WE NEED FREEDOM!

WE NEED FREEDOM!

Sunday, March 30, 2014

የጥላቻው እሳት ቆስቋሹን ያቃጥለው

የትግል መሰረቱን ጎጥ ላይ ያደረገ፣ የእድገት ልኩን ዘረፋ ላይ ያዋለና የእውቀት ጥጉን ውሸት ላይ የመሰረተ እንዴትም ሆኖ የነጻነት ታጋይ አይሆንም። ይልቁንም በሕዝብ ጫንቃ ላይ ተንፈራጥጦ እንዲኖር የክፋት መርዙን ይረጫል እንጂ። ምንም በሁኔታዎች አስገዳጅነት ቢተጣጠፍ እንኳ ኢትዮጵያዊነትን ከፍ የማድረግ አቅም ስለሌለው ሕብረት ያስፈራዋል፣ ነጻነት ያጥወለውለዋል፣ አንድነትም ያስበረግገዋል። ኢትዮጵያ ለወያኔ ትርፍ እስካስገኘች ድረስ እንደምትታለብ ላም ነች። ከዚያ በላይ ወያኔዎች ሀገራዊ ራዕይ የሚባል ነገር የላቸውም።Tigray people liberation front, tplf
እንደ ሀገርና እንደ ሕዝብ ያለብንን ፈተና በጎጥ መነጽር አይተን በጥላቻ ክርክር ተጯጩኸን በግል ስምና ዝና ጦዘን ልንወጣው ፈጽሞ አይቻለንም። በተለይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እለት በእለት የምንመለከተው ሁነት እያሳየን ያለው ተፋቅረንና  ተደጋገፈን መኖር የሚገባን ወገኖች ተናንቀን ስንነካከስ ነው። ጃስ እያሉ የሚያናክሱን ደግሞ እንግሊዝ በቀበረው የእርስ በእርስ መተላለቂያ ፈንጂ፣ ጣልያን በቀመመው የጎሳ ክልል መርዝና በየሃገሩ እሳት ጭረው በሚወጡት ለጥቅማቸው ሲሉ ምንም ከማድረግ በማይመለሱ ሀያላን እገዛ እየተጠቀሙ ወደ ጥፋት የሚነዱን ደናቁርቶች ናቸው። ሰሞኑን በወያኔዎችና ለወያኔ የጥላቻና ፕሮፖጋንዳ ሰለባ በሆኑ ቡድኖች ወገኖቻችንን በዘር ለማናከስ እንደ አበደ ውሻ የሚክለፈለፉ በዝተዋል። የሰከነ የአንድነት ድምጽ እንዳይደመጥ ወያኔ ከፍተኛ አፈና በሚያደርግባት ኢትዮጵያ ጎልቶ የሚደመጠው የደንቆሮ ጩኸት ነውና አማራጭ ድምጽ እንዲደመጥ ካላደርግን ህዝባችን ሊወናበድ ይችላል።
በከሃዲና ስግብግብ የአፍሪካ መሪ ተብዬዎች ውክልና የሀገርና አህጉር ሀብትና ቅርስ በንግድ ሽፋን ዘረፋ ላይ ለተሰማሩ ሀገር በቀልና የወጪ ከበርቴዎች እየተቸረ ነው። በዘመናዊ ትምህርት ስም የሀገር ፍቅርንና ለህዝብ የመቆም አስፈላጊነት ችላ እንድንል የተበረታታን ተልፈሰፈስንና የማንነት መሰረታችን ተናግቶብን ብዙ ዘመነኞች እኛንና ህዝባችንን ለብልቦ የሚፈጀንን የጥፋት እሳት እንደ ደመራ እያጨበጨብን ከበን እያየነው እንገኛለን።  ኢትዮጵያ በታሪክዋ አይታ የማታውቀው በሌላውም አለም ያልተለመደ አይነት አሳፋሪ የሀገር ጠላት የሆነ የዱርዬ ስብስብ መንግስት ነኝ እያለ አገሪቱን ለእቁብ ወይንም ለቤት ኪራይ ገንዘብ እንዳጠረው ነጋዴ ሃገራችንን በርካሽ ዋጋ እየቸበቸበ ይገኛል።
በሀገር ልማት ስም ከየአቅጣጫው የሚሰበሰበው የብድር መአት በኛ ዘመን ቀርቶ በልጅ ልጆቻችን ጊዜም ተከፍሎ አያልቅም። የተበደሩት ገንዘብ ግን ግማሹ ወደ መጣበት ሀገር ተመልሶ በሌቦቹ ባለስልጣናት ስም በተከፈቱ የባንክ ሂሳቦች ገቢ ተደርጎ የጨረቃ ሚሊየነሮችን መፍጠሪያ ሆኗል። ኢትዮጵያ የኢኮኖሚ መሰረትዋና አብዛኛው ህዝቡዋ የሚተዳደርበት ሁኖ ሳለ የእርሻ መሬቶች ለውጪ መንግስታትና ግለሰቦች እየተቸበቸቡ ነው። ይህ ደግሞ ኢትዮጵያውያንን ዛሬ መሬት አልባ ነገ ደግሞ አገር አልባ  ያደርጋቸዋል።
የዛሬዎቹ መሪ ተብዬዎች መሬትን መያዝ ሀገርን መቆጣጠር ነው ብለውም ነው መሬት የመንግስት ነው የሚሉት። አዎን ዛሬ መሬት የትግራይ ማፊያዎች ሀብት ነው። ያሻቸውን ለማድረግ የያዙት ታንክና ላውንቸር መብት አጎናጽፎአቸዋል። የተቀረው ኢትዮጵያዊ መሬትም መብትም የለውም! ሌላ ቀርቶ ነገና ከነገወዲያ ጤፍ፣ ስንዴና ገብስም የትላልቅ ‘ምርጥ ዘር’ አምራቾች ሸቀጥ እንጂ ለዘመናት መሬቱንና የሰብሉን ዘር ሲንከባከብ የኖረው ገበሬው ሀብት አይሆኑም። ገበሬው የዘርና ማዳበርያ ዋጋ መክፈል እያቃተው መሬቱን ጥሎ ለማኝና ስደተኛ እንዲሆን እያደረጉት ነው። ይህን አደገኛ አኪያሄድ አሁን ካልገደብነው ኢትዮጵያ የምትባል አገር መኖሩዋ አጠራጣሪ ይሆናል። ይህም ባይሆን እንኩዋን ህዝባችን በገዛ ሀገሩ ለጥቂት የውጭና የውስጥ ዘራፊ ባለሃብቶች ጪሰኛ ይሆናል። ወያኔዎች ያለመታከት ለዚህ መከራ እያሰናዱን ነው እኛም ዛሬ ለነሱ ደባ ተመቻችተንላቸው ለዘመናት በጎሳ በቁዋንቁዋም ይሁን በሀይማኖት ሳንለያይ አብረን መኖራችንን ችላ በማለት በጎጥ አንሰን  በመንደርም እየተከፋፈልን  አገርም ማንነትም ለሚያሳጡን አረመኔዎች በራችንን በርግደን እንዲያምሱን ልንፈቅድ አይገባም።
ዛሬ በራሱና በወገኖቹ ላይ በሚደርሰው ሰቆቃ በማዘን “ራሴን ጠላሁ” “በኢትዮጵያዊነቴ አፈርኩ” የሚለው የተቆጣ ሕዝብ ብዙ ነው። ይህን ቁጣውንና ዱላውን ለሰቆቃው ምንጭ በሆነው ወያኔ ላይ እንዳያሳርፍ እነ ስብሃትና በረከት ስምኦን ጸቡን በአማራና ኦሮሞ፣ በክርስትያንና ሙስሊም ወ.ዘ.ተ. መካከል ለማስቀረትና ለኛው የእልቂት ድግስ መደገስ ከጀመሩ ብዙ ቆዩ። ያለመንግስትና ያለፖሊስ ተከባብሮ የመኖር ድንቅ ባህልን ያዳበረውን ሕዝብ ዛሬ አናቁረውት ሌብነት ቅጥፈትና ዘረፋ የብልጥ መንገድ እንደሆነ እየሰበኩ ወደ ንቅዘት የሚመሩት እነዚሁ የወያኔ ወሮበሎች ናቸው። የማይሞላ ከርስና ባዶ ጭንቅላት ያላቸው የየብሄረሰቡ ተወካይ ተብዬዎች ደግሞ አንደ ተወጠረ ከበሮ አለቆቻቸው ትንሽ ኮርኮም ወይም ኮርኮር  ሲያደርጉዋቸው ይጮሀሉ። በጎሳና ሀይማኖት ህዝባችን አይነጣጠልም  ያልነው እውነት እንዲሆን እርስ በራሳችን እንዳንፋጅ ሁላችንም የወያኔን የጥላቻ ቅስቀሳ ልማክሰም የድርሻችንን የምናደርግበት  ጊዜ ዛሬ ነው። ይሄ አያገባኝም ወይም አይደርስብኝም ማለት ከሌሎች ተሞክሮ አለመማር  ይሆናል።
ሩዋንዳውያን አንድ ሚሊየን ያህል ወገኖቻቸው በግፍ ከተፈጁ በሁዋላ በህልማችንም በእውናችንም ጉዋደኛ ለጉዋደኛ ጎረቤት ለጎረቤት እየተራረድን እንዲህ ያለ ክፋት እኛው በኛው ላይ እንፈጸማለን ብለን አናስብም ነበር ሲሉ መስማት የተለመደ ነው። ከበርካታ አመታት በሁዋላ በሕዝብዋ ላይ የተፈጸመው ጭፍጨፋ አሁንም ድረስ ድባቡ አልጠፋም። አሁንም ድረስ እያስታወሱ የሚያለቅሱ አሉ። በዚሁ ግፍ ምክንያት በርካቶች አይምሮአቸውንም ስተዋል። በቁንጅናዋ ተማርኮ በጸባይዋ ተመስጦ አፍቅሮ ያገባትን ሚስቱንና የልጆቹን እናት የጥላቻ ቅስቀሳ ሰለባ በመሆን በቆንጨራ ጨፍጭፎ እንዲገድል የተደረገ ሰው በህይወት ቢኖርም ሰው መሆን አይችልም። ሺህ ይቅርታ ሺህ ሱባዔ ሺህ ቅጣት ያንን ጤና መልሶ ሊሰጠው አይችልም። የጥላቻውን መርዝ መጀመሪያ የረጩትና እሳቱን ያራገቡት ግን ለመግዛት እንዲመቻቸው አንዱን ከሌላው አሳንሰው እርስበርስ እንዲጠላላ በማድረግ የኖሩት ቅኝ ገዢዎቹ ናቸው። ከነጻነት  በሁዋላም ጎረቤት በጎረቤቱ ላይ በጥላቻ እንዲነሳሳና ያ ሁሉ እልቂት እንዲፈጸም እጃቸው አለበት የሚባሉት መስቀል ይዘው ክርስትና ሰባኪ ነን የሚሉ ነጮች መሆናቸው ይነገራል።
ኤርትራ “በነጻ አውጪዎቹ” ስትያዝ ለብዙ አመታት እዚያው ኑሮ መስርተው ሃብት አፍርተው የነበሩ ኢትዮጵያውያን “አያት ቅድም አያቶቻችሁ ከዚህ አይደሉም” እየተባሉ በጎሳ ጥላቻ ቤተሰባቸው እንዲፈርስ ተደርጎ ባዶ እጃቸውን በባዶ እግር እንዲባረሩ ወደባህርም እንዲገፉ የተደርጉትን ልናስብ ይገባል። ከመሀል አገርም ከሌላ ብሄረሰብ ተወላጆች ጋር ተጋብተው ይኖሩ የነበሩ ኤርትራውያን እራሱ ኤርትራው በሆነው በመለሰ ዜናዊ “የአይናቸው ቀለም ካላማረን እናባርራልን” የሚል የ እብሪት ፖለቲካ ቤተሰባቸውንና ንብረታቸውን በትነው ከሀገር እንዲወጡ እንደተደርጉ  ልናስታውስ ይገባል። ዛሬም ከየቦታው የሚፈናቀሉት ወገኖቻችንን  ቁጣ ልናስብና ይህ ቁጣም ወዴት ሊያመራ እንደሚችል ማሰቡ ከሚጠብቀን አደጋ እንድንጠነቀቅ ያመቻቻል።
አማራው ከኦሮሞው ቢጣላ ገላጋይ ሆነን እንቆማለን የሚሉት የትግራይ ተገንጣይ ቡድን አባላትና ደላሎቻቸው ሕዝብን ከሕዝብ ለማናከስ ደፋ ቀና የሚሉት እሳቱ ቢነሳ እነርሱ የሚተርፉ መስሏቸው ነው። የተገፋው የተጨቆነውና በደል በቃኝ የሚለው የኢትዮጵያ ሕዝብ ጠላቱን ለይቶ አውቆ የጥላቻ እሳት እየቆሰቆሱ ያሉትን በተባበረ ክንድ ሊደቁሳቸው እንደሚችል የተገነዘቡ አይመስልም። ለዚህም ነው ሕዝቡ ቁጣውን ወደነዚህ አረመኔዎች ሊያዞርና ሴራቸውን ሊያከሽፍ የሚገባው ዛሬ ነው ጊዜው እየረፈደም ነው የሚል ጥሪ ከየአቅጣጫው የሚስተጋባው። በርካቶች ወደ ጥላቻ ወጥመዳቸው እንዳይገቡ እነዚህን ክፉዎች መንጥሮ ማውጣት ለነገ የማይባል አስቸኩዋይ የህልውና ጥያቄ ነው። መሰረታዊው ልዩነት ሀገር በሚዘርፉ፣ በሚያፈርሱና እልቂት በሚደግሱት ወያኔዎችና በተቀሩት ኢትዮጵያውያን መካከል እንጂ በተለያዩ ብሄረሰቦችና ሃይማኖት ተከታዮች መሀከል አይደለም።
በምዕራቡ ሀገራት በሚሰበክው የመድብለ ፓርቲዎች አስፈላጊነት ምክንያት ኬንያ በርካታ ፓርቲዎች ማቋቋም ባሰበችበት ወቅት ፖለቲከኞቹ መራጮቻቸውን ፍለጋ በየጎጡ መሄዳቸው ያስከተለው ከባድ ቀውስ ዛሬ የሚታወስ ነው። አሜሪካ መድብለ ፓርቲ ብላ አስጨንቃ ከያዘችን ብለው እነዚያው የቀድሞ ፖለቲከኞች ወደየዘመዶቻቸው ሲሄዱ ይህ ሊያስከትል የሚችለውን አደጋ ያገናዘበ አገናዝቦም መፍትሄ የሰጠ አልነበረም። ብዙ ፓርቲዎችም ተፈጠሩ ግን የጎጥ ፓርቲዎች ሆኑ። ይህን በመከተልም አሰቃቂ የሆነ አደጋ ሰላማዊ ተብላ በምትታወቀው አገር ተከሰተ። የአንድ ሀገር ልጆች መሆናቸውን ከመቅጽበት ዘንገተው ኩኩዩ ሉዎ እየተባባሉ በገጀራና በቀስት እርስበርስ ይገዳደሉ ጀመር። ኬንያውያንም እኛ ሰላም ወዳዶችና የጎሳ ፖለቲካ ወደ ጽንፍ የማይወስደን ነን  የሚል ጽኑ እምነት የነበራችው ቢሆኑም የጥላቻው ቅስቀሳ ለጊዜያው የፖለቲካ ጥቅም ከተለኮሰ በሁዋላ በሀገራችን እናያለን ብለው ያልገመቱት የጥላቻ ግድያ ሲፈጸም ለመመልከትና ተሳታፊም ለመሆን ተገደዱ። ። የረገፉት ረገፉ የተፈናቀሉትና ከሞት የተረፉት ግን ዳግም የሰላም እንቅልፍ አይኖራቸውም። ኬንያ የበርካታ የውጭ መንገስታትና ድርጅቶች የፖለቲካና የኢኮኖሚ ጥቅም የሚያገኙባት ሀገር በምሆኑዋ ዓለም ትኩረት ሰጥቶት እንደ ኮፊ አናን ያሉ መፍትሄ አፈላላጊዎች ሁሉ ተረባርበው እሳቱን ለጊዜውም ቢሆን አበረዱት።
የኛዋ ኢትዮጵያ ግን እኛው ካላዳንናት   በእሳቱ ላይ ነዳጅ የሚጨምር እንጂ እሳት የሚያበርድላት ብዙ እንደማይኖር ልብ ልንል ይገባል። ወራሪን በማሸነፍ የሚገኝ ነፃነት የሚያስከፍለውን መስዋትነት በኩራት ልንሸከም የሚገባን እኛው ኢትዮጵያውያን ነን። አዋሳኝ አገሮችም በአብዛኛው ለኛ መዳከምና መበታተን ተግተው የሚሰሩ ናቸው። የጎጠኞችና የባንዳዎች ብቸኛ ሕልም ደግሞ ምንም ያክል ትሁን ስልጣንና ሀብት ማጋበስ ብቻ ነው። በጎጥ የጀመረ ፀብ በእንጭጩ ካለተቀጨ መንደርና ቤተሰብ ድረስ ይዘልቃል። የትግራይ ተገንጣይ ቡድን ሚሊየኖችን አስፈጅቶ ስልጣኑና ሀብቱ ግን የተገደበው በጥቂት ቤተሰብና መንደር ላይ መሆኑ ሩቅ የማይወስድ ምሳሌ ነው። የትግራይ ሕዝብ በጥቅሉ ከሌላው በተለየ ደስተኛ እንዳልሆነ ማየት ትምህርት ነው። በመከባበርና በመተሳሰብ ለልጆቻችን ለልጅ ልጆቻችን ህልውናና ነፃነት ስንል የአቅማችንን እንስራ ኢትዮጵያንም እናድናት።
በጎጠኞች መርዘኛ ሴራ ኢትዮጵያዊነት አይረታም!http://ecadforum.com

