በተለይም አገዛዙ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሰላም ጥበቃን፣ የፀረ-ሸበርተኝነትን፣ የድንበር ጥበቃንና እንዲሁም የመከላከያ አዛዡን ስታፍ ሰራተኞች ስለማይመለከት ተጽዕኖው በወታደሩ ላይ ዝቅ ያለ መሆኑንን አንደማሳያ ይጠቁማሉ።
ፍርድ ቤቶችን ከፖለቲካ ተፅዕኖ ቁጥጥር ስር ውጭ ማድረግ፣ የሚዲያ፣ ሀሳብን በነጻነት የመግለጽና የመሰብስብ ነፃነት፣ እንዲሁም ሌሎች በቅድመ ዕርዳታው መስፈርት ሆነው የተዘረዘሩትን አንኳር ጉዳዮች ኢህአዴግ አጥብቆ የሚፈራቸውና ህልውናውን አደጋ ላይ የሚጥሉት በመሆናቸው በቀላሉ ለመቀበል የሚያዳግተው መስፈርቶች እንደሆኑ ለማንም ግልጽ ነው ሲሉ ዶ/ር ፈቃዱ ተናግረዋል። ይልቁኑም “እስካሁን ድረስ ለምን ዘገዩ? የሚመለከተው አካልም ሆነ የኦባማ አስተዳደር እስካሁን ድረስ ምን አስጠበቃቸው? አሁን ምን አዲስ ነገር ታያቸው? እስካሁን ድረስ የኢትዮጵያ ህዝብ ይሰቃይ ላይ አልነበረም ወይ? ለ22 ዓመታት የአገዛዙ የጭቆና ድርጊት ከአሜሪካ መንግስት የተሰወረ ጉዳይ ነበር ወይ? የሚሉት ጉዳዮች ሲነሱ የጸደቀውን ህግ ጉዳይ በጣም እንቆቅልሽ ያደርገዋል” በማለት ከጉዳዩ ጀርባ አንድ በጊዜ ሂደት እየጠራ የሚሄድ ጥቅል ጉዳይ ስለመኖሩ አመላካች እንደሆነ ምሁሩ ያስረዳሉ። በዚሁ መነሻ ፓለቲካዊ ትርጉሙ በቀላሉ ሊታለፍ የማይችልና ለአገዛዙ አስቸጋሪ ሁኔታ የሚፈጥርበት እንደሚሆን መገመቱ ከባድ እንዳልሆነ ይገልጻሉ።
“በሌላ ወገን ግን ለነፃነትና ለዲሞክራሲ ለሚደረገው ትግል አዎንታዊ ተፅዕኖ ያለውን ያህል፣ የራሱ የሆነ አሉታዊ ተፅዕኖም ሊኖረው ይችላል። ምናልባት አገዛዙ የተወሰኑ ነገሮችን የሚያሟላ ከሆነ ተቃዋሚው ኃይል ወደ መመቻመች /ኮምፕሮማይዝ/ ውስጥ በመግባት ለአጠቃላይ ነፃነት የሚደረገው ትግል አደጋ ውስጥ እንዲወድቅ ያደርገዋል። ይህ ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያ ህዝብ የነጻነትና የብልጽግና ጉዳይ የዓለም አቀፍ ኮሚኒቲው በሚፈልገው አካሄድ ብቻ የሚወሰን ይሆናል ማለት ነው” ሲሉ አጠቃላይ ስጋታቸው ያስቀመጡት ዶ/ር ፈቃዱ፣ አጠቃላይ ህዝቡን የሚጠቅም የኢኮኖሚ ዕድገት፣ የሀብት ክፍፍል፣ በተለይም የመሬት ጥያቄ፣ እስከዛሬ ድረስ የተፈጠረው አዲስ የይዞታና የህብረተሰብ ግኑኝነት፣ የኢትዮጵያ ህዝብና ዲሞክራቶች በሚፈልጉት መንገድ ላይፈቱ በሚችሉበት ሁኔታ መሰናክል ይደርስበታል። ስለዚህ ይህ ዓይነቱ ውሳኔ ህግ የዛሬው አገዛዝ ወደፊት በስልጣን ዙሪያ ሊኖረው የሚችለው ተሳትፎ፣ የኃይል አሰላለፍ ጉዳይና የፓለቲካው አወቃቀርና አካሄድ ጉዳይ ላይ፣ የኢኮኖሚያዊና የህብረትሰብ ግኑኝነት፣ ማለትም የሀብት ክፍፍልና አዲስ ሀብት በአዲስ የኢኮኖሚ ፖሊሲ መሳሪያ የመፍጠር ጉዳይ፣ የማህበራዊ ጥያቄ ጉዳይ፣ እነዚህና ሌሎች ለአገሪቱ የወደፊት እንደህብረተሰብ መኖርና መገንባት አንፃር በሰፊው ካልታየና ተቃዋሚ በሚባለው ጭንቅላት ውስጥ ካልተብላላ አደጋም ሊኖረው ይችላል።