Thursday, March 20, 2014

የኢትዮጵያ ተተኪ ሴቶች ትውልድ መነሳሳት! (ፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም)

“ከዚህ በኋላ ትዕግስታችን ተሟጧል!”
ሰማያዊ ፓርቲ በኢትዮጵያ እንደገና ወኔ የተሞላበት የትግል መንፈሱን በማደስ ጥንካሬውን አሳየ !
Semayawi party female youth activists released
እ.ኤ.አ ማርች 9/2014 የተከበረውን ዓለም አቀፍ የሴቶች በዓል ምክንያት በማድረግ በአዲስ አበባ ከተማ ተዘጋጀቶ በነበረው የ5 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ የሰማያዊ ፓርቲ ወጣት ሴቶችም ተሳትፎ አድርገው ነበር፡፡ ከዴሞክራሲያዊ ምርጫ ባፈነገጠ መልኩ በኃይል በስልጣን ኮርቻ ላይ ተፈናጥጠው ስልጣንን የሙጥኝ በማለት ከህግ አግባብ ውጭ በህዝብ ላይ ደባ በመፈጸም ላይ የሚገኙትን የሰብአዊ መብት ደፍጣጮች ዕኩይ ምግባር የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ እንዲገነዘበው በማሰብ ወጣት ሴቶቹ እውነታውን ያለምንም መሸፋፈን በማጋለጥ እምቢ አሻፈረኝ በማለት ተቃውሟቸውን ለዓለም በይፋ አሰምተዋል፡፡ እንዲህ በማለትም ተቃውሟቸውን አጠናክረዋል፣
“ከዚህ በኋላ ትዕግስታችን ተሟጧል! ተርበናል! ነጻነት እንፈልጋለን! ነጻነት እንፈልጋለነ! እስክንድር ይፈታ! አንዷለም ይፈታ! አቡባከር ይፈታ! ርዕዮት ትፈታ! የፖለቲካ እስረኞች በሙሉ ይፈቱ! ፍትህ እንፈልጋለን! ነጻነት! ነጻነት! ነጻነት! አትከፋፍሉን! ኢትዮጵያ አንድ ነች! አንድ ኢትዮጵያ! ከዚህ በኋላ ትዕግስታችን ተሟጧል! ውኃ ናፈቀን! መብራት ናፈቀን! ተርበናል!…“
ለሰማያዊ ፓርቲ ሴት ወጣት አመራሮች ባርኔጣዬን ዝቅ በማድረግ ከወገቤ ጎንበስ በማለት ያለኝን አድናቆት ልገልጽላቸው እፈልጋለሁ፡፡ በእነርሱ እጅጉን ኮርቻለሁ፡፡ ባለፉት ጥቂት ወራት ሰማያዊ ፓርቲን ለምን እንደደገፍኩ እና በጽናትም ከፓርቲው ጎን ለምን እንደምቆምኩ በርካታ ሰዎች ጥያቄዎችን አቅርበውልኝ ነበር፡፡ የሰማያዊ ፓርቲ ቁጥር አንድ አድናቂ (አንደኛ ቲፎዞ) ለምን እንደሆንኩ ማንም ቢሆን ጥያቄዎች ካሉት/ካሏት ይህንን ቪዲዮ (እዚህ ይጫኑ) እንዲመለከቱት እጋብዛለሁ፣ እናም መልሱን ከእዚያው ያገኙታል፡፡
አረመኔው ገዥ አካል በአሁኑ ጊዜ የኢትዮጵያን ወጣት ሴቶች እና ወንዶች በዱላ እየደበደበ እና እንደ እባብ እየቀጠቀጠ ሁሉንም የጭቆና ዓይነቶች በእነርሱ ላይ እየተገበረ ባለበት ሁኔታ ከዳር ቆሜ ለመመልከት ህሊናዬ ሊፈቅድልኝ አይችልም፡፡ የመናገር መብታቸውን ተጠቅመው ሀሳባቸውን ለመግለጽ በመሞካራቸው ምክንያት ብቻ የኢትዮጵያ ወጣቶች ሲታሰሩ፣ ሲደበደቡ፣ ሲሰቃዩ እና ግፍ ሲፈጸምባቸው በዝምታ አልመለከትም፡፡ በወጣቶቹ ላይ የሚፈጸመውን ግፍ እና ስቅይት የእነርሱ ድምጽ በመሆን ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ እናገራለሁ፡፡
ወጣት ሴቶቹ ተቃውሟቸውን የገለጹት በሰላማዊ መንገድ ነው፡፡ በሰላማዊ መንገድ ተቃውሟቸውን በማሰማታቸውም በጨካኙ የገዥ አካል ማሰቃየት ተፈጽሞባቸዋል፡፡ በሰላማዊ እና ከአመጽ በጸዳ መልኩ በአገሪቱ ውስጥ ለውጥ ለማምጣት ሲሉ ነው በአሁኑ ጊዜ የሰማያዊ ፓርቲ አባላት በመሰቃየት ላይ የሚገኙት፡፡ የሰማያዊ ፓርቲ ሴት ወጣት አመራሮች እና አባላት እንደማንኛውም ሰው ሁሉ የ5 ኪ/ሜ ሩጫውን ተቀላቀሉ፡፡ በሰላማዊ መንገድ እሮጡ እና ከማጠናቀቂያ ቦታው ደረሱ፡፡ ምንም ዓይነት ህግ አልጣሱም፡፡ አንድም ጠጠር አልወረወሩም፡፡ በማንም ላይ ጥቃት አልፈጸሙም፡፡ ምንም ዓይነት ሁከትን በሚያመጡ ተግባራት ላይ አልተሳተፉም፡፡ ከአንድ ሺህ በላይ ሯጮች በተሳተፉበት በዚያ ሩጫ ላይ የሰማያዊ ፓርቲ ሴት ወጣት አመራሮች እና አባላት በመሳተፋቸው (ወይም በሌላ ምክንያት) በአንድም ሰው ላይ ጉዳት አልደረሰም፡፡ ቅንጣት ያህል ንብረት ላይ ጉዳት አልተፈጸመም፡፡ አንድም ባለስልጣን ማስፈራሪያ አልደረሰበትም ወይም ደግሞ የጥቃት ሰለባ አልሆነም፡፡ የሰማያዊ ፓርቲ ሴቶች ምንም ዓይነት የዘለፋ ቃላት እንኳ አልተጠቀሙም፡፡ ሁሉምን ነገር በሰላማዊ መንገድ፣ ሞገስን በተላበሰበ መልኩ እና በሚያስደምም ሁኔታ ነው ያከናወኑት፡፡ እነዚያ ጀግና ወጣት ሴቶች የምርጥ ተደናቂነት ተምሳሌት ቀንዲል ናቸው! በእነዚህ ወጣቶች እጅግ ኮርቻለሁ እናም ባርኔጣዬን ዝቅ በማድረግ አድናቆቴን ልገልጽላቸው እፈልጋለሁ፡፡
በዕለቱ የተከበረውን በዓል ኃላፊነት በመውሰድ ያዘጋጀው የገዥው አካል የሴቶች፣ የህጻናት እና ወጣቶች ሚኒስቴር ነበር፡፡ የገዥው አካል የዕለቱ መፈክር “የምርጥ ሴቶች የመጀመሪያው ዙር የ5 ኪ/ሜ ሩጫ“ የሚል ነበር (ምን ለማለት እንደተፈለገ ግልጽ ባይሆንም)፡፡ ገዥው አካል ዕለቱ ከ10,000 በላይ ሴቶችን እና ልጃገረዶችን ያሳትፋል በማለት ዲስኩር አድርጎ ነበር፡፡ ገዥው አካል በበዓሉ ዕለት ሴቶች እንዲሳተፉ በስፋት የጥሪ ማሳሰቢያ ሲያደርግ ጠንካራዎቹ የሰማያዊ ፓርቲ ሴት ወጣት አመራሮች ማሳሰቢያውን ሊሰሙት እንደሚችሉ እረስቶት ኖሯል፡፡ መንፈሰ ጠንካራዎቹ ወጣት ሴቶች ግን ማድረግ ያለባቸውን ነገር በሚያስደምም ሁኔታ አደረጉት፡፡ ወጣት ሴቶቹ ለገዥው አካል ፕሮፓጋንዳ ፍጆታ ሳይሆን ብጫ ካናቴራ በመልበስ ተልዕኳቸውን ሲፈጽሙ ታይተዋል፡፡ እዚያ የተገኙት ለመሮጥ ነበር፣ ለነጻነታቸው ለመሮጥ፣ ለኢትዮጵያ ብሄራዊ አንድነት ለመሮጥ፣ የኢትዮጵያ እስረኞች እንዲፈቱ ለመሮጥ፣ በመሰቃየት ላይ ላለው እና ተስፋ ለራቀው ህዝብ ትኩረት በመሳብ  ለመሮጥ፡፡ ወጣቶቹ የሰማያዊ ፓርቲ ሴቶች አረመኒያዊ እና ጨካኝ እየተባለ በሚታወቀው ገዥው አካል ፊት ደፋርነታቸውን ማሳየት መቻላቸው ብቻ አይደለም አስደናቂ የሚሆነው ሆኖም ግን የእራሳቸውን የብልህነት ፈጠራ በመጠቀም የስርዓቱን ዕኩይ ምግባር በማጋለጣቸው ጭምር እንጅ፡፡
የአምስት ኪሎ ሜትሩ ሩጫ ከተጠናቀቀ በኋላ ሰባት የሰማያዊ ፓርቲ ወጣት ሴቶች በቁጥጥር ስር ውለዋል፣ ተደብድበዋል እንዲሁም ለእስር ተዳርገዋል፡፡ የሰብአዊ መብት እረገጣው ሰለባ ከሆኑት ውስጥ፡ ሜሮን ዓለማየሁ፣ ምኞቴ መኮንን፣ መታሰቢያ ተክሌ፣ ወይኒ ንጉሴ፣ ንግስት ወንድይፍራው፣ ወይንሸት ሞላ፣ እና እመቤት ግርማ ይገኙበታል፡፡ በሰማያዊ ፓርቲ በከፍተኛ የስልጣን እርከን ላይ የሚገኙ  ጌታነህ ባልቻ (የድርጅተ ጉዳይ ኃላፊ)፣ ብርሀኑ ተክለያሬድ (የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ) እና አቤል ኤፍሬም (የህዝብ ግንኙነት ኮሚቴ አባል) የተባሉ ሌሎች ሶስት ወጣት ወንዶች ደግሞ እስረኛ ሴቶች ያሉበትን ሁኔታ ለመጠየቅ  በሄዱ ጊዜ በቁጥጥር ስር ውለው እነርሱም ለእስር ተዳርገዋል፡፡
የጣይቱ እና የምኒልክ ልጆች በይስሙላው/በዝንጀሮዎች (ካንጋሩ ኮርት) ፍርድ ቤት፣
በኢትዮጵያ ያለው ገዥ አካል የይስሙላ ፍርድ ቤት ስርዓት በአገሪቷ ዘርግቶ በመተግበር ላይ ይገኛል በማለት ሁልጊዜ ስናገረው የቆየሁት ጉዳይ ነው፡፡ በሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች ላይ የተመሰረቱት “ክሶች” የገዥው አካል የይስሙላ ፍርድ ቤቶች እንዴት ባለ ሁኔታ እየተካሄዱ እንዳሉ ከምንም ጥርጣሬ በላይ በግልጽ ያመላክታሉ፡፡ በሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች ላይ የተመሰረቱት ክሶች በባዶው የትወና መድረክ ላይ ብቻ የሚከናወኑ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ የይስሙላው ፍርድ ቤት  እ.ኤ.አ ማርች 14/2014 ያደረገው የሁለተኛው ቀን “የችሎት” ትወና በሳሙኤል በኬት፣ ኢጀን ኔስኮ፣ ጂን ገነት ወይም ካፍካ ላይ የተደረገ ያለቀለት የትያትር ትወና ይመስል ነበር፡፡ የህጋዊነት ትወናው በምግባር የለሾች፣ በስም የለሾች፣ የማስተዋል ብቃት በሌላቸው፣ በህሊና የለሾች፣ በሀሳብ የለሽ ደነዞች፣ታማኝነት በሌላቸው ፖለቲከኞች እና ዋናው ተግባራቸው ህዝቡን ማሰቃየትን እና መከራ ማሳየትን እንደመርሀ የሚከተሉ አስመሳዮች በግልጽ በማይታይ መልኩ የሚጦዝ የውሸት የህጋዊነት ሽፋንን ተላብሶ እየተተገበረ ያለ ኃላፊት የጎደለው እና የተዋረደ የመድረክ ተውኔት ነው፡፡ ፍትህ ፊት የሌላት እና ቅርጿ የተበላሸ የይስሙላ ስርዓት ዘርግታ ትገኛለች፡፡ ፍትህ በሚያስገርም ሁኔታ በመደምሰሷ ምክንያት አካል የላትም፡፡ በኢትዮጵያ የፍትህ ፊት እና አካል በይስሙላው ፍርድ ቤት በርቀት በቁጥጥር ስልት መጠቀሚያ መሳሪያ ተይዞ የሚመራ እና በጌቶቹ ትዕዛዝ እንዲያደርግ የተሰጠውን ብቻ ያለምንም ኃፍረት ተቀብሎ እንደበቀቀን የሚደግም የሮቦት ዳኛ (አንደየተሞላ አሻንጉሊት) የተሰማራበት ሆኗል፡፡ የፍትህ አካሉ በዘራፊዎች ቁጥጥር  ስር ዉሎአል፡፡
በ “ችሎቱ” ክፍል እንደ አንድ ተመልካች ዘገባ ከሆነ “የማታ” በሚል ስም የሚታወቅ “የፖሊስ መርማሪ” የሰማያዊ ፓርቲ ሴቶች የጣይቱ ልጆች ነን (የ19ኛው ክፍለ ዘመን የኢትዮጵያ ንግስት የነበሩት) እና የእምዬ ምኒልክ ልጆች ነን (በ19ኛው ክፍለ ዘመን የኢትዮጵያ ንጉስ እና የንግስት ጣይቱ ባለቤት የነበሩት) በማለት በአደባባይ በመጮህ በሽብር ተግባር ላይ ተዘፍቀው ታይተዋል በማለት የምስክርነት ቃሉን ሰጥቷል፡፡ “መርማሪው” በተጨማሪም ተከሳሾቹ እየተራቡ ያሉ መሆናቸውን እና የፖለቲካ እስረኞች እንዲፈቱ እንዲሁም በእስር ላይ የሚገኙት ፖለቲከኞች እና ጋዜጠኞች ማለትም ርዕዮት፣ እስክንድር፣ አንዷለም እንዲሁም ሌሎች እንዲፈቱ” እያሉ በአደባባይ ጩኸት እያሰሙ ነበር ብሏል፡፡ እንግዲህ ይኸ ነው በሰማያዊ ፓርቲ ሴቶች ተፈጸመ የተባለው “የሽብር ተግባር” ይዘት፡፡
የችሎት ስነስርዓቱ ከታቀደለት በአንድ ሰዓት ዘግይቶ ነው የተጀመረው፣ ምክንያቱም የሰማያዊ ፓርቲ ሴቶች በሰልፉ ላይ ለብሰዋቸው የነበሩትን ካናቴራዎች ወደ ችሎቱ ሲቀርቡ እንዲቀይሯቸው ቢጠየቁም ለመቀየር ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ነበር፡፡ ፖሊሱ እስረኞቹን ከነካናቴራቸው ወደ ፍርድ ቤቱ እንዲቀርቡ መፍቀድ የፖለቲካ እምቢተኝነትን አምኖ እንደመቀበል ያስቆጥራል የሚል እምነት አደረበት፡፡ እንደ ዘገባው ከሆነ ሴቶቹ ወደ “ፍርድ ቤቱ” ጉዞ ከመጀመራቸው በፊት የለበሷቸውን ካናቴራዎቻቸውን በማስገደድ እንዲቀይሩ ለማድረግ ፖሊ ሁከት ፈጥሮ እንደነበሩ ታውቋል፡፡ የሰማያዊ ፓርቲ ወጣት ሴቶች እስከሚወሰዱ ድረስ በተያዙበት ቦታ እንዲቆዩ ተደርገዋል፡፡ “የፍርድ ቤቱ” ክፍል በተመልካች ተጨናንቋል፣ የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችም በሙሉ ተገኝተው ነበር፡፡
የፌዴራል አቃቤ ህግ ጉዳዩን ለመመርመር እና መረጃ ለማሰባሰብ ተጨማሪ የ14 ቀናት ጊዜ እንዲሰጠው ሴት እስረኞችም በእስር እንዲቆዩ ጠየቀ፡፡ (በቁጥጥር ስር የማዋል ልምድ እና ተጠርጣሪን በእስር ቤት አውሎ ለጥፋተኝነት መረጃዎችን ለመፈለግ መሞከር የገዥው አካል የይስሙላው ፍርድ ቤት አሰራር ዋናው መለያ ባህሪው ነው፡፡ አንድ ተጠርጣሪ ፍርድ ቤት ከመቅረቡ በፊት የሚደረገው አሳፋሪ ዘዴ በእያንዳንዱ ከፍተኛ የወንጀል ጉዳይ ከሁለት ደርዘን ወይም ከዚያ በላይ በሚሆኑ በቀድሞዎቹ ባለስልጣኖች እና ባለፈው ዓመት ደግሞ በንግዱ ማህበረሰብ አባላት ላይ ሙስና በሚል ሰበብ የተደረገው እስራት ሲታይ ገዥው አካል ካለፉት አስርት ዓመታት በላይ ሲፈጽመው የቆየ ተግባር መሆኑን ነው፡፡ አቃቤ ህጉ እስከ አሁንም ድረስ ለሙስናው መረጃ ፍለጋ በሚል ሰበብ ጊዜ እየነጎደ በሄደ ቁጥር እነርሱ በእስር ቤት ተረስተዋል፣ ገዥው አካል ጉዳዩን ለሁለት ዓመታት ያህል ምርመራ እየተካሄደበት ነው በማለት በይፋ የገለጸ ቢሆንም)፡፡
የይስሙላ አቃቤ ህጉ ለሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች የዋስትና መብት መሰጠት እንደሌለበት ተከራክሯል፣ ምክንያቱም “ዋስትናው ከተሰጠ አሁን በፖሊስ ቁጥጥር ስር ያሉት ታሳሪዎች መረጃዎችን ያጠፋሉ፣ እናም ምስክሮች የምስክርነት ቃላቸውን እንዳይሰጡ በማንገራገር እና በማስፈራራት እንዳይመሰክሩ ሊያደርጉ ይችላሉ” ብለዋል፡፡ የሰማያዊ ፓርቲ መከላከያ ጠበቃ አቶ ዓለሙ ጎቤቦ (በእስር ቤት የምትገኘው እና በዓለም አቀፍ ደረጃ ዕውቅናን ያተረፈችው ርዕዮት ዓለሙ አባት) ጉዳዩ የፖለቲካ ባህሪ ያለው ስለሆነ ልጆቹ የዋስትና መብታቸው ተጠብቆ ከውጭ ሆነው እንዲከራከሩ እንዲደረግ በማለት የክርክር ጭብጣቸውን አቅርበዋል፡፡ ቀጥለውም እንደ ህጉ ከሆነ ደንበኞቼ የዋስትና መብት እንዲያገኙ ይፈቅዳል፣ እናም ይህንን ላለማድረግ እየተከናወነ ያለው የዳኞቹ ተቃውሞ ተጠርጣሪዎቹን በእስር ቤት ለማማቀቅ የተደረገ ደባ ነው ብለዋል፡፡ “ዳኛው” የዋስትና ጥያቄውን አልተቀበሉትም፣ እናም የዳኝነት ሂደቱን ቀጠሉ፡፡ (ባለፉት በርካታ ከፍተኛ የሆኑ የፍርድ ቤት ጉዳዮች የፍርድ ሂደት ላይ እ.ኤ.አ የ2006 የቅንጅት ፓርቲ አመራሮችን “የፍርድ ሂደት” ጉዳይ ጨምሮ ገዥው አካል ምስክሮችን በማስፈራራት፣ ጉቦ በመስጠት፣ በሙስና አማልሎ ተጽዕኖ በማሳደር እና ከህግ አግባብ ውጭ በሆነ መልኩ ቃለመሃላን በመጣስ የውሸት የምስክርነት ቃል እንዲሰጡ በማድረግ ዕኩይ ምግባር ላይ ተዘፍቆ ይገኛል)፡፡
እንደ ፍርድ ቤት ተመልካች ታዛቢዎች ከሆነ የሰማያዊ ፓርቲ ሴቶች በእስር ቤቱ ውስጥ በቁጥጥር ስር ሆነው እያለ ከህግ አግባብ ውጭ በፖሊስ እና በደህንነት ኃላፊዎች አካላዊ ጉዳት እንደደረሰባቸው እንዲሁም የማስፈራራት ሰለባ እንዲሆኑ ጥረት እየተደረገ እንደሆነ ለይስሙላው ፍርድ ቤት ተናግረዋል፡፡ በሌሎች የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች ላይ ቅጥረኛ እና ሰላይ እንዲሆኑ ብዙ ገንዘብ ቀርቦላቸዋል፡፡ ከተከሳሾቹ መካከል ትዕግስት ወንድይፍራው የተባለችው ባለፈው እኩለ ሌሊት ላይ ሶስት ወንድ ፖሊሶች እርሷ ወደታሰረችበት ክፍል መጥተው እንድትወጣ ትዕዛዝ እንደሰጧት “ለፍርድ ቤቱ” ተናግራለች፡፡ ከኃላፊዎች መካከል አንደኛው ዱላ በማንሳት በማወዛወዝ ካልተባበረች በስተቀር እስክትሞት ድረስ እንደሚደበድቧት ማስፈራራታቸውን ገልጻለች፡፡ ሌሎችም ሴቶች ተመሳሳይ የማስፈራሪያ ዛቻ እንደተፈጸመባቸው ተናግረዋል፡፡ ፖሊስ ሴቶቹ በሰማያዊ ፓርቲ ላይ የሚያደርጉትን ንቁ የአባልነት ተሳትፎ እና ጓዳዊ የትግል መንፈስ እንዲተው እና ከድጊታቸው እንዲታቀቡ በመደብደብ እንዳዋረዳቸው እና እንዳስፈራራቸው ያላቸውን ምሬት ገልጸዋል፡፡ በተመልካቾች ዕይታ “ብቃት የለሽ” ተብሎ የተፈረጀው የዕለቱ የችሎት ዳኛ ፖሊስ ምርመራውን አጠናቅቆ እ.ኤ.አ ለመጋቢት 18/2014 እንዲቀርብ ትዕዛዝ በመስጠት አሰናብቷል፡፡
በይስሙላው ፍርድ ቤት ያለውን ኃይል መገዳደር፣
የሰማያዊ ፓርቲ ሴቶችን በቁጥጥር ስር የማዋል እና የፍርድ ሂደታቸው እንዲታይ ማድረግ እ.ኤ.አ በ2015 ይካሄዳል ተብሎ በሚታሰበው አገር አቀፋዊ ምርጫ ሰማያዊ ፓርቲ እንዳይሳተፍ እና ለመዝጋት በደጋኑ የተተኮሰ የመጀመሪያው ቀስት ነው፡፡ ገዥው አካል ለሰማያዊ ፓርቲ የሚያስተላልፈው መልዕክት ግልጽ እና ግድፈት ሊደረግበት የማይችል ሀቅ ነው፡፡ ይህም ሁኔታ በአንክሮ ሲታይ በቅርቡ ባረፉት በአቶ መለስ ዜናዊ የተጻፈው የባለ ሶስት ድርጊት የረዥም ጊዜ ተውኔት ተከታይ ነው፡፡ እነዚህ የተውኔት ድርጊቶችም እንደሚከተለው ቀርበዋል፡፡ ድርጊት አንድ፡ “ምርጫው” ከመድረሱ በፊት የሰማያዊ ፓርቲ, አመራሮችን እና አባላትን የይስሙላውን ፍርድ ቤቶች በመጠቀም ማሰቃየት፣ ማስፈራራት፣ ሽባ እና አቅመቢስ ማድረግ፡፡ በዚያ መንገድ ሌላ ተጨማሪ የኃይል እርምጃዎች ቢወሰዱ በህዝቡ ዘንድ የተለመደው አካሄድ እንጅ የበቀል እርምጃ አይደለም የሚል እንደምታ እንዲኖር ከመሻት የመነጨ ነው፡፡ ድርጊት ሁለት፡ ምርጫው ከመድረሱ ጥቂት ወራት በፊት የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችን እና አባላትን ሰብስቦ በእስር ቤት ማጎር፡፡  ይሄም የይስሙላውን ፍርድ ቤት አንደውነት የፍርድ ሸንጎ የሚሰራ ለማስመሰል ነው፡፡ ድርጊት ሶስት፡ ከምርጫ በኋላ እ.ኤ.አ በ2005  (1997 ምርጫ) የተደረገውን  ጭፍጨፋ ድርጊት መድገም ነው፡፡!
የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችን እና አባላትን የህግ ሂደት እና ጥቃት በተመለከተ ሁለት አማራጮች አሉ፡፡ 1ኛ) በይስሙላው ፍርድ ቤት የፍርድ ሂደት ላይ ተስፋ በመቁረጥ እራስን መነቅነቅ እና በመሰላቸት ጥሎ መሄድ 2ኛ) እንደ ኪልኬኔ አገር ድመቶች ከይስሙላው ፍርድ ቤት ጋር ጎሮሮ ለጉሮሮ መተናነቅ እና የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችን እና አባላትን መብት ማስከበር፡፡
ገዥው አካል ኢትጵያውያን እና ሌሎች በይስሙላው ፍርድ ቤት የውሸት ማስመሰያ ምክንያት እራሳቸውን በመነቅነቅ ሁሉንም ነገር ይተውታል ወይም ደግሞ ትችት በመስጠት ብቻ ጥለው ይሄዳሉ የሚል እሳቤ ላይ የተንጠለጠለ ነው፡፡ ገዥው አካል በጊዜ ሂደት የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችም እንደ እስክንድር ነጋ፣ ርዕዮት ዓለሙ፣ አንዷለም አራጌ፣ አቡባከር አህመድ እና ሌሎችም  በእስር ቤት ታጉረው “ይረሳሉ” የሚል ስሌት አለው፡፡ ገዥው አካል የይስሙላው የፍርድ ቤት ማስፈራሪያ ዘመቻ በከፍተኛ ውጤታማነት እና ብቃት ላይ ተመስርቶ የሚቀጥል ላለመሆኑ ትንሽም እንኳ ቢሆን ጥርጣሬ የለዉም፡፡
የሰላማዊ ትግል ዋና ዓላማው የጨቋኙን አካል ተቋማት እና ህጎች በመጠቀም በጨቋኙ አካል ላይ ትግሉን በሰላማዊ መልኩ በማፋፋም መቀጠል ነው፡፡ በአጠቃላይ መልኩ ሲታይ ከጉዳዩ ጋር ተያያዥነት ያለው ምንም ዓይነት የተፈጸመ ስህተት የለም፡፡ በገዥው አካል የይስሙላው ፍርድ ቤቶች ዘንድ የፍትህን ጥላ እንኳ ማግኘት እንደማይችል ማንም መገመት ይችላል፡፡ ማንም ቢሆን በውሸት እምነት ላይ በተመሰረተው የይስሙላው ፍርድ ቤት ፍትህ ሰበብ መሰቃየት የለበትም፡፡ ወደፊት ምን ሊከሰት እንደሚችል በእርግጠኝነት እናውቃለን፡፡ የክስ ሰነዱ ቀደም ሲል ተጽፎ ተዘጋጅቷል፣ በግልጽ ለመናገር ቀደም ሲል የነበረዉን የፖለቲካ ተቃዋሚዎች ክስ ስማቸውን በመለወጥ፣ በማደስ እና ሌሎች ዝርዝር ጉዳዮችን በማካተት የክስ ሰነዶቹ እነዚህን ለመዳኘት በስራ ላይ ይውላሉ (በግልጽ አባባል ለማጥቂያነት ይውላሉ)፡፡