በሌላ አነጋገር የዕድገታችንን ጉዞ ሊያጣምመው ይችላል። ምክንያቱም ይህ ዓይነቱ ውሳኔ ህግ እስከተወሰነ ደረጃ ድረስ ቢሟላና አገዛዙም እንደፖለቲካ ኃይል ተፎካካሪ ሆኖ የሚቆይ ከሆነ ወደፊት ለሚወሰዱ አገርን የሚጠቅሙ የዕድገት ዕርምጃዎች መሰናክል እንደሚሆን መጠርጠር ይቻላል። በሌላ አነጋገር የኢትዮጵያ ህዝብ ከዚህ አገዛዝ ባሻገር ሊገነባው የሚችለው አዲስ ኢትዮጵያ የብዙ ዓመታት ህልም ሆኖ ሊቀር እንደሚችል የራሳቸውን አማራጭ ምልከታ አስቀምጠዋል። ሌላኛውንም መንገድ አካተዋል።
በሌላው በኩል ደግሞ ይህ ውሳኔ ህግ በገዢው መደብ ውስጥ ቅራኔን መፍጠሩ እንደማይቀር፣ ህይወታቸውን ከአሜሪካን መንግስት ጋር ያያዙ ኃይሎች፣ በተለይም ግፊቱ እየበዛ ሲሄድ ወደፊት የሚመጣባቸውን አደጋ በማጤን ውሳኔ ህጉን በከፊልም ሆነ መሉ በሙሉ ተግባራዊ እናድርግ በሚሉ (ዘመናዊ ወያኔዎች) እና ውሳኔ ህጉን አንቀበልም በሚሉ አክራሪ ኃይሎች መሀከል ፍጥጫ መፈጠሩ እንደማይቀር ዶ/ር ፈቃዱ ግምገማቸውን አኑረዋል።
ቀጥሎስ?
በጉዳዩ ዙሪያ ከጎልጉል ጋር ወደፊት ሰፊ ቃለ ምልልስ ለመስጠት ፈቃዳቸውን የገለጹት አቶ ኦባንግ “እዚህ የተደረሰው በወፍ ዘራሽ ዝም ተብሎ አይደለም፤ ብዙ ተለፍቶ ነው። የአውሮፓ አገራት ተመሳሳይ ጥያቄ ሲቀርብላቸው አሜሪካን ምክንያት ሲያደርጉ ነበር። አሁን ሊያቀርቡ የሚችሉት አንዳችም ምክንያት የለም። አጠናክረን ስራችንን እንሰራለን። ሰክነን እንታገላለን። ኢህአዴግ ሳይወድ በግዱ በሩን ይከፍታል” ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል። ከአውሮፓ አገራት ጋር አጋሮቻቸው በመሆን ስራቸውን በአዲስ መልክ እያጠናከሩ መሆናቸውን አስታውቀዋል። ይህንን አዲስ ህገ ውሳኔ በማስረጃነትና በማቅረብ የአውሮፓ መንግሥታም ተመሳሳይ እርምጃ እንዲወስዱ፤ በሚሰጡት ዕርዳታም ሆነ ድጎማ ላይ ኢህአዴግን ተጠያቂ በማድረግ የፖለቲካ ምህዳሩ እንዲሰፋ መርዳት ባይችሉም እንኳን ኢትዮጵያውያን ለሚያደርጉት ትግል እንቅፋት እንዳይሆኑ አበክረን እንወተውታለን ብለዋል አቶ ኦባንግ፡፡
አዲስ ስለ ጸደቀው ውሳኔ ህግ ለተጠየቁት “ብዙ ለመናገር ጊዜው ገና ነው። ኢትዮጵያዊያን በጎሳና በዘር የደም አዙሪት ውስጥ እየፈሩ እንዲኖሩ ሲደረግ የነበረው ድጋፍ ግን ማክተሚያው የተቃረበ ይመስለኛል፤ ኢህአዴግ እኔ ሥልጣን ከለቀቅሁኝ በአገሪቷ ውስጥ ደም መፋሰስ ይሆናል፤ ኢንተርሃምዌ የዘር ዕልቂት ይካሄዳል፤ የአፍሪካ ቀንድም ቀውስ ውስጥ ይገባል፣ ወዘተ በማለት እየዘላበደ የተቃዋሚውን ኃይል ከማዳከም አልፎ ሕዝቡ ፍራቻ ውስጥ በማስገባት አሜን ብሎ እንዲኖር የተጠቀመበት ማደንዘዣ ኃይሉ እየደከመ መጥቷል፤ ይኽኛው የውጭው ነው” የሚል ጥቅል መልስ ሰጥተዋል።
የመንታው መንገድ መሃንዲስ – ቻይና?