ያንን ትያትር ቀደም ሲል አይተነዋል፡፡ ክስ የቀረበባቸው የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች እና አባላት በየጥቂት ሳምንታት ልዩነት ከማጎሪያ እስር ቤቶች ወደ የይስሙላው ፍርድ ቤት እንዲመላለሱ ይደረጋል፡፡ የገዥው አካል አቃቤ ህግ ማስረጃ ለመፈለግ (የሩጫው ዕለት የተጠናቀቀ ስለሆነ እና ሌላ ተጨማሪ ማስረጃ ማግኘት የተሳሳተ እና ውኃ የሚቋጥር ባይሆንም) በሚል ስልት ብዙ የማዘግየት ስራዎችን በመስራት የተለመደውን የገዥውን አካል የበቀልተኝነት የሱስ ጥማት ለማርካት ጥረት ያደርጋል፡፡ የዋስትና መብት ጥያቄዎች ተከልክለዋል፣ ሺህ ጊዜ የሚጠየቁ ቢሆንም፡፡ የሰማያዊ ፓርቲ ሴቶች ይደበደባሉ፣ ህግወጥ አያያዝ ይፈጸምባቸዋል፣ እናም በእስር ቤት የሰብአዊ መብት ድፍጠጣ ይፈጸምባቸዋል፡፡ እርስ በእርሳቸው ላይ መተማመን እንዳይኖርም ጫና ይፈጸምባቸዋል፡፡ ህሊናቸውን እንዲሸጡ ገንዘብ እና ሌላ ሌላም ነገር ይሰጣቸዋል፡፡ የሰማያዊ ፓርቲን ከፍተኛ አመራሮችን እንዲክዱ ላቅ ያለ ዋጋ የሚያወጡ ጌጣጌጦችን ይሰጧቸዋል፡፡ በጓደኞቻቸው፣ በፓርቲ አባላት እና አመራሮች እንዳይጎበኙ ክልከላ ሊጣል ይችላል፡፡ ለብቻ በአንድ ክፍል ውስጥ ሊታሰሩ ይችላሉ፡፡ የህክምና እርዳታ እንዳይደረግላቸው ክልከላ ሊደረግ ይችላል፡፡ በገዥው አካል በተቀጠረ ባለሙያ እንደተገለጸው እነዚህ እስረኞች  “በሚከረፋው እስር ቤት” የገሀነም ህይወት እንዲገፉ ሊደረግ ይችላል፡፡ ይህ ጉዳይ ለብዙ ጊዜ ማለትም እ.ኤ.አ በ2015 እስከሚደረገው አገር አቀፍ “ምርጫ” ድረስ ቀጣይነት ሊኖረው ይችላል፡፡ ዘዴው ቀላል ነው፡ የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችን ሃሳብ ማስቀየስ፣ ማሸማቀቅ፣ ማስፈራራት፣ ከመሰረታዊ ዓላማቸው እንዲርቁ ማድረግ እና በአጠቃላይ መልኩ ደግሞ ምርጫ እየተባለ ከሚጠራው የይስሙላ ምርጫ ተሳትፏቸውን ሽባ ማድረግ ነው፡፡
ገዥው አካል የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችን ያለምንም ውይይት በፍጥነት ወደ እስር ቤት የመውሰዱን ሁኔታ በተመለከተ በእራሱ የይስሙላ ፍርድ ቤቶች ለምን ሊጠየቅ እና ሊሞገት እንደሚገባው አራት አሳማኝ ምክንያቶች አሉ፡፡ በመጀመሪያ የጅምላ ሰብአዊ መብት ረገጣው ተግባራዊ እንዲሆን የሚያግዙት የገዥው አካል ለጋሽ እና አበዳሪ ድርጅቶች (በተለይም የምራብ መንግሥታት) እነርሱ በሚያደርጉት ልገሳ ድርጊት እየተደረገ ያለውን የሰብአዊ መብት ድፍጠጣ በተጨባጭ እንዲያዩት ይገደዳሉ፡፡ ለጋሽ እና አበዳሪ ድርጅቶች በኢትዮጵያ ዴሞክራሲ እንዲስፋፋ እና ሰብአዊ መብት እንዲጠበቅ ደንታ አንደማይሰጣቸው የታወቀ ነው፡፡ ሁለተኛ የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች የይስሙላ የፍርድ ሂደት በእራሱ በይስሙላው ፍርድ ቤት ላይ አንዲፈረጅበት ማድረግ ያስፈለጋል፡፡ ገዥው አካል እራሱ ለይስሙላው የፍርድ ቤት ሂደት መቅረብ አለበት፡፡ ሶስተኛ የይስሙላው ፍርድ ቤት የፍርድ ሂደት ዛሬ በፍትህ ወንበር ላይ ተቀምጠው (እና ሌሎች ከመጋረጃ ጀርባ ተቀምጠው በዳኝት ወንበር ላይ የተሰየሙትን ዳኞች ጣቶች የሚጠመዝዙ) በእራሳቸው ዳኝነት ነገ እንደሚዳኙ በመገንዘብ ከፍተኛ ተቃውሞ መኖር አለበት፡፡ ዛሬ ከህግ አግባብ ውጭ ለመፍረድ በወንበር ላይ የተቀመጡት ሰዎች ከፍትህ ረዥም ክንድ ሊያመልጡ እንደማይችሉ የኑረምበርግ የፍርድ ሂደትን፣ የካምቦዲያ ፍርድ ቤት ልዩ የፍርድ ቤት ሂደትን፣ የሩዋንዳ የዓለም አቀፉን የወንጀለኞች ፍርድ ቤት የፍርድ ሂደትን፣ የደቡብ አፍሪካ የእውነት እና የዕርቅ ኮሚሽንን፣ የቻርለስ ቴለር የዓለም አቀፉን የወንጀለኞች ፍርድ ቤት የፍርድ ሂደትን እና የቦካሳን እና ሌሎች የአገር ውስጥ የፍርድ ሂደቶች ሊያስታውሱ ይገባል፡፡ ሁኔታዎች ሁልጊዜ ይገለባበጣሉ፡፡ ስለ ሁኔታዎች መገለባበጥ ጉዳይ እስቲ ደጋግማችሁ አስቡ፡፡ ሁልጊዜ ይገለባበጣሉ!
ከደቡብ አፍሪካ ታሪክ ብዙ ቁም ነገሮችን ልንማር እንችላለን፡፡ እ.ኤ.አ በ1964 የአፓርታይድ ገዥ አካል የአፍሪካ ኮንግረስ መሪዎችን እና ሌሎች የጸረ አፓርታይድ ተሟጋቾችን ኔልሰን ማንዴላን፣ ዋልተር ሲሱሉ፣ ጎቫን ኢምቤኪ፣ ራይሞንድ ሃላባ፣ አህመድ ካትራዳ፣ ኤሊያስ ሞሶሌዲ እና ቢሊ ኔይር ሰብስቦ በይስሙላው የአፓርታይድ የፍትህ ችሎት ፊት ገተራቸው፡፡ እነዚህ ሰባት አመራሮች እንደ “ጣይቱ ሰባት” የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች ሁሉ በአፓርታይድ የይስሙላ ፍርድ ቤቶች ፍትህን እናገኛለን የሚል እምነት አልነበራቸውም፡፡ ሆኖም ግን መሰረተ ቢስ ክሱን አጥብቀው ተቃውመውታል፡፡ ይህንንም በማድረጋቸው  ለደቡብ አፍሪካ ብቻ ሳይሆን ለጠቅላላው ዓለም ታሪክ ሰርተዋል፡፡ የሰባቱ የጸረ አፓርታይድ መሪዎች የሪቮኒያ የፍርድ ሂደት ለዛሬዋ ደቡብ አፍሪካ ፍትህ መስፈን መሰረትን የጣለ ነው፡፡
አራተኛው እና ምናልባትም በጣም ጠቃሚው ነገር የይስሙላውን ፍርድ ቤት አጥብቀን መዋጋት አስፈላጊ ነው ምክንያቱም በህግ የበላይነት ለሚያምኑ ሁሉ ለህጉ ተገዥ ላልሆኑት ወንጀለኞች የህይወት እና የመተንፈስን ያህል ጠቃሚ መሆናቸውን ሊያስተምሩ የሚችሉበት ብቸኛው መንገድ ነው፡፡ በህግ የበላይነት ላይ እምነት ያላቸው ሰዎች ብቻ ናቸው ስለወንጀለኞች ማስተማር እና መጮህ ያለባቸው፡፡ እራሱ ያወጣቸውን እና ያጸደቃቸውን ህጎች የሚደፈጥጥ ወሮበላ መንግስት በእራሱ እና በህግ የበላይነት ላይ ንቀትን የሚፈለፍል ነው፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ  የህግ የበላይነትን ለመያዝ እና ለመንከባከብ ከማንም የተሻለ መሆን አለበት፡፡
“የጣይቱ ሰባት የህግ ጥበቃ ፈንድን (ድጎማ/ዝክር)” እንደግፍ፣
ሁሉንም አንባቢዎቼን “ለጣይቱ ሰባት የህግ ጥበቃ ፈንድ (ድጎማ/ዝክር)” እንድታዋጡ በአክብሮት እጠይቃለሁ፡፡ የሰኞ ትችት መጣጥፌን ለበርካታ ዓመታት ስታነቡ የቆያችሁ በርካታ ወገኖቼ እንዳላችሁ እገነዘባለሁ፡፡ የሰኞ ትችት መጣጥፌ አሁን ስምንተኛ ዓመቱ መሆኑ ነው፡፡ አንዳንዶች ከእኔ ጋር በሁሉም ነገር በሀሳብ የማይግባቡ እንዳሉ አውቃለሁ፡፡ እንደዚሁም በርካታ ለመቁጠር የሚያስቸግር ብዛት ያላቸው አንባቢዎቼ ደግሞ ቢያንስ በጥቂት ነገሮች ላይ ከእኔ ሀሳብ ጋር እንደሚስማሙ እገነዘባለሁ፡፡ የእኔ አቤቱታ የቀረበው ለእነዚህኛዎቹ ወገኖቼ ነው፡፡  በኢትዮጵያ በገዥው አካል የይስሙላው ፍርድ ቤት የፍርድ ሂደት እየተሰቃዩ ያሉትን “የጣይቱ ሰባት” ጀግኖችን በመርዳቱ ጥረት እያንዳንዳቸው ማገዝ እንዲችሉ ያቀረብኩትን ሀሳብ በመደገፍ በተግባር እንዲያሳዩ በአክብሮት እጠይቃለሁ፡፡ እርዳታ እንዲያደርጉም በአጽንኦ እማጸናለሁ፡፡ ምንም ትንሽም ቢሆንም እንኳን ስጋት አይደርባችሁ፣ ትልቅ ጋን በትንሽ ጠጠር ይደገፋል ነውና፡፡ ባለፉት ዓመታት ምን ለመስራት እንዳቀድኩ አድናቆታቸውን የገለጹልኝ በርካታ ኢትዮጵያዊያን/ት ወገኖቼን በተለያዩ ጊዚያት አግኝቸ ነበር፡፡ ምንም ይሁን ምን ለሰራሁት ሁሉ ምስጋናን አልሻም፣ በኢትዮጵያ ያለው የሰብአዊ መብት ያለመሻሻል ሁኔታን ስመለከት ካሁን የበለጠ ሺ አጥፍ መሆን የሆነ ስራ መስራት ነበረብኝ በማለት አራሴን ወቅሳለሁ፡፡
የዛሬ ሰባት ዓመት በዚሁ ወር “ትንሿ ወፍ እና የጫካው እሳት: የዲያስፖራው ማህበረሰብ የሞራል ትረካ” በሚል ርዕስ ስር በትችት መጣጥፌ ላይ ምን ለመስራት እንዳሰብኩ ለአንባቢዎቼ ተናግሬ ነበር፡፡ በዚህም መሰረት ማድረግ የምችለውን ሁሉ እያደረግሁ ነው፡፡ አሁን አንባቢዎቼን መጠየቅ የምፈልገው ማድረግ የሚችሉትን ሁሉ እንዲያደርጉ ነው፡፡ እስቲ በጥሞና አስቡት ወገኖቼ በመቶዎች እና በሺዎች የሚቆጠሩ ትናንሽ ወፎች አንድ ላይ ተባብረው በመስራት የጫካን እሳት መግታት ይችላሉ፡፡ በአሁኑ ጊዜ የ”ጣይቱ ሰባት” ጀግኖች በአረመኔው ገዥ አካል የእሳት ማቀጣጠያ ጉድጓድ ውስጥ ናቸው፡፡ ሲቃጠሉ መመልከት አለብን ወይም ደግሞ ከእነርሱ ጎን በመቆም ታግለን ለድል መብቃት አለብን፡፡ “ለጣይቱ ሰባት የህግ ጥበቃ ፈንድ(ድጎማ/ዝክር)” እርዳታችሁን እንድታደርጉ እማጸናለሁ፡፡ ለወደፊቱ የኢትዮጵያ ወጣት ወንዶች እና ሴቶች ተቆርቋሪነታችሁን አሁኑኑ በተግባር አሳዩ፡፡
የሰማያዊ ፓርቲን ሴት ጠይቁ…
ከቀድሞዋ የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚኒስትር ማጊ ታቼር ጋር በብዙ ነገሮች ላይ እንደማልስማማ አምናለሁ፡፡ ነገር ግን ጠቅላይ ሚኒስትሯ በሴቶች የፖለቲካ አመለካከት ላይ በነበራቸው እምነት ምንም ዓይነት ያለመስማማት አዝማሚያ አልነበረኝም፡፡ “በፖለቲካው ዓለም የተነገረ ምንም ነገር በፈለጋችሁ ቁጥር ወንድን ጠይቁ፡፡ የተሰራ ምንም ነገር በፈለጋችሁ ጊዜ ግን ሴትን ጠይቁ“ ነበር ያሉት፡፡ ሰለሆነም ለእነዚህ ወጣት ሴት የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች እና አባላት አንድ ነገር እናድርግ፡፡http://ecadforum.com/