ቻይና ከኢህአዴግ በተለይም ከህወሃት ከፍተኛ ሰዎች ጋር አላት ከሚባለው “የተለወሰ ሽርክና” አንጻር አሜሪካ የምትሰጠውን የበጀት ድጎማና ርዳታ በየዓመቱ እየሸፈነች ኢህአዴግን ትታደጋለች የሚለው ጉዳይ ቻይና ከምትከተለው መሰረታዊ የንግድ እምነትና አንጻር በዜሮ የሚባዛ እንደሆነ ይነገራል። ቻይና ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ነዳጅና ማዕድን እየተከተለች የምትገባበት ኢንቨስትመንት እያከሰራት እንደሆነ የሚናገሩ ክፍሎች ቻይና የሃይል ሚዛኑን ተመልክታ ርምጃዋን ከማስተካከል ያለፈ ስራ እንደማትሰራ ይናገራሉ።
china_africa_usበሌላ በኩል ደግሞ ሰሞኑን ይፋ ሆኖ የሰነበተውና የቻይናን “የዓይን ቀለም” የቀየረው የጃፓኑ ጠ/ሚ/ር የኢትዮጵያ ጉብኝትና የፖለቲካ መሞዳሞድ በቻይናና በኢህአዴግ መካከል የግንኙነት መሻከር እንደሚፈጥር የፖለቲካ እሳቤ አለ፡፡ ኢህአዴግ ከቻይና ታሪካዊ ጠላት ጃፓን ጋር በግልጽ ይህንን ዓይነቱን “ያደባባይ ፍቅር” ማሳየቱና የፖለቲካ ቅርጫ ውስጥ መግባቱ የምዕራቡ ወዳጅ ከሆነችው ጃፓን ጋር በመወገን በምዕራባውያን የድጎማ ዕቀባ ጭስ እንዳይታፈን መተንፈሻ እየፈለገ መሆኑን የሚያሳይ ነው፡፡
ሰጥቶ በመቀበል፣ አበድሮ በመውሰድና የአምባገነኖችን ህልውና ለማስጠበቅ የሚውል ቴክኖሎጂን በመገንባት አፍሪካን እያለበች ያለችው ቻይና ኢህአዴግ ከምዕራባውያን የሚያኘው እርዳታ ቢቋረጥበት ከብድር በዘለለ በየዓመቱ ሌሎቹ እንደሚያደርጉት በጀት እየደጎመች የኢህአዴግን  ነፍስ ለመጠበቅ የምትምልበት ዘመን ሊኖር እንደማይችል ከግምት በላይ የሚናገሩ ክፍሎች፣ ኢህአዴግ መለሳለስ በመሳየት ቆዳውን ሊቀይር ይችላል የሚለው እምነት አላቸው። አሜሪካ አሁን የያዘችው አቋም ከምትከተለው አዲሱ ፖሊሲዋና በሂደት የኢትዮጵያ ጉዳይ ተመርምሮ የተያዘ ስለሆነ እንደ HR2003 በውስዋስ (ሎቢ) ሊቀለበስ የሚችል እንዳልሆነ አጥብቀው ይናገራሉ።
ባለፈው ዓመት ነሐሴ ወር መጀመሪያ ላይ ለጎልጉል አስተያየት የሰጡ ዲፕሎማት ጠቅሰን ገመዱ በኢህአዴግ ላይ እየከረረ እንደሚሄድ በዘገብን ወቅት “ኢህአዴግ በቅርቡ የአውሮፓ ህብረት ተወካዮች እስር ቤቶችን እንዳይጎበኙ እንደከለከለው ማድረግ አይችልም … በደቡብ ሱዳን ያለው የፖለቲካ ቀውስ፣ በሶማሊያ ጭብጡ ያለየለት ሁከት፣ በኤርትራ ያለው የዛለ መንግስት እጣፈንታና የኢትዮጵያን ህዝብ በዘር ከፋፍሎ ጥቂቶች እንዲበለጽጉ ያደረገው ኢህአዴግ መጨረሻው አሜሪካንን በእጅጉ ሃሳብ ላይ ጥሏታል። በዚህም የተነሳ ኢትዮጵያ ውስጥ እየሰፋ የሄደው ቁርሾና የጥላቻ ፖለቲካ ሳይፈነዳ ኢህአዴግን ማረቅ የአሜሪካ ቀዳሚ አጀንዳ ሆኗል። ይህንን አጀንዳ አሜሪካ በቀላሉ ተጭበርብራ የምትቆልፈው አይሆንም። ኢህአዴግ በጎሳ ደምና እኔ ከሌለሁ አገርና አፍሪካ ቀንድ ይተራመሳል በሚል የሚነግደውን ንግድ አሜሪካኖቹ ተረድተዋል ብለን ነበር፡፡ የአሜሪካው ምክርቤት እንደራ የሆኑት ክሪስ ስሚዝ “በሽብር ዙሪያ ከአሜሪካ ጋር ተባብሮ መስራት ህዝብን ለማፈንና ረግጦ ለመግዛት ዋስትና አይደለም” በማለት መናገራቸውን ከዲፕሎማቱ አስተያየት ጋር አክለን ነበር፡፡
አዲስ የወጣውን ውሳኔ ህግ አሜሪካ በኢህአዴግ ላይ ፊቷን እያዞረች መሆኗን ማሳያ ነው በማለት የሚወስዱ ክፍሎች ይህ ህግ ከቀድሞው HR2003 ፈጽሞ የተለየ እንደሆነ ይናገራሉ፡፡ የዛሬ አስር ዓመት፤ HR2003 በምክር ቤት ደረጃ የእንደራሴዎችን ከፍተኛ ድጋፍ ካገኘ በኋላ የሕግ መወሰኛ ም/ቤት (ሴኔት) አጽድቆት በፕሬዚዳንቱ ተፈርሞ የአሜሪካ ፖሊሲ እንዳይሆን በመደረጉ ተቋማዊና አስተዳደራዊ ለውጥ ሊያመጡ የሚችሉ ጉዳዮች መከኑ። በወቅቱ የህጉ መርቀቅና እንዲጸድቅ የተጀመረው እንቅስቃሴ ያስበረገገው ኢህአዴግ ጡረተኛ የሴኔት አባላት ከሚመሩት ዲኤልኤ ፓይፐር ከተባለ የውስዋስ (ሎቢ) ቡድን ጋር ከፍተኛ በጀት በጅቶ ታገለ። ባፈሰሰላቸው መጠን ወትዋቾቹ ባልደረቦቻቸውን ጠመዘዙና ህጉ አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ የምትከተለው አዲስ የዴሞክራሲና የሰብዓዊ መብት ህግ እንዳይሆን ተደረገ።
አሁን አዲስ የወጣው ህገ ውሳኔ ግን ከዚህ የተለየ ነው፡፡ ምንም ዓይነት በገንዘብ ለኢትዮጵያ ፖሊስና የጦር ኃይል ከመለቀቁ በፊት የኢህአዴግ ሸሪክ የሆነውን የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚ/ር መስሪያቤት ገንዘቡን ለሚፈቅደው የምክርቤት አከፋፋይ ኮሚቴ በኢትዮጵያ ውስጥ የህግ አካላት በነጻነት የሚሰሩ መሆናቸውን፣ የመናገር፣ የመሰብሰብ፣ የሃይማኖት ነጻነት መኖሩን፣ የተቀናቃኝ ፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የሲቪክ ማኅበራትና ጋዜጠኞች ያለ ወከባና አፈና ሊሰሩ መቻላቸውን ማረጋገጫ መስጠት አለበት፡፡ በሌላ በኩልም በሶማሊ ክልል የሰብዓዊ መብትና ግብረሰናይ ድርጅቶች በነጻነት መንቀሳቀስ መቻላቸውን፣ ለወታደርና ለፖሊስ ኃይላት ስልጠና የሚሰጠው ገንዘብ በሰብዓዊ መብት ጥሰት ላይ ለሚገኙ ክፍሎች እንዳይደርስ የሚያረጋግጥ ሰነድ፣ እነዚህን መብቶች በጣሱ የሠራዊቱና የፖሊስ አባላት ላይ ምርመራ በማድረግ ደረጃ የኢትዮጵያ መንግሥት የወሰዳቸውን እርምጃዎች ምን እንደሆኑ የሚያረጋግጥ ሰነድ በማቅረብ ይሆናል፡፡