Wednesday, March 19, 2014

በነፃነት ቀን ነፃነት ማጣት

Young semayawi party female activists
ሰብአዊ መብቶች እያንዳንዳችን ሰው በመሆናችን ብቻ የሚገቡን ከሰብአዊነታችን ተለይተው ሊታዩ የማያችሉ መብቶች ናቸው፡፡ መንግስታት እነዚህን በአለም አቀፍ ደረጃ እውቅና የተሰጣቸውን ሰብአዊ መብቶች ለማክበር ለማስከበርና ለማሟላት በቀዳሚነት ኃላፊነት አለባቸው፡፡ በዚህም መሰረት ኃላፊነት ከፈረሙ ቀደምት አገራት መካከል ኢትዩጵያ ትገኝበታላች፡፡
ይሁን እንጂ የሴቶች ሰብአዊ መብቶች በሚፈለገው መልኩ ተግባራዊ ካለመሆኑ ባሻገር ኢ-ፍትሃዊነት እጅግ የበዛ ነው፡፡ ይህም በመሆኑም እ.ኤ.አ. በ1908 በአሜሪካ ኒወርክ ከተማ በጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ ይሰሩ የነበሩ ላብአደር ሴቶች ‹‹ለእኩል ሥራ እኩል ክፍያና የተመቻቸ የሥራ ሰዓት ለሴቶች›› በሚል መፈክር የሥራ ማቆም አድማ በማካሄድ የሴቶች ድምፅ እንዲስተጋባ አድርገዋል፡፡ ይህን ተከትሎ የዓለም ሴቶች በማህበር በመደራጀት ትግላቸውን በማጠናከራቸው የዓለም መንግስታትን አስተሳሰብ በመለወጥ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አባል አገሮች የሴቶች መብት ስምምነት/ኮንቪክሽን/ እንዲፈራረሙ እብይ ምክንያት ሆነዋል፡፡
እ.ኤ.አ. በ1910 በኮፕን አገር ከተማ በተደረገው ሁለተኛው ዓለም አቀፍ የሴቶች ጉባሄ ላይ የመነሻ ሃሳብ በማቅረብ ማርች 8 በየዓመቱ እንዲከበር ያደረጉት ሴቶች ለመብታቸው ያደረጉትን አስታውጾ ለመዘከር ዓለም አቀፍ መድረክ ለማመቻቸት በመቻላቸው ስማቸው በአክብሮት ይነሳል፡፡ ለመጀመሪያ ጊዜ በዓሉን ያከበሩት ጀርመን፣አውስትራሊያ፣ሲውዘርላንድ እና ዴንማርክ ለመሆናቸው መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡
ከዚሁ የአንድነት ተምሳሌትነት በመነሳት በዓለማ አቀፍ ደረጃ ማርች 8 የሴቶች ቀን በማድረግ ዓለም አቀፍ ስያሜዎችን በመስጠት አገራችን ኢትዮጵያ ጨምሮ በተለያየ መልክ ሲከበር አመታትን እቆጥሯል፡፡ የዘንድሮዉም ማርች 8 አለም አቀፍ የሴቶች ቀን እስከ ዛሬ በአገራችን በተከታታይ የኢትዮጵያ ሴቶች ካከበሩት በዓላት የሚለየው ሁሌም የምኮራባቸው የሰማያዊ ፓርቲ ሠላማዊ ታጋይ ሴቶች የፈፀሙት ገድል ነው፡፡
በአገራችን ኢትዮጵያ የዜጎች መብት በእኩልነት ተጠብቆ በሴቶች ላይ አጥልቶ የኖረው የጾታ ጭቆና እስከዛሬ ምላሽ ያላገኘ መሆኑ የሚታወቅ ነው፡፡በተለይ በወያኔ/ኢህአዴግ መንግስት የስልጣን ዘመን የሴቶች ጭቆና እና የመብት እረገጣ በህግ ማቀፍ ውስጥ መሆኑ ይብልጥ አሳሳቢ ያደርገዋል፡፡ ይህን ለማለት የሚያስደፍረው የህጎች ሁሉ የበላይ ህግ ነው በሚባለው ህገመንግሰት የፆታን አድልዎ የሚቀርፍ እና የሴቶችን መብት የሚያመላክት ድንጋጌዎች በውስጡ አካቶ የያዘ ቢሆንም ተግባሪዊነቱ ፕ/ር መስፍን እንዳሉት ‹‹የተፃፈበትን ወረቀት ያህል ዋጋ የማያወጣ ነው››፡፡ ዋጋ አለው እንኳን ከተባለ የትርፉ ተካፋይ የሆኑት የገዥው መንግሰት አጨብጫቢዎች እና የጡት ልጆች ብቻ ናቸው፡፡
በአገራችን መከበር ከጀመረ ከሦት አስርታት በላይ ያስቆጠረው ማርች 8 ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን ለሴቶች በሴትነታቸው ከሚደርስባቸው ጾታዊ በደል እና የሰብአዊ መብት ጥሰት ያስቀረላቸው አንድም ነገር የለም፡፡ በተለይ ከላይ እንደተገለፀው በወያኔ/ኢህአዴግ መንግሰት ሴቶች በህግ እና በመብት ጥላ ስር ከፍተኛ የሰብአዊና የዲሞክራሲ ጥሰት እየተፈፀመባቸው ይገኛል፡፡
እጅግ አስገራሚው ክስተት ደግሞ የኢህአዲግ ሴቶች ሊግ ፣ የሴቶች ፎረም ኢህአዲግ የሚያዘው እና አገዛዙ ያስተባበራቸው በርካታ የሴት ማህበራት ተጠሪነታቸው በቀጥታ ለወያኔ መንግስት ስርአት ነው፡፡ ስርአቱ ደግሞ የመላው ኢትዮጵያዊያን ድጋፍ እና ይሁንታ ያላገኘ መሆኑ ነው፡፡ ነገሩን ይበልጥ አሳሳቢ የሚያደርገው ደግሞ ኢትዮጵያዊያን ሴቶች ከመንግስት ድጋፍ ውጪ በራሳቸው ፍቃድና አቅም አንድም የተደራጀ ማህብር የሌላቸው መሆኑ ነው፡፡ እርግጥ ነው የሴቶች የፅዋ እና የእድር እንዲሁም የዕቁብ ማህበራት በአገራችን ለቁጥር የሚታክቱ ነው፤ግን እነዚህ ማህበራት የሴቶችን ሁለንተናዊ ችግሮችን የሚቀርፉ አይደለም፡፡
ለመደራጀት ሳይሆን ለማደራጀት ትኩረት እና ድጋፍ የሚሰጠው መንግሰት በሴቶች ላይ ማላገጥን ስራዬ ብሎ ተያይዞታል፡፡ለዚህም እንደማሳያ ከታችኛው የቀበሌ ባለስልጣን ጀምሮ እስከላይኛው የአገር መሪ የሴቶች እኩልነት እና የመደራጀት መብት በህግ የተጠበቀ እንደሆነ ሳይታክቱ የሚገልፁት ነገር ነው፡፡ይሁን እንጂ የሴቶች እኩልነት እና የመደራጀት መብት ለኢህአዴግ አባልነት እና ቤት ለቤት ቡና እያጣጡ የተነገራቸው መልሰው ከማውራት ከቅያስ ወይም ከጎሮ ከድሬነት ያለፍ ተሳትፎ ከተደራጁበት ሳይሆን ከደራጃቸው አካል ያተረፉት ነገር የለም፡፡ ከላይ የተጠቀሰው አሳብ ለመረዳት እና ለመታዘብ ብዙ መራቅ አያስፈልግም በህገመንግስቱ መሰረት ተደራጅተዋል የተባሉ ማናቸውም እንዲሁም በየትኛውም ቦታ የሚገኙ የሴት ማህበራት ከመንግሰት ተፅኖ ውጪ ላለመሆናቸው ከማህበራቸው የስም አወጣጥ ጀምሮ ተግባራቸው በመመልከት በቀላሉ ማህበሩ እና ማህበርተኞችን እነማን እንደሆኑ ለመረዳት ይቻላል፡፡
ለዚህ ፁሑፍ መነሻ የሆነው አሳብ ዘንድሮ ተከብሮ ሳይሆን ተደፍሮ ለማለት በሚያስችል ሁኔታ ማርች 8 መሰረት ያደረግ ነው፡፡ እንደሚታወቀው የባለፈው እሁድ ማርች 8 አስመልክቶ የሴቶች 5 ሺህ ኪ.ሜ ሩጫ ውድድር ተካሂዶአል፡፡ በውድድሩ ላይ ቁጥራቸው የበዛ ሴቶች ተሳትፈዋል ፤ከተሳታፊዎቹ ብዛት ቁጥራቸው ቀላል የማይባሉ በአነስተኛ እና ጥቃቅን መንግስት ያደራጃቸው ሴቶች ናቸው፡፡ እነዚህ ሴቶች አደባባይ ይዘው የወጡት አሳብ ጥቃቅን መሆኑ በእርግጥም ማህበርተኞቹ ምን ያህል አንድ ለአምስት ‹‹እደተጠረነፉ›› የሚያሳይ ነው፡፡ የጉዳዩ አሳሳቢነት የሚጀምረው እነኚህ ጢቂት ‹‹የተጠረነፉ›› ሴቶች በነፃነት ቀናቸው ነፃነት የተነፈጋቸው መሆኑ ነው፡፡ ምክንያቱ ደግሞ እሩጫው ላይ የተሳተፉት በራሳቸው ፍቃድ ሳይሆን በድረጅታቸው ትዕዛዝ ነው ሊያስብል የሚያስችል የተለያየ ‹‹ልማታዊ›› የሆነ መፈክሮችን ሲያሰሙ ተደምጠዋል፡፡በመንግሰት ልዩ ድጋፋ የተደረገላቸው እነኚህ ሴቶች ለሚደግፉት ሳይሆን ለተገደዱበት ዓላማ የመሰላቸውን መፈክር እና ቀረርቶ በማሰማት እንዲሁም የተለያዩ ፖስተሮችን በመያዝ በዕለቱ ሲንቀሳቀሱ ታይተዋል፡፡
ይሁን እንጂ ለመንግስት ደጋፊዎች የተፈቀደው ለሌሎች ለመንግሰት ተቃዎሚ ሴቶች ፖሊስ ያደረገው ክልከላ እና እስራት ክስተቱን አስገራሚ ብቻ ሳይሆን አሳሳቢያ ደርገዋል፡፡ እንደሚታወቀው ማርች 8 ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን ነው፤ ይህ ቀን ሴቶች ተሰባስበው ከበሮ ይዘው የሚደልቁበት ቀን ሳይሆን ለነፃነታቸው ቀደምት ሴቶች ያደረጉትን ተጋድሎ በመዘከር ያሁኖቹ ሴቶች ለበለጠ እኩልነት እና ነፃነት በጋራ የሚቆሙበት የቃል ኪዳን ቀን ነው፡፡ ይህም እንደሆነ የተረዱ ሴቶች በነፃነት ቀናቸው ስለነፃነታቸው ከፍ ባለ ድምፅ ሲዘምሩ ማየት ምንኛ መታደል ነው ! ይህን በድፍረት ላደረጉት የሰማያዊ ፓርቲ ወጣት ሴቶች አድናቆት ሊቸራቸው እና ድጋፍ ሊሰጣቸው ይገባል፡፡
ከዚህም በተጨማሪ ሴቶች በፖለቲካ አመለካከታቸው ብቻ በአደባባይ ታፍሰው ለእስር የበቁት በእኔ ዘመን ይህ የመጀመሪያ ነው ፡፡የኔ ዘመን ደግሞ 23 ዓመት ሙሉ የሴቶች የፖለቲካ ተሳትፎ የበላው ጅብ አልጮው ብሎ ተቸግረን የከረምንበት ወቅት ነው፡፡ እርግጥ ነው ይህ የሆነበት ምክንያት ለማወቅ እና ለመዘርዘር ሰፊ ጥናት ያስፈልጋል፡፡ የችግሩ አሳሳቢነት እንደተጠበቀ ሆኖ እንቢ ለነፃነቴ በማላት አደባባይ በመውጣት የሰማያዊ ፓርቲ ወጣት ሴቶች ‹‹ እኔ የጣይቱ ልጅ ነኝ ! እስክንድር ይፈታ ! እርዮት ትፈታ ! አብበከር ይፈታ ! አንዱአለም ይፈታ ! መብራት እና ውሃ ናፈቀን ! ፍትህ እንፈልጋለን ! ›› እና የመሳሰሉትን መፈክር በልበ ሙሉነት በማሰማት ያሳዩት ቆራጥነት ታሪክ መቼም የሚዘነጋው አይደለም፡፡ በይበልጥ ደግም በዚሁ የፖለቲካ አመለካከታቸው ምክንያት ብቻ ለእስር መዳረጋቸው የመንግስት ስርዓት ምን ያህል አምባገነን እና ጨቋኝ እንደሆን በግልፅ የሚያሳይ ነው፡፡http://ecadforum.com

Monday, March 17, 2014

በአዲስ አበባ ውሃ እስከ 20ቀናት ይጠፋል

መፍትሔ ያጣው የውኃ ችግር ተባብሶ ቀጥሏል
waterline


* “የውኃ ምርት ችግር የለብንም የኤሌክትሪክና የማሰራጨት እንጂ” የውኃና ፍሳሽ ባለሥልጣን
የፌዴራል መንግሥት መቀመጫና የአፍሪካ መዲና በሆነችው በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ፣ ለሁለትና ሦስት ቀናት ይጠፋ የነበረው የውኃ ችግር እስከ 20 ቀናት እየጠፋ  መሆኑንና ችግሩ ተባብሶ መቀጠሉን ነዋሪዎች እየገለጹ ነው፡፡
በተለይ ከሳሪስ እስከ ቃሊቲ፣ አየር ጤና፣ ወይራ ሠፈር፣ ለቡ፣ ጉለሌ፣ ኮልፌ ቀራኒዮ፣ ፒያሳ፣ ሽሮ ሜዳ፣ መርካቶ፣ የካ በተለያዩ ወረዳዎች አራት ኪሎ (አልፎ አልፎ) በአጠቃላይ በከተማው ከአምስት እስከ 20 ቀናት ውኃ ጠፍቶ እንደሚሰቃዩ ገልጸዋል፡፡ ወ/ሮ ስንታየሁ አበበ የተባሉ የሳሪስ አቦ ማዞሪያ አካባቢ ነዋሪ እንደገለጹት፣ የውኃ ችግር ከቀን ወደ ቀን እየጨመረ መምጣቱ ያስገርማቸዋል፡፡ ቀን ቀን ይጠፋና እኩለ ሌሊት ይመጣላቸው በነበረው ውኃ ሲማረሩ፣ ይባስ ብሎ የመጥፋቱ ሁኔታ ወደ ሦስት፣ አራትና አምስት ቀናት አድጐ አሁን እስከ 20 ቀናት ውኃ እንደማያገኙ ጠቁመዋል፡፡ በመንገድ ግንባታ ምክንያት በሚል በተለይ ከ2001 ዓ.ም. እስከ 2004 ዓ.ም. መጀመርያ ወር ድረስ በፈረቃ በሁለትና ሦስት ቀናት ቆይታ ያገኙት የነበረው ውኃ፣ መንገዱ ከተጠናቀቀ በኋላ ብሶበት ወደ ወር ሊቃረብ መድረሱንና አሁን ባለው ሁኔታ በቅርቡ ወር ሙሉ ላያገኙ እንደሚችሉ ተናግረዋል፡፡
መንግሥት ከፍታ ባላቸው አካባቢዎች ውኃ ማዳረስ እንዳቃተው አምኖ ሲገልጽ የከረመ ቢሆንም አሁን ግን በለገዳዲ፣ ገፈርሳና አቃቂ ቃሊቲ የከርሰ ምድር ውኃ አካባቢ ያሉ ነዋሪዎችም ውኃ እያጡ በመሆኑ ‹‹ምን ተፈጠረ?›› የሚል ጥያቄ እየተፈጠረባቸው መሆኑን ወ/ሮ ስንታየሁ ገልጸዋል፡፡ ቀደም ባሉት ጊዜያት ውኃና ኤሌክትሪክ  የሚጠፉበት ጊዜና ቀናት በመገናኛ ብዙኃን ይነገር እንደነበር ያስታወሱት ወይዘሮዋ፣ አሁን መንግሥት ሰልችቶት ይሁን አሳፍሮት ዝምታን መምረጡ እያሰጋቸው መሆኑን አክለዋል፡፡
ከመሀል አዲስ አበባ (ፒያሳ) ጀምሮ እስከ ዳር ከተማና አቀበት በሚባሉ አካባቢዎች የሚኖሩ ሁሉ እንደ ወ/ሮ ስንታየሁ ‹‹የውኃ ያለህ›› እያሉ ሲሆን፣ የውኃና ፍሳሽ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቶች፣ በክፍለ ከተማና እስከ ማዘጋጃ ድረስ እየሄዱ አቤት ቢሉም ምላሽ ሊያገኙ እንዳልቻሉ እየገለጹ ነው፡፡ ከሁለት ሳምንት በፊት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ድሪባ ኩማ ባቀረቡት የግማሽ በጀት ዓመት የሥራ አፈጻጸም ላይ፣ ውኃን በሚመለከት ያቀረቡትን ሪፖርት በተለይ በውኃ ችግር water lineውስጥ ያሉ ነዋሪዎች አምርረው እየተቃወሙ ነው፡፡ አንድ ስማቸው እንዲገለጽ ያልፈለጉ የሽሮ ሜዳ ነዋሪ እንደገለጹት፣ ‹‹እኛስ መጣች መጣች ብለን ሌሊቱን ስንሯሯጥ መኖሩን ለምደነዋል፡፡ የኛ ዕጣ ፈንታ የደረሳቸው የመሀል ከተማ ነዋሪዎች ግን ያሳዝኑኛል፡፡ ይበልጥ ደግሞ ያዘንኩት የታደለ አገር በዘመናዊ መንገድ ማንኛውንም አቅርቦት እንደልቡ ሲቀርብለት፣ እኛ የውኃ ጥም ለማርካት ቦቴ መኪና እንደሚገዛልን እየተነገረን ነው፤›› በማለት የከንቲባውን ሪፖርት ተገቢ አለመሆኑን በመግለጽ ተቃውመዋል፡፡
አስተዳደሩ ትኩረት በመስጠት ከተንቀሳቀሰባቸው ተግባራት አንዱ የውኃ ምርትን መጨመር መሆኑን የገለጹት ከንቲባ ድሪባ፣ በአቃቂ ቃሊቲ 19 ጥልቅ ጉድጓዶች መቆፈራቸውንና 80 ሺሕ ሜትር ኩብ ውኃ ማምረት መቻሉን፣ በለገዳዲም 11 ጥልቅ ጉድጓዶች እየተቆፈሩ መሆኑን፣ ለገዳዲን በማስፋትና የድሬ ግድብን በማሻሻል የውኃ ማምረት አቅምን ወደ 195 ሺሕ ሜትር ኩብ ለማሳደግ የሚያስችል ሥራ እየተሠራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ በአጠቃላይ ወደ 260 ሺሕ ሜትር ኩብ የሚጠጋ ውኃ ማምረት የሚያስችል ሥራ እየተሠራ መሆኑንና ሁሉም ሥራዎች ሲጠናቀቁ 610 ሺሕ ሜትር ኩብ የውኃ ምርት ከፍ እንደሚልም በሪፖርታቸው ከንቲባው አብራርተዋል፡፡
ነዋሪዎች ግን ሥራውና ዕቅዱ ወይም እንቅስቃሴው ከወረቀት ላይ እንደማያልፍ  በመግለጽ፣ የዕለት ጥማቸውን የሚያስታግሱበት መፍትሔ እንዲፈለግላቸው እየጠየቁ ነው፡፡
የአዲስ አበባ ውኃና ፍሳሽ ባለሥልጣን ግን በነዋሪዎቹ አቤቱታና ሮሮ አይስማማም፡፡ ‹‹የውኃ ምርት እጥረት የለብንም፣ ችግራችን የሥርጭት ነው፡፡ ለዚህ ደግሞ የመንገድ ግንባታዎችና በተደጋጋሚ የኤሌክትሪክ መጥፋት ከፍተኛ ችግር እየፈጠረብን ነው፤›› ሲሉ የባለሥልጣኑ ኮሙዩኒኬሽን ኃላፊ የሥራ ሒደት ባለቤት አቶ ሙሉጌታ ከምሴ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡
ባለሥልጣኑ ችግር ያለባቸውን አካባቢዎች ለይቶ ማወቁንና ከፍተኛ ችግር አለባቸው የተባሉትን ንፋስ ስልክ ላፍቶ፣ ጉለሌ፣ የካና ኮልፌ ቀራኒዮ ክፍላተ ከተማዎች ውስጥ ለሚገኙ ነዋሪዎች፣ ለተወሰኑት ጊዜያዊ የፕላስቲክ መስመር እየዘረጋ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ አቀበት ለሆኑት ደግሞ በመከላከያ ኢንጂነሪንግ ያሠራቸውን ታንከሮች እየተተከለ መሆኑን፣ ዘላቂ መፍትሔ ለማምጣት ደግሞ ጄኔሬተር እየተገዛና የፀሐይ ኃይል ለመጠቀም ጥናት እየተካሄደ መሆኑን አስረድተዋል፡፡http://www.goolgule.com/

Saturday, March 15, 2014

የኢህአዴግ ማመልክቻ ድጋሚ ውድቅ መደረግ አለበት!

በመጀመሪያ አፋኝ ሕጎች መሠረዝ አለባቸው!
eiti


የተፈጥሮ ሃብትን በትክክለኛ መንገድ ለሕዝብ ጥቅም መዋሉን በመከታተል ለአገራት እውቅና የሚሰጠው The Extractive Industries Transparency Initiative (EITI) ለተሰኘ ዓለም ዓቀፋዊ ተቋም ኢህአዴግ በድጋሚ ያቀረበው የእውቅና ጥያቄ ማመልከቻ ውድቅ መደረግ እንዳለበት ዓለምአቀፉ የሰብዓዊ መብት (Human Rights Watch) ድርጅት አስታወቀ፡፡ ኢህአዴግ የእውቅና ማመልከቻ አስገብቶ ውድቅ ተደርጎበት የነበረ ሲሆን በኢትዮጵያ ላይ የታወጁት አፋኝ ሕጎች እስካልተወገዱ ድረስ ድጋሚ ማመልከቻው ውድቅ ሊደረግ እንደሚገባው ጨምሮ ተነግሯል፡፡
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ ከሳምንታት በፊት “ኢህአዴግ ራሱ ባወጣው አፋኝ ሕግ ታፈነ” በሚል ርዕስ ባወጣው ዜና ጉዳዩን በስፋት ዘርዝሮ ነበር፡፡ “EITI የዛሬ 11ዓመት አካባቢ የተቋቋመ በተፈጥሮ ሃብት ዙሪያ ዕውቅና የሚሰጥ ድርጅት ሲሆን ድርጅቱ የተፈጥሮ ሃብት የህዝብ መሆኑን የሚያምን ሲሆን ማንኛውም የተፈጥሮ ሃብት – ማዕድን፣ ዘይት፣ ብረታብረትና ጋዝ – ከመሬት በሚወጣበት ጊዜ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ የሚኖረውን ያህል ግልጽነትና ተጠያቂነት በሌለባቸው አገራት ድርጊቱ ለሙስና እና ግጭት በር እንደሚከፍት ይናገራል፡፡ በመሆኑንም ድርጅቱ (EITI) አገራት ለሚያቀርቡት የዕውቅና ጥያቄ ማሟላት ያለባቸውን መስፈርት በዝርዝር አስቀምጧል፡፡ ልማትና እድገት በሚል ሰበብ የሕዝብ ሃብት የሆነውን የተፈጥሮ ሃብት በማውጣት የህዝባቸውን መብት ለሚረግጡ አገራት የሚያቀርቡትን የዕውቅና ማመልከቻ ውድቅ ያደርጋል፡፡”
በወቅቱ ጎልጉል የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ምንጭ ጠቅሶ እንደዘገበው “ኢህአዴግ ያቀረበው የእውቅና ጥያቄ ውድቅ መደረጉ እውነት ነው። ምንጩ እንዳሉት ኢህአዴግ በውሳኔው በመበሳጨት ይግባኝ ለመጠየቅ በዝግጅት” ላይ መሆኑን ጠቁሞ ነበር፡፡
የEITI ዕውቅናን ለማግኘት ቋምጦ የነበረው ኢህአዴግ በድርጅቱ ውሳኔ ባለመደሰት ጥቂት ዓመታትን ቆጥሮ ከአቶ መለስ ሞት በኋላ በአቶ ሃይለማርያም በመመራት በድጋሚ የዕውቅና የማግኘት ዘመቻውን ማጠናከር ከጀመረ ቆይቷል፡፡ የማዕድን ሚ/ር መ/ቤትም የEITI ዕውቅና ማግኘቱ በጣም የሚያስፈልግ እንደሆነ በይፋ በመናገር ዘመቻውን አጧጡፎ ነበር፡፡ ከዚህም አልፎ ለዓመታት ሲጠቀምበት የነበረውን አሠራር በዓለምአቀፉ ድርጅት ላይ ተግባራዊ በማድረግ ኢህአዴግ Ethiopia Revenue Transparency Initiative (ERTI) የሚባል “ተለጣፊ” ተቋም በመመሥረት እንቅስቃሴ ሲያደርግ እንደቆየ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቱ ለEITI በጻፈው ደብዳቤ ላይ መግለጹንጎልጉል ጨምሮ ዘግቦ ነበር፡፡
clare
ክሌር ሾርት
ዛሬ የወጣው የሰብዓዊ መብት ድርጅት መግለጫ ይህንኑ የኢህአዴግን ጥያቄ የሚያስረዳ ሲሆን በአፋኝ ህጎቹ ላይ አንዳችም ለውጥ ያላሳየው ኢህአዴግ ማመልከቻው ውድቅ መደረግ እንዳለበት መግለጫው በአጽዕኖት ይናገራል፡፡ ምክንያቱንም ሲጠቅስ “የኢትዮጵያ መንግሥት ሚዲያውን አፍኗል፤ (ሰብዓዊ መብት እንዲከበር) እንቅስቃሴ የሚያደርጉ ሁሉ አድቅቋል” በማለት ያስረዳል፡፡ ኢህአዴግ ከዚህ በፊት ባስገባው ማመልከቻ ላይ የEITI ቦርድ ውሳኔውን ሲያስተላልፍ “የመያዶች ሕግ የተሰኘው አዋጅ ተግባራዊ እንዳይሆን እስካልተደረገ” ማመልከቻው ሊታይ እንደማይገባው በዋንኛነት ማመልከቻው ውድቅ እንዲደረግ የተደረገበት ምክንያት እንደነበር የጠቀሰው የሰብዓዊ መብት ድርጅት መግለጫ EITI አሁንም ይህንኑ ውሳኔውን እንዲያከብር ጠይቋል፡፡
ማመልከቻው እንደገና እንዲታይና የቦርዱ የቀድሞ ውሳኔ እንዲቀለበስ እየተንቀሳቀሱ የሚገኙት የቀድሞ የእንግሊዝ ዓለምአቀፍ ትብብር ሚ/ር የሆኑት ክሌር ሾርት መሆናቸውን መግለጫው ያስረዳል፡፡ እኚህ ግለሰብ የአፍሪካ አምባገነኖችን በመደገፍ የሚታወቁ ሲሆን ይህ ከጥቅማቸው ጋር የተሳሰረው ግንኙነታቸው አሁንም ኢህአዴግን እንዲደግፉ እንዳደረጋቸው ይነገራል፡፡ እንዲሁም በሌሎች ኢህአዴግ ባቋቋማቸው ዓለምአቀፋዊነት ሽፋን በተላበሱ ድርጅቶች ውስጥ የአመራር አባል በመሆን ሚስ ሾርት እንደሚያገለግሉ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ የእንግሊዝ ፓርላማ አባል በነበሩበት ወቅትም ያላወጡትን ወጪ አውጥቻለሁ በማለት በብዙ ሺዎች የሚገመት ገንዘብ ለግል ጥቅማቸው ያዋሉ መሆናቸው በወቅቱ ዴይሊ ቴሌግራፍ ባወጣው መረጃ አጋልጦ ነበር፡፡ የተወሰነውን ገንዘብ የመለሱ ቢሆንም ጋዜጣው በወቅቱ ያወጣው መረጃ ግለሰቧ የሕዝብን ገንዘብ ለግል ጥቅማቸው የተጠቀሙ “ሙሰኛ” መሆናቸውን ያስረዳል፡፡
ከእነዚህና ሌሎች መረጃዎች አኳያ ኢህአዴግ በየቦታው እየደለለ “ባስቀመጣቸው” በመጠቀም የፈለገውን ለማድረግ ሲሞክር ዝም ሊባል እንደማይገባው በዚሁ ጉዳይ ላይ በከፍተኛ ሁኔታ የሚንቀሳቀሰውን የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄን ጠቅሶ ጎልጉል መዘገቡ ይታወሳል፡፡
የሰብዓዊ መብት ድርጅቱ ዛሬ ባወጣው መግለጫ መሠረት ኢህአዴግ የEITI አባል መሆን ከፈለገ ያወጣቸውን አፋኝ ሕጎች በሙሉ መሠረዝ እንዳለበትና የመናገር መብትን፣ የፕሬስ ነጻነትን፣ የመሰብሰብ፣ ወዘተ መብቶችን በይፋ ማክበር እንዳለበት እና የEITI የአባልነት ቅድመ መስፈርቶችንም በሙሉ ማሟላት እንደሚገባው ጨምሮ ገልጾዋል፡፡http://www.goolgule.com/

Thursday, March 13, 2014

ትዝብት – ደርሶ መልስ ዲያስፖራ (አንደኛ)

ነገሩ የሆነው አዋሳ ዩኒቨርሲቲ ነው። ቆነጃጅት ወጣት ሴት ተማሪዎች ከዩኒቨርሲቲው ቅጥር ግቢ ውጭ ባሉ የከተማው ደለላዎች ጋር በመተባበር እጅግ ዘግናኝ ስራ ይሰራሉ። ደላሎቹ የቆነጃጅቶቹን ተማሪዎች ፎቶ የያዘ ትልቅ ካታሎግ ይዘው ከአዲስ አበባም ሆነ ከአቅራቢያው ከተሞች አለዚያም ከዚያው ከአዋሳ ከተማ ብቅ የሚሉ ሃብታም ደንበኞቻቸውን የተማሪ ኮረዶችን ፎቶ በመስጠት ያስመርጣሉ።
ሰውየው ውብ ወጣት ተማሪ ኮረዳ እንደሚፈልግ በሰው በሰው የተገናኘውን ደላላ ይጠይቃል። እናም ከተሰጠው የፎቶ ድርድር ላይ ማመን ያቃተውን የአንዷን ውብ ፎቶ እያሳየ ‘ይህችን ታውቃታለህ?’ ሲል ይጠይቃል። የደላላ መልስ አንድ ነው… ሁሉንም ስለሚያውቃቸው አልተቸገረም ‘አዎ እሷን ይፈልጋሉ?’ ሲል ይጠይቃል። ሰውየውም ‘እባክህ’ ሲል በመማጸን ፈቃደኝነቱን ይገልጻል። ከፊቱ የመጣለትን ገቢ ተደራድሮ ልጅትን ለመጥራት ይሮጣል። ደላላው።
እናም ቆንጅት ተበጃጅታ፣ አምራና ደምቃ ትመጣለች። በቀጥታ ወደ ሰውየው መኪና ስትደርስ ሰውነቷ ይርዳል። በቁጣ አይኑ የተንቀለቀለው ሰውየም ወደ ልጅቷ ያፈጣል… በቀጥታ ተንደርድሮ የልጅቷን ክርን ይይዛል… ደላላው እየሆነ ያለውን ሊረዳ አልቻለም… የልጅቷን እጅ የያዘው ሰው (ደንበኛ) የልጅቷ ወላጅ አባት ኖሯል።
ኢትዮጵያ ደርሶ የሚመጣ የውጭ ሀገር ነዋሪ (ደርሶ መልስ ዲያስፖራ) በተለያየ አይነት እይታ የተለያዩ እውነታዎችን ይዞላችሁ ይመጣል።
አንዳንዱ የህንጻውን ግንባታ አዳንቆ ሲያወራ፤ ሌላው ስለጭፈራ ቤቶች ይዘክራል። ጓደኞቹን በስራ ብዛት ሊያገኝ እንዳልቻለ የሚያወራላችሁ እንደመኖሩ ሁሉ በስራ አጥነት ችግር የተነሳ ዱርየ መበራከቱን የሚተርክላችሁ አታጡም። የቆነጃጅቶችን ውበትና የዳንኪራ ቤቶችን ሁናቴ የሚነግራችሁ፤ በየቡና ቤቱ ብሎም በየትምህርት ቤቱ ያሉ ወጣቶችን ችግር ያስረዳችኋል። የሀገሪቱን እድገት በኮንስትራክሽን መጥለቅለቅ የሚያጫውታችሁ፤ በመንገዱን መቆፋፈር ሰው ስለመማረሩ በማንሳት ያትትላችኋል። አዲስ አበባን በመመስረት ላይ እንዳለች ታላቅ ከተማ አድርጎ የሚተርክም አታጡም።
ይሄ ሁሉ እንደ እድገት በአንዲት መንግስት የሚባል አካል አላት በተባለች ሀገር መታየቱ ምኑ ይገርማል?። አንዳንዴ ሀገሩን አይቶ ዘመድ ወዳጅ ጠይቆ መምጣትም ሆነ ሰው ሀገሩ ደርሶ መመለሱ እጅግ መልካም ነገር ነው። ያየውን ግልብ ነገር ከራሱ አይን ጥግ ስር አንጻር ብቻ ተመልክቶ በሰዎች ላይ የሚደርስን ስቆቃ ሸፋፍኖ ያለጥናት የተሰሩ መንገዶችንና ህንጻዎችን እንደትልቅ ለውጥ ማውራት ግን የሞራል ጥያቄን ያመጣል።
በእርግጥ የውብ ሀገር ነችና ውቦች ሊኖሩ ይችላሉ። መሸታ ቤቶቹም ደማምቀው ሊሆን ይችላል። ህንጻ ግምባታውም ቢጧጧፍ አያስነውርም። መንገዶች ተንጣለው ቢታዮም ጸጸት የሚገባው የለም። ነገር ግን ሰው በቀላሉ ቆሎ ሽጦ ይኖርበት ከነበረ መንደር ተባሮ መግቢያ ያጣበት ሀገር፤ ውሃ ልማት የቆፈረውንና ውሃ ቧንቧ ቀብሮ ያበጀውን መንገድ ነገ ቴሌ የሚያፈርሰው ከሆነ… ከዚያም ማዘጋጃ ቦይ ተደፈነ ብሎ ከተረተረው… ወጣት እንስት ህጻን ታናሽ እህቷንና ወንድሟን ትምህርት ቤት ለመስደድ መንገድ ከወጣች፤ ጥቂት የባለጊዜ ልጆች የሚሰሩት አጥተው በተንፈላሰሱባት ሀገር መለመንን ተጠይፈው ዱሮ የነበራቸውን ጽዱ ልብስ ለብሰው ፊታቸውን የከለሉ ሰዎች በየጥጋጥጉ የሚለምኑባት ሀገር ከሆነች… አባት ትምህርት ቤት ብሎ የላካት ወጣት በኮሌጅ ያለውን ፍላጎቷን ለማሳካት ገበያ መውጣት… ዘግናኝ ነው…
የሚሰራው መንገድ ተሸርሽሮ ከአመት በላይ አገልግሎቱ አልቆለት ተቦርቡሮና ውሃ ቋጥሮ የሚታይበት ሀገር እየገነቡ መሰረት መጣል አይቻልም ነው ጥያቄው። ደረጃቸውን ባልጠበቁና በይድረስ ይድረስ የተሰሩ ህንጻዎች ጋጋታ የከተማንም የሀገርንም እድገት ሊያሳዩ አይችሉም ነው እየተጮኸበት ያለው ነገር። ፍትህ ራሷን ችላ የምትራመድበትን ሀገር የሚመራ መንግስት ይኑር ነው ልፈፋው። የህወሃት ሰዎችና ጥቂት አሸርጋጆች የሚያደርጉት አገራዊ ጥፋት ይቁም። ልጆቻችን እርስበርስ የዚህና የዚያ ብሄር ወይንም ከወዲያ አለዚያም ከወዲህ መንደር የመጡ እየተባባሉ በጥርጣሬ እየተያዩ የሚኖሩበትንና የሚያድጉበትን ሀገር እናፈራርስ ነው እሪታው። የህወሀት አለያም ጥቂት ሽርጉደኞች በገፍ የሚገነቧቸው ህንጻዎች ከሙስና ባሻገር ሆኖ ራሳቸው ኢንጂኒዬርና አርክቴክት ሆነው የሚገነቡት ሀገር ሀገር አይሆንም ነው ጉዳዩ።
22 አካባቢ የተሰራው ጎላጎል ህንጻ ባለጊዜው ባለቤት ህንጻውን ሲያስገነባ ዋናው መንገድ ውስጥ መግባቱን ያየ መሀንዲስ ወይንም ኢንጂኒዬር ‘አግባብ አይደለም፤ ወደፊት መንገድ ይዘጋል’ ብሎ ምክር ቢሰጠው ‘እኔ ያልኩህን አድርግ’ ብሎ ጀርባውን የተማመነው ባለቤት ሲያዘውና ያ ባለሙያ የታዘዘውን በማድረጉ ግንባታው ከተጠናቀቀ በኋለ አሁን መንገዱን የዘጋውን ህንጻ የሚደፍረው ጠፍቶ፤ መረማመጃው ዘግቶ መታየቱ የሚወራው ዝም ብሎ ከመሬት ተነስቶ አይደለም።
አሁንማ የህወሃት ሰዎች እጅግ ከመድፈራቸው የተነሳ አዲስ አበባ ውስጥ በስማቸው ሆኗል ፎቅ የሚያስገነቡት ተክላይ ህንጻ፣ ገብረጻዲቅ ህንጻ… ብሎ ያጫወተኝ ወዳጄ ታዲያ ምን ችግር አለው? ስለው ‘ምንም ችግር የለውም በህዝቡ ውስጥ ግን የማህበራዊ ህይወት መራራቅንና ሃሜትል ያስከትላል ብሎም ህዝቡን እነሱ እና እኛ የሚያስብል የሳይኮሎጅ ጣጣ ውስጥ ከቶታል።” አለኝ
ሀገሪቱን የህወሃት ጄኔራሎችና መኮንኖች ብቻ በሀብት የወረሯት ሀገር ተሸክሞ የት እንደሚደረስ ማሰብ ሰው መሆን ነው። ይህ ወዳጄ ታዲያ በአንጻሩ የሽንኩርትን ገበያ ለማየት ጉሊት ወርዶ ያየውን ጉድ በልኩ አስተውሎ መጥቷል። አንድና ሁለት ራስ ትንንሽ ሽንኩርት አልያም ቲማቲም ለሳምንት ለማብቃቃት የሚሰቃይ ህዝብን ይዞ ጉዞው የት ነው የሚያደርሰን።
የአገሪቱን የዘር ችግር ጥግ ላይ መድረስ ባለፈው 767 አውሮፕላንን ይዞ ጄኔቫ የገባው ወጣት ረዳት አብራሪን በሚመለከት መግለጫ የሰጡት ሬድዋን ሁሴን “ጠላፊው ከየት ነው?’ ተብለው ሲጠየቁ ‘ኢትዮጵያዊ ነው’ ብለው ሲመልሱ አረ ከየትኛው ክልል ተብለው መጠየቃቸው ጉድጓድ ውስጥ የሚከት ቅሌት ነው። መልሳቸውም እረሪሪሪሪሪ የሚያስብል ነበር። ‘ከየትኛው ብሔር እንደሆነ አልታወቀም።’
መጠጥና ዳንኪራ ቤቶች
ከ5 ሚሊየን ህዝብ በላይ (እስከ 8 ሚሊዮን ይገመታል) የሚኖርባት አዲስ አበባ የጭፈራ ቤቶችን ብዛትና የጨፋሪውን አይነት የነገረኝ ወዳጄን ቀኑን ሙሉ ሲተራመስ የሚውለው አዲሳቤ በጊዜ በ12 ሰዓት ከቶ በየፊናው ሲገባ ከተማው ምን ያህል ጭር እንደሚል አላስተዋለም። 100 የማይበልጡ ምሽት ቤቶች (አጋንኘው ነው) 100 ሰው እያንዳንዳቸው ቢያገኙና ቢያስጨፍሩ 10ሺህ ሰው… እንጨምረው እና 50ሺህ ሰው በምሽት ስለጨፈረና ስለደነከረ ሀገር በጥጋብ እንደዘለለ ማውራት ነውር ነው ነው ጨዋታው። ይሄንኑ ግምት እናስላው ከተባለ የገዥው ህወሃት/ኢህአዴግ ባለስልጣናትና ጥቅም ተሻራኪዎች 70 በመቶውን ቢያነሱ 15 በመቶ በዲያስፖራና ዘመዶች እንዲሁም የተቀረው ለፍቶ አዳሪ አለያም ከቤተሰቡ የሚቃርም ሊሆን ይችላል።
ለነገሩማ የዘመነኞቹ ሰዎች ልጆች የሚገቡበት ቡና ቤት ውስጥ ቀድሞ የገባ ሌላ ደንበኛ ሾልኮ እንዲወጣ የሚደረግባት ምድር። በድርድር የታሰረ ብር ለአስተናጋጅ ተሰጥቶ ቆጥረሽ ውሰጅ የሚል ረብጣው ያጨናነቀው የዘመኑን ሰው ማየት የተለመደ መሆኑንም እየሰማን ነው።
ምን እዚህ እኛ በብርድ እየወጣን ሰላማዊ ሰልፍ እያልን እንጮሃለን እነሱ ሚሊየነሮች ሆነዋል ያለኝና ሀገር ቤት ሄዶ በጓደኛው የቀና ሰው ያጫወተኝም አለ። ያ ጓደኛው ከዘመንኛ ሰዎች ጋር ገጥሞ ህዝብ እየቦጠቦጠ መሆኑን የነገረኝ ደርሶ መልስ ዲያስፖራ… አሁንም እዚህ ኖርዝ አሜሪካ ከተመለሰ በኋላ እዚያው አገር ቤት ቢሆን እንደጓደኛው ሚሊየነር ይሆን እንደነበር ሲያወጋኝ በመቆጨት ነበር። ዘመንኞቹና ጓደኛው የሚቦጠቡጠው ህዝብ ስቃይ በሚሊየን ብር ተጋርዶበት። አረ እየተስተዋለ! እዚያኮ ሀገር እየተቆራረሰ ነው! አረ ስለአምላክ! ሀገሪቱም በመንደር እየተተበተበችኮ ነው! ስለእመብርሃን! ምድራችን ፍትህ የጠፋባት ሆናለችኮ! በሽብርተኛ ስም ስንቱ ታጎረ… አረ ስለአላህ! ሰው ኑሮ መረረኝ እያለ ነው እኮ! እንኳን ከአሜሪካ ከመንግስተ ሰማያትም አመጣኻለሁ የሚል ለስራው ብቁ ያልሆነ ሰው የሚሾምበት ሀገር ውስጥ የሚኖር ህዝብ እኮ ነው የያዝነው። ጭራሽ የሶማሌ ክልል ባለስልጣን ይባስ ብሎ ምኒባስ ታክሲ በከተማ እንዳይገባ ብሎ በራሱ ስልጣን አግዶ እገዳውን የጃፓን መንግስት ቢመጣም እንኳን አልቀበልም እያለ እኮ ነው ጎበዝ… ሰሚ የለም እንዴ በግዜር!?
http://ecadforum.com/