ከዚህም ሌላ “የልማት ዕርዳታ” እና “የኢኮኖሚ ድጋፍ ፈንድ” በሚል ለታችኛው ኦሞ ሸለቆና በጋምቤላ ለሚኖሩ የሚሰጠው ዕርዳታ በምንም ዓይነት መልኩ ነዋሪዎቹን በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ መንገድ አስገድዶ በማፈናቀል ተግባር ላይ እንዳይውል፤ የነዋሪዎቹ ህይወት በሚያሻሽል ሥራ ላይ ብቻ የሚውል መሆኑ እና ከነዋሪዎቹ ጋር በምክክር የሚደረግ መሆኑን የሚያረጋግጥ ሰነድ የውጭ ጉዳይ ሚ/ር መ/ቤት ማቅረብ አለበት፡፡ መ/ቤቱ ይህንን ሳያረጋግጥ ገንዘብ መውሰድ አይችልም፡፡ ኢህአዴግን ለመደገፍ በሚል የተዛባ መረጃ በማቅረብ ገንዘቡን ወስዶ ለኢህአዴግ እንዲደርስ ቢያደርግ እንኳን የሰብዓዊ መብት ድርጅቶች የኢትዮጵያን ሁኔታ አስመልክቶ የሚያወጡት ዘገባ ዕውነቱን ቁልጭ አድርጎ የሚያጋልጥበት ይሆናል፡፡ ከውጭ ጉዳይ ሚ/ር በተጨማሪ የገንዘብ ሚ/ር መ/ቤት (Department of Treasury) በኢትዮጵያ ውስጥ አስገድዶ ከመኖሪያ ቦታ ከማፈናቀል ጋር በተያያዘ ለሚደረግ እንቅስቃሴ ምንም ዓይነት ዕርዳታ እንዳይሰጥ ለዓለምአቀፉ የፋይናንስ ተቋም ዋና ዳይሬክተር መመሪያ እንዲሰጥ ታዟል፡፡
ይህንን እና የመሳሰሉ የትም የማያፈናፍኑ መመሪያዎች ያካተተው ውሳኔ ህግ የራሱ የሆኑ ተጽዕኖዎች ያመጣል እየተባለ በሚጠበቅበት ሁኔታ ለሚከሰት ማናቸውም ዓይነት ክፍተት ቻይና ከኢኮኖሚ ጥቅሟ አኳያ ለኢህአዴግ መድህን ሆና ልትቀርብ የምትችልበት ሁኔታ በብዙዎች አንድ አመኔታ የሚጣልበት አይደለም፡፡ በውጭ ምንዛሪ እጥረት ውስጥ ያለው ኢህአዴግ ከመጪው ምርጫ አኳያ እንዲህ ዓይነት በቅድመ ሁኔታዎች የታጠረ ህገ ውሳኔ አክብሮ ይቀበል ይሆን? ወይስ ፊቱን በአሜሪካ ላይ በማዞር በእብሪት ቻይናን ታደጊኝ ይላታል? መንታው መንገድ በዚህ የሚያቆም አይመስልም – የራሱን መንታ መንገዶች እየከፈተ ይሄዳል የሚሉ ፍንጮችም እየታዩ ነው፡፡http://www.goolgule.com/eprdf-at-cross-road/

Monday, February 10, 2014

የነጻነት ትግል መሰዋእትነት ብእርም ብቻ አይደለም ተግባርም እንጂ!

የጽሁፌ መነሻ Ato ያሬድ ሃይለ ማርያም ወረድ ብሎ ደግሞ የማይቀረው ማእረግ ያለበት ለ ሰባት አመት በኢትዮጵያ የሰበአዊ መብት ምክርቤት የሰራ በወያኔ ግፍ ከሚወዳት ሀገሩ በ97 አም ጭፍጨፋ የተሰደደ ከፈለጋችሁ ደግሞ በአውሮፓ ህብረት የተናገረውን ምስክርነት ተመልከቱ ይላል። ይበጅ ብያለሁ! ከዚህ በፊት ለዳዊት ከበደ(አውራምባ ጋዜጠኛ) እልል በሉ ተብለን በኢሳት ቀርቦ እንዲሁም ሌሎች ሌሎች ተደርጎ አጨብጭበናል። ይህም ይሁን ዝናን የማይፈልግ ኢትዮጵያዊ ቁጥር በጣም ጥቂት ስለሆነ… ፕሮፌሰር…ዶክተር….ተመራማሪ…..ኢንጅነር…አንጋፋው ጋዜጠኛ…አንጋፋው አርቲስት… ወዘተ ብዙ ዝና አለን። ብዙ የነጻነት ታጋዮች፣ ወታደሮች የሉንም ቢኖሩም ጥቂትና እነሱንም ማጥፋት የተለመደ እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል ባህሪያችን ነው። ምክንያቱም እነዚህ የነጻነት ታጋዮች ከዶክተሮቹ ከሰበአዊ መብት ተሟጋቾቹ መብለጥ የለባቸውም በሚል አናሳ አስተሳሰብ ነው። ቆብ ሌላ ተግባር ሌላ።
Ginbot 7 Popular Force - GPF formed
ወያኔ በሚሰጠን የቤት ስራ እየተዘናጋን ስራ ፈቶችን ሰብስቦ ትግሉ አንድ እርምጃ ወደፊት እንዳይራመድ እንባላ ዘንድ ማእረግ ባላቸው ሰዎች የምቀኝነትን መርዝ ማሰራጨት ይጀምራል። እኛ ደግሞ እንመቻቻለን። የነጻነት ትግል መንገዱን ወጣ ገባ ለማደረግ ያልተተባ፣ ያልተገራ ብእራችንን አንስተን “ግንቦት 7 ሆይ ፍረስ ወያኔ የጀመረን ይጨርሰን፣ ተዋርደን መገዛታችን እንቀጥል ዘንድ ወታደሮችህን ጋዜጠኞች አድርጋቸውና የዜና ሀተታ ይስሩልን” እንላለን።
እኔ ግን ከቻልን ትግሉን መቀላቀል ካልቻልንና እውነተኛ የኢትዮጵያ ህልውና እንዳትፈራርስ የምንፈልግ ከሆንን እሲት ገለል እንበል። ለወያኔ ብቻ ሳይሆን ለግንቦት ሰባትም፡፡ ማናችንም ቢሆን ብእርን አንሰተን ዌብሳየት ፈጥረን የምንታገለውን መሰዋእት ሳይሆን፤ እንደ እየሱስ ክርስቶስ በሞታቸው ድነትን፣ በደማቸው ነጻነትን፣ በአጥንታቸው ክብርን ሊመልሱልን ከበርሃ ማዶ ድቅድቅ ባለ ጨለማ የኢትዮጵያን ኤሎሄ ሰምተው ዳር ሳይሆን እሳት ላይ ያሉትን ጀግኖች ከእነ ችግራቸው በርቱ ከማለት ፈራርሱ ብሎ ማለቱ ማን ነኝ እኔ ማን ነው እሱ? እንበል እኔ ማጨብጨብ ደክሞኛል።
ስለዚህ ጸሃፊውና ብእሩ ምነው በዴሞክራቲክ በተባለው የወያኔ ግሩፕ ላይ አተኩሮ ሀገራችንን አደጋ ውስጥ የከተታትን ‘እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይበቅል’ ያለቸውን አህያ ነጭና ጥቁር አሊያም ቢጫ መሆኗን በካበቱት ልምዳቸው ለምን አላዩልንም ወይስ ይሄን አይጋ ፎረም ላይ አገኘዋለሁ?