Monday, March 10, 2014

ኢህአዴግ – ሌባ ወይስ አገር አስተዳዳሪ?



ከላይ የጠየቅነው ጥያቄ ዛሬ የተነሳ አዲስ ነገር አይደለም። ኢህአዴግ መሰረቱን ዝርፊያ ላይ ያደረገ አገር አስተዳዳሪ መሆኑ ግብሩ ራሱ ምስክር ነውና “ሌባ አገር አስተዳዳሪ” ስለመሆኑ ማስተባበያ ሊያቀርብም አይቻለውም፤ አያስፈልገውም። ሌብነቱ አገርንና ህዝብን ወደ ገደል እየሰደደ መሆኑ ግን ሁሌም የሚያስጨንቅ ነውና ዛሬ እንደ አዲስ አነሳነው እንጂ!!
ኢህአዴግ ግዙፍ፣ ሃብቱ በዶላር ካልሆነ በብር የማይቆጠር፣ በህገወጥ ንግድ ሰላማዊ ነጋዴዎችን የሚውጥ፣ ለብቻው መግቢያና መውጪያ የተዘጋጀለት፣ የተለየ ጨረታና የነጻ ቀረጥ እድል የሚበጅለት፣ በየትኛውም ተቋም እንደፈለገ መጋለብ የሚችል ልጓም አልባ የሆነ፣ በፈለገው ቦታና ማህበረሰብ ጥቅም ላይ እንዳሻው ከበሮ እየደለቀ የሚጨፍር፣ ጡሩምባ ይዞ የሚያንጠራባ፣ የፈለገውን ማስወገድ፣ ማሳገድ፣ ማስከፈት፣ ማዘጋት የሚችል፣ ድንበርና ኬላ የማይዘው የንግድ ተቋም አለው። እወክላቸዋለሁ በሚላቸው የአንድ ክልል ሕዝብ ስም ባቋቋመው ሻርክ ኦዲት በማያውቀው የ”ንግድ” ተቋም አማካይነት አገሪቷን እየዘረፈና እየዋጠ ነው።
አገሪቱ አምጣ የምታገኘውን የውጪ ምንዛሬ በበላይነት ሲፈልግ ከራሱ ባንክ፣ ሲያሻው የራሱ ሰዎች በሚያዙበት የህዝብ ባንኮች በተራ ትዕዛዝ ያግበሰብሳል። በፋይናንስ ዘርፉ ውስጥ እጅና እግሩን ነክሮ እንዳሻው ያንቦጫርቃል። የሚቀናቀኑ ብቅ ሲሉ እየበለተ ይሰቅላቸዋል። ሲያሻው ፋይል አስከፍቶ በ”አጎብዳጅ ባንዳ” ዳኞች ያስፈርድባቸዋል። “ጸረ ልማት” ብሎ የፍየል ወጠጤ ያዘፍንባቸዋል።
እንቶኔን ያየ … በሚል አገር ወዳዶች ሸሽተው አለቁ። ምሁሩ አገሩን ከዳ። ነጋዴው ኮበለለ። ወጣቱ በኑሮ ጠኔ መጨረሻው በማይታወቅ ስደት የባህር ላይ ሞትን መረጠ። የቻሉ አረብ ምድር ገብተው በግፍ አለንጋ ተጠበሱ። ኢኮኖሚያዊ ቀውሱ የበረታባቸው ራሳቸውን ማጥፋት ጀመሩ። ይህ ሁሉ የማያስደነግጣቸው ህወሃትና ጭፍሮቹ በጥጋብ ያገሳሉ።
ተቀናቃኞቹን በሰበብ ለማላመጥ የተቋቋመው የፌደራል የስነ ምግባርና የጸረ ሙስና ኮሚሽን በቅርቡ በሰጠው ማረጋገጫ ያለ ህጋዊ ቀረጥ ከሚነግዱ ድርጅቶች መካከል ይኸው የህወሃት ድርጅት ግንባር ቀደም ነው። ነገር ግን ጠያቂ የለውም። ለምን ቢባል ባለቤቱ ራሱ አገር መሪ ነውና። ሌባ አገር አስተዳዳሪ ነውና!!
“አስገራሚውና አነጋጋሪው ጉዳይ ህወሃት መቼ ነው ዘርፎ የሚጠግበው?” የሚለው ነው። አንድ ነጻ አውጪ ድርጅት አገር መምራቱ በራሱ ይገርማል፤ ምን አልባትም በዓለም ላይ በነጻ አውጪ የምትገዛ ብቸኛ አገር ኢትዮጵያ ትሆናለች ። በዚህም ላይ ይህ “ነጻ አውጪ” ከፍተኛ አመራሮቹ እንደሚሉት ከበረሃ ጀምሮ ዘርፎ ዘርፎ አለመጥገቡ ያስደንቃል። ከሁሉም በላይ የሚያስገርመው ግን በየቀኑ የጠላቶቹን ቁጥር በሺህዎች እያባዘ ነገ ምን ሊገጥመው እንደሚችል ያለመገመቱ ነው።
እዚህ ላይ አጠንክረን የምንለው ይኖረናል። ህወሃት አንዱን ከሌላው በማጋጨት መሰረት ላይ በተከለው ፖለቲካ የትግራይ ህዝብ የሌላውን ብሔረሰብ ህዝብ ሙሉ በሙሉ እንዲጠረጥርና ራሱን እንዲከላከል እየሰራ መሆኑን እናውቃለን። የማያውቁና መረጃ የሌላቸው ከግምት በላይ ይረዱታል። ይህ ሰይጣናዊ አካሄድ ዋጋው አስቀድመን እንዳልነው “ደም” ነውና ከወዲሁ ማርገቢያ እንዲበጅለት እናሳስባለን።
በቁጥር እየከፋፈሉ በምስጢር ከየአይነቱ በማስታጠቅ የትግራይ ህዝብን ከሌላው ህብረተሰብ ጋር ለማጋደል በምርጫ 97 ወቅት ሟቹ አቶ መለስ የሰጡትን ትዕዛዝ አጠንክሮ መያዝ አሁንም መዘዙ የከፋ ነውና ህዋሃት ከዚህ ተግባሩ እንዲታቀብ እንመክራለን። በወቅቱ “ራስህን ተከላከል፣ ሊያጠፉህ ነው” በሚል በመታጠቅ በየቀበሌው ለመተላለቅ መመሪያ የተጠበቀበት ደረጃ ተደርሶ እንደነበር ለምናውቅ ድርጊቱን ስናስበው ይቀፈናል። ያመናል። ያስበረግገናል። ተከስቶ ቢሆን ኖሮ ጠባሳው ምን ያህል በከፋ ነበር?
የትግራይ ህዝብ እንደ ህዝብ እንደ ማንኛውም የተረገጡ ዜጎች ሁሉ የስርዓት ለውጥ ያስፈልገዋልና ሌላው ህብረተሰብ ከጭፍን ጥላቻ ራሱን እንዲያርቅ እንመክራለን። የትግራይ ልሂቃንም በገለልተኛ ሚዛን በራሳቸው ላይ እንዲሆን የማይፈቅዱት በሌሎች ላይ እየተደረገ መሆኑንን በመቃወም በህዝብ መካከል የተረጨውን መርዝ በማምከን ተግባር ላይ ሊሰማሩ እንደሚገባ ለመጠቆም እንወዳለን። ዙሪያችንን የከበቡን ጠላቶች ይበቁናልና!!
ኢህአዴግ እንደ ገዢ ያለው አቅም ተቦርቡሯል። ሟርት ነው ካልተባለ የኑሮ ብሶት፣ ሌብነትና በሌላው ህዝብ ላይ የሚፈጽመው የግፍ ክምር ሊንደው ተቃርቧል። የሚመካበት የጦር ሃይልም ቢሆን ወገን አለውና አንድ ቦታ ከተፈረከሰ አደጋው የአገር ነው። በቡድን አደራጅቶ መሳሪያ በማደል በጎጥ ወኔ የህዝብን ቁጣና ምሬት መቋቋም የሚታሰብ አይደለምና ህወሃት በመፈክር አታሎ በጨረሳቸው ታጋዮች ደም ላይ የሚደንሰውን ከልክ ያለፈ የጥጋብ ጭፈራ ይግታው። በነጻ አውጪ ስም አገር እየመሩ ዝርፊያ ተራ የማፊያ ተግባር እንጂ አገር እምራለሁ ከሚል ወገን የሚጠበቅ አይደለምና ያደባባይ ዝርፊያ ይቁም!! ኢህአዴግ ሌባ ወይስ አገር አስተዳዳሪ በማለት የሚጠይቁ ሁሉ እውነት አላቸውና ልብ ያለው ልብ ይበል።
በግብር የምናየው ኢህአዴግ ከተዘፈቀበት ችግር ራሱን ከማጽዳት፣ ህዝብ የሚበጀውን እንዲመርጥ መንገድ ከማመቻቸትና አገሪቱን ወደ መልካም ጎዳና ከማሸጋገር ይልቅ፣ ህዝብን በጅምላ “ለሃጫም” እያለ መስደብ የሚያስደስተው ነው። ህዝብን “ጠባብ፣ አሸባሪ፣ ጸረ ልማት፣ …” በማለት መፈረጅ የድል ያህል የሚያስፈነድቀው ነው። ራሱ ስራ ፈት ያደረገውን ትውልድ “ቦዘኔ” ሲልና ሲሳደብ የስኬት ገድል ያስመዘገበ ያህል ይመስለዋል። ከሁሉም በላይ የህወሃት የእጅ ስራ ውጤት የሆኑ አሻንጉሊት ካድሬዎች እንደ ጌቶቻቸው “ለሃጫም” እያሉ ህዝብን ሲሰድቡ ሽልማት ለመስጠት ይሽቀዳደማል። ህዝብ ሲያኮርፍና ሲበሳጭ ይደሰታል። አገሪቱን ባህር አልባ አድርጎ ስለቀረቀረባት ኩራት ደረቱን ይነፋል። በማያገባው ጦርነት ምስኪን ወገኖችን ማሽጨፍጨፉ ልዩ ገድል ሆኖ ይታየዋል። ድንግል መሬት በሳንቲም ሲቸበቸበ ልማት ነው ይላል፡፡ ነዋሪዎችን ለትውልድ ከኖሩበት እያፈናቀለ መሬታቸውን ለውጪ ባለሃብቶች እየሰጠ “እስካሁን ያልሸጥነው መሬት ነው የሚያሳስበን” በማለት በሰው ደም ይቀልዳል፡፡ በዚህ ሁሉ ትዕቢቱ ላይ ንጹሃንን እያሰረ ማሰቃየቱ፣ መግረፉና መግደሉ፣ አሁን አሁን ይፋ የሆነበት የመርዝ ጣጣ ጀብድ ሆኖበታል። በልክ በልኩ የሰራቸውን አሻንጉሊት ተላላኪዎቹ ሰብስቦ በሚሰራው ድራማ መደነሱና ውሸታም አገር አስተዳዳሪ መሆኑ የኩራቱ ሁሉ ኩራቱ ነው። በዚህ ሁሉ ሲደመር ዜሮ በሚሆን ትምክህት ውስጥ ሆኖ አገር መምራቱ በእጅጉ ያሳስበናል፣ ያስጨንቀናል፣ ወደፊት የሚመጣውን ስናስበው እንደ ዜጋ ያስበረግገናል። ለዚህ ነው “ኢህአዴግ ሌባ – ወይስ አገር መሪ” ስንል የጠየቅነው። መልሱን የሚሰጥ ሁሉ እንዳመላለሱ ትግሉን ሊያካሂድ ይገባዋል እንላለን፡፡http://www.goolgule.com/