በአኬልዳማ ድራማ ወያኔ ይህንን ጸሃፊው አሁን ያሉንን “የብዙ ወጣት ኢትዮጵያዊያኖችም ሕይወት በዚህ መያዣና መጨበጫ በሌለው የግንቦት 7 ቅዥት ተደናቅፏል” የሚለውን ዜማ ደጋግመን ሰምተናል። አብዛኞቻችን አይ ወያኔ እና ኢቲቪ ብለን እሰየው ግንቦት 7 በርቱ ወያኔ እንቅልፍ አጥቶ ሌሊት እየተነሳ ድራማ መስራት ጀምሯል አልን፤ ደገፍናቸውም። ታዲያ ወያኔና አጫፋሪዎቹ በደነገጡ ቁጥር ስራ ሳይሰራ ይቅር? ኧረ ግንቦት ሰባቶች ይህን ሰምታችሁ ቅር እንዳትሰኙ። በአማራው ፕሬዝዳንት ለሃጫም አማራ፣ ማንነቱን የማያውቅ ጫማ የሌለው ህዝብ፣ በሶማሊያው ፕሬዝዳንት አማራው ና ኦሮሞው እንዳየተባበሩ ትግሬውን ውደዱ፣ ከደቡብ ደግሞ አማራውን አስወጡ፣ ዋልድባን አፍርሱ… ዜጎቻችን ህገ-ወጥ ናቸው በሳውዲ ይገደሉ… እኮ የትኛው ይሆን ግንቦት 7 ፈጽሞት እንታገለው የምንለው? ኧረ ጎበዝ ማንነው የምንታገለው? በዳዩን ወይስ ተበዳዩን?
በርግጥ ነው ዝና የሚፈልጉ ሰዎች ወይም እኔ ያልኩት ካልሆነ የሚሉ ሰዎች ብእራቸውን አንሰተው አንዴ ስለ ግንቦት 7 የውጪ ፖሊሲ ሌላ ግዜ ደግሞ ስለ መከረኛው የህዝብ ልሳን “ኢሳት” ላይ መጎንተራቸው አልቀረም። ይህም ባልከፋ የአጻጻፉ ዘይቤ ወይም የትረካው አጨራረስ ግን ምን አለበት አንድ ሆነን እንደ ግንቦት 7 መረር ብለን “ታላቁን’ ህወሃት እንጥለው ዘንድ አመስግነው ቢዘጉት፤ ከፈቶ ከማበላሸት ይልቅ።
ልጨርስ “ነፃነትን የማያውቁ ነፃ አውጪዎች’ መሆን ይከብዳል። ስለዚህ በእኔ እምነት ግንቦት ሰባት የሚባለውን ሁሉ እያዳመጠ ሙያ በልብ ብሎ እንደሚሰራ አልጠራጠርም። ዶክተሮችም፣ ፕሮፌሰሮቹም፣ ኢንጅነሮችም፣ ወታደሮቹም አሉት ለየት ከሌላው የሚያደርጋቸው ማእረጋቸው ሳይሆን ለተነሱለት አላማ መጠመዳቸው ለተግባራዊ ስራ መፍጨርጨራቸው ነውና ተግባርን እናስቀድም፤ ከዛ ደግሞ እንተቻቸው። ትችት ጥሩ ነው ግን ከቅንነት ጋር ሲሆን ይጠቅማል፡፡ ስለዚህ ጠላታችን ወያኔ ነው!!! ብእራችን፣ ገንዘባችን፣ ጉልበታችን ሁሉ ለነጻነት ለሚደረጉ እልህ አስጨራሽ ትግል የሚረዱ ጋሻዎች ይሁኑን እላለሁ።
ህዝባዊ ሃይሉም በርታ! የማንችል ደግሞ አምላክ ጩኸታችን ሰምቶ ሀገራችንን የሰላም የደስታና የነጻነት ሃገር ያድርግልን ዘንድ እንጸልይ። የምንችል ደግሞ አንድ ሁነን ትግሉ ውስጥ እንግባና እንደህዝባዊ ሃይሉ እምቢ ለነጻነቴ፣ ለሀገሬ እንበል!!! ነገር ግን እምቢ ለወሬ……http://ecadforum.com/Amharic/archives/10949/