Sunday, March 9, 2014

በኢንቨስትመንት ስም አፍሪካ ውስጥ የሚደረገውን የመሬት ቅርምት አስመልክቶ

የካናዳ ፓርላማ አባላትና ምሁራንን ያሳተፈ ውይይት ተደረገ
landgrab2


Coalition for Equitable Land Acquisitions and Development in Africa በምህጻረ ቃል CELADA በመባል የሚታወቀው በካናዳ ኦታዋ ውስጥ የተቋቋመ ድርጅት በአፍሪካ እየተኪያሄደ ያለውን የመሬት ቅርምት አስመልክቶ በርካታ የፓርላማ አባላት፣ የተራድኦ ድርጅት ሃላፊዎች የዩኒቨርሲቲ መምህራን በተገኙበት በአፍሪካ በኢንቨስትመንት ስም የሚደረገውን የመሬት ቅርምትና ካናዳ ልትይዘው የሚገባትን ፖሊሲ በተመለከተ  በኦታዋ ፌብሩዋሪ 25 ቀን 2014 ዓም  land grab2የተሳካ ስብሰባ አድርገዋል።
በሚሊየን የሚቆጠሩ በእርሻ የሚተዳደሩ ማህበረሰቦችን አግባብ በሌለው ሁኔታ የማፈናቀሉ ሥራ እጅጉን ተጧጡፎ ያለው በተለይ በአፍሪካ በመሆኑ CELADA የተሰኘው ድርጅት ይህ ጉዳይ አለም አቀፍ ትኩረት ያገኝ ዘንድ የበኩሉን ለማድረግ ጥረት በማድረግ ላይ ይገኛል። ይህ ድርጅት በተለያየ ተቋማት ውስጥ የሚያገለግሉ ካናዳውያን እንዲሁም ከበርካታ አፍሪካ ሀገራት የመጡና  በአህጉሪቱ ውስጥ እየሆነ ያለው ነገር ይመለከተናል የሚሉ ትውልደ አፍሪካ ምሁራንን ጭምር ያካተተ ነው። በዚህ ድርጅት ውስጥ በርካታ ትውልደ ኢትዮጵያውያን ምሁራንም የሚሳተፉበት ሲሆን ከመስራች አባላት አንዱ ታዋቂው የሰብዓዊ መብት ተሟጋች የሆኑት አቶ ኦባንግ ሜቶ ናቸው።
የስብሰባው ዓላማ ድርጅቱን ከፓርላማ አባላትና በሀገሪቱ ውስጥ የፖለቲካ ተጽእኖ ማሳደር የሚችሉና አለም አቀፍ እውቅና ካላቸው ካናዳውያን ጋር ማስተዋወቅ ሲሆን። በዋነኛነትም ይህ ህገወጥ የመሬት ነጠቃና ቅርምት በሚደረግባቸው አገሮች ውስጥ የካናዳ ግብር ከፋይ ሕዝብ ገንዘብ ተጨማሪ የመጨቆኛ መሳርያ በመሆን ለአምባገነን መንግስታት እንዳይውል ለሚደረገው እንቅስቃሴ ድጋፍ ማሰባሰብያም ነበር።
ስብሰባውን በንግግር የከፈቱቱ  የፓርላማ አባል የተከበሩ ሄለን ላቫንዴር ሲሆኑ ለስብሰባው ዝግጅትና ስኬትም ከፍተኛውን አስተዋጽኦ ያደረጉ ናቸው። እርሳቸውም የጉዳዩን አሳሳቢነት አጽንኦት ሰጥተው ከተናገሩ በሁዋላ መድረኩን ለመስራችና የወቅቱ ሊቀመንበር ለሆኑት ለፕሮፌሰር ሮይ ኩልፔፐር  አስተላልፈዋል። ሮይም የስብሰባውን ተካፋዮች አመስግነው በበኩላቸው ይህ ጅምር ተጠናክሮ እንዲቀጥል የሚያስፈልጉባቸውን ጉዳዮች በመዘርዘር የድርጅቱ ማለትም የ CELADA ዓላማና ግብም በመላው አፍሪካ እየተከናወነ ባለው የመሬት ነጠቃና ቅርምት ዙርያ ያጠነጠነ መሆኑን አስረድተው ለእለቱ ተናጋሪዎች እድል ሰጥተዋል።
oየመጀመርያው ተናጋሪ እውቁ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች የተከበሩ ኦቶ ኦባንግ ሜቶ ሲሆኑ ከንግግራቸው ቀደም ሲልም ጥቂት ደቂቃዎች የሚፈጅ በሊቢያ አማካይነት በማሊ ውስጥ የተደረገው የመሬት ቅርምት የሚያደርሰውን አፍራሽ ተጽእኖ፣ የሕዝቡን ቁጣና ተቃውሞ የሚያመለክት ፊልም እንደ መግቢያ ካሳዩ በሁዋላ የችግሩን ጥልቀትና ውስብስብነት በማስረዳት ኢትዮጵያ ውስጥ እየተከናወነ ያለውንም ነገር በመጥቀስ ካናዳ ልትወስድ የሚገባትን አቋም፣ ሊኖራት የሚገባውን ፖሊሲ በማሳሰብ ንግግራቸውን አብቅተዋል። አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ የያዘችው አቋምም የጉዳዩን አሳሳቢነት የሚያመለክት በመሆኑ ካናዳም የምትለግሰውን እርዳታ በዚሁ መነጽር ትመለከተው ዘንድ አሳስበዋል።
የማዳጋስካር ተወላጅዋ የ CELADA አባል የሆኑት ማጊ ራዛፊምህኒ ለበርካታ አመታት ለUNICEF ያገለገሉ ሲሆኑ በማዳጋስካር እየሆነ ያለውን የሀገሪቱ ፖሊሲ አገም ጠቀም የሆኑ እርምጃዎችን ቢወስድም አደጋው የከፋ መሆኑን በመግለጽ እርሳቸውም ተመሳሳይ ጥሪ ለካናዳ ሕዝብና መንግስት አቅርበዋል።landgrab3
በመሬት ቅርምት ላይ ጠንካራ አቋም በመያዝ በተለያየ መስክ ስኬትን ያገኘው የኦክሰፋም ካናዳ ዳይሬክተር የሆኑት ሮበርት ፎክስ በበኩላቸውም የሁኔታውን አሳሳቢነትና አደገኛነት በመግለጽ መሬትም እንደማንኛውም ሸቀጥ ሊሸጥ ሊለወጥ ይችላል በሚል መርህ ሕዝቡን ማፈናቀልና ሀብት ማጋበስ በሚፈልጉ ሰዎች የገንዘብ ፈሰስና ለሀገራቸው ሕዝብ ደንታም በማይሰጣቸው ባለስልጣኖች ግፍ እየተፈጸመ መሆኑንና አብራርተው ምንም እንኳ ችግሩ ዛሬ የአፍሪካ ቢሆንም ነገ ግን ሁላችንንም የሚያስጨንቅ ጉዳይ መሆኑን መዘንጋት የለብንም ብለዋል። በመቀጠልም መሬትን እንደ ተቀማጭ ሀብት የሚያዩት ከበርቴዎች ትላልቅ የእርሻ መሬቶችን በልማት ስም በመግዛት አጥረው ካለምንም ልማት በመያዝ የመሬት ዋጋ የሚያሻቅብበትንና ከፍተኛ ትርፍ የሚያጋብሱበትን ጊዜ እየጠበቁ ነው በማለት በአፍሪካ ድሀ ገበሬዎች ላይ የሚሰራውን ግፍ ተናግረዋል። ለዚህም ምሳሌያቸው ሞዛምቢክ ነበር። ሞዛምቢክ ውስጥ ለውጭ ባለሃብቶች ከተሰጠው መሬት ውስጥ 70% የሚሆነው ታጥሮ የመሬት ዋጋ ውድ የሚሆንበትን ጊዜ የሚጠብቅ ሸቀጥ ሆኗል ብለው ነበር። በዚህም ምክንያት መልማት ያለበት መሬት በከበርቴዎች ተይዞ ሳለ ሚሊየኖች ግን በረሃብ ያልቃሉ የሚል አንድምታ ያለውን አስተያየታቸውን ሰጥተዋል። እንደ ደቡብ ሱዳን ያለ ገና የጸና መንግስትና ፖሊሲ የሌለበት ሃገር ውስጥ በሀገሪቱ ውስጥ መልማት ካለበት መሬት ውስጥ 10% በውጭ ኢንቨስተሮች ተይዟል። ይህ እጅግ በጣም ሰፊ መሬት ነው።
landgrab4ኢትዮጵያን እንደምሳሌ በጠቀሱበት ንግግራቸውም የ140 የእግርኳስ ሜዳን የሚያህል ስፋት ያለው የአበባ እርሻ ልማት ውስጥ በርካታ ወጣት ሴቶች በቀን ሰራተኛነት ተቀጥረው በአለም ላይ ያሉ ኬሚካሎችን ሄርቢሳይድ፣ ፈንጂሳይ፣ ኢንሴክቲሳይድ፣ ባክቴሪሳይድ ወዘተ በቆዳቸው በሳንባቸው እየሳቡ ያለ እድሜአቸው የሚረግፉ እንዲሆኑ መገደዳቸውን በመግለጽ የመሬት ቅርምቱ በተለይም በሴቶች ላይ ያስከተለውን አደገኛ ተጽእኖ ለተሰብሳቢዎች ገልጸዋል። ተጋንኖ የሚነገረው የእርሻው ኢንቨስትመንት የስራ እድል ይፈጥራል፣ የምግብ ምርት ያሳድጋል ለማህበራዊ አገልግሎቶች አመቺ እድል ይሰጣል የሚባሉት መደለያዎች ፈጽሞ ከእውነት የራቁ መሆናቸውን ሲገልጹ በመሰረቱ ዘመናዊ ቴክኖሎጂ የሰራተኛ ቁጥርን በመቀነሱ እንጂ በስራ እድል ፈጣሪነቱ አይታወቅም ብለዋል።
ኢንቨስተሮችም የሀገሬውን ህዝብ የመቀለብም ሆነ በሀገር ውስጥ የሚሸጥ ምግብ የማምረት ግዴታም የሌለባቸውና እንዲያውም የእርሻ መሬትን በአብዛኛው ለምግብ የሚሆን ሳይሆን ለስኳርና የነዳጅ ዘይት ለማምረቻ የሚጠቀሙበት መሆኑን ገልጸዋል።  ኮካኮላ የስኳር ምርቱን በዚህ ጉዳይ ከሚጠቀሱ አምራቾች ባለመግዛት የጥፋቱ ተካፋይ ላለመሆን የወሰደው እርምጃ አበረታች መሆኑንም ለተሰብሳቢው ገልጸው የመሬት ቅርምቱ ለአጭርጊዜም ይሁን ለረጅም ጊዜ ሕዝባዊ ጠቀሜታ እንደሌለው አክለዋል።  በመጨረሻም ካናዳም ሆነች የበለጸጉ ሀገሮች በዚህ ጉዳይ ላይ የሚወስዱት አቋም ወቅታዊም አስፈላጊም መሆኑን አበክረው ተናግረዋል።
ሌላው ተናጋሪ ብሩስ ሙር ሲሆኑ የ Canadian Hunger Foundation (CHF) ዳይሬክተር የነበሩና በተለያዩ አንጋፋ ድርጅቶች ውስጥ በቦርድ አባልነት በዳይሬክተርነት ያገለገሉና በአሁኑ ወቅት የ ‘North South Institute’ የቦርድ ሰብሳቢ፣ የ Forum of Democratic Global Governance (FIM) የቦርድ አባል እንዲሁም የ ‘Transparency International’ አባል ናቸው። ብሩስ ሙር በአስከፊው የኢትዮጵያ ድርቅ ወቅት ለውጪ ሰዎች መጓጓዝ አስቸጋሪ በሆነ ሁኔታ እስከ ኮረም ድረስ ዘልቀው የችግሩን ስፋትና ክብደት ከተመለከቱ በሁዋላ ለካናዳ መንግስትና ለዐለምም የችግሩን መጠን ያሳወቁ በዚህም ሳቢያlandgrab5 ከፍተኛ እርዳታ ለኢትዮጵያ እንዲደርስ አስተዋጽኦ ያደረጉት ሲሆኑ  በዚሁ የመሬት ቅርምትና የለጋሽ አገሮች ሚና በተለይም ካናዳ ሊኖራት ስለሚገባው ፖሊሲ አጠር ያለ ግን ጥልቅና ጠበቅ ያለ አስተያየት ሰንዝረዋል።
እንደ እርሳቸው አባባልም የከተማዎች የከፋ ድህነት የገጠሩ ጉዳይ ችላ መባሉን አመልካች ነው በማለት ተናግረዋል። በማከልም ከ 2000 -2010 ዓ ም በሰነድ የሚታወቅ  የመሬት ይዞታ ዝውውር 200 ሚሊየን ሄክታር ሲሆን ከዚህ ውስጥ 134 ሚሊየኑ በአፍሪካ ውስጥ ነው። ይህም ጉዳዩ ለ አፍሪካ እጅግ አሳሳቢ መሆኑን ያመለክታል። የምግብ እጥረት ከተከሰተ በሗላ ሳውድአረብያ ከ ኢትዮጵያ ብዙ መሬት ገዝታ ነበር በጣም የሚገርመው በ2009 ዓም ሳውዲ የመጀመርያ ምርቷን ከኢትዮጵያ በወሰደችበትና ሕዝብዋን በመገበችበት ወቅት ወርል ፉድ ፕሮግራም አምስት ሚሊየን የ ኢትዮጵያ ረሃብተኞችን መግቦ ነበር። ይህ የሚናገረው ትልቅ እውነት አለ፣ ይህ የሚያመለክተው ትልቅ ክፍተት አለ በማለት የተሰማቸውን ገልጸዋል።
landbrab3ሌሎች ተሰብሳቢዎችም አስተያየታቸውን የሰጡ ሲሆን ይህ ጥልቅና ውስብስብ ጉዳይ ለፓርላማ አባላት ቀርቦ ካናዳ ልትወስድ ስለሚገባት አቋም በቂ ግንዛቤ ማስጨበጡ እንደ አማራጭ ቀርቧል። በተለይም የግብር ከፋዮች ገንዘብ ለሕዝብ መፈናቀል ተጨማሪ መሳርያ እንዳይሆን ካናዳውያን ኢንቨስተሮችም ይህንን በመረዳት እንደዚህ ያሉ አገሮች ውስጥ የሚደረግ ኢንቨስትመንት የሚያስከትለውን ተጽዕኖና የሚያመጣውንም አደጋ ልብ እንዲሉ እንዲደረግ ሁሉም የድርሻውን እንዲያደርግ በየአቅጣጫው መረባረብ አስፈላጊነቱን ጠቅሰዋል።
በመዝጊያ ንግግራቸው ላይ የ CELADA ሊቀመንበር ፕሮፌሰር ሮይ በዚህ የመሬት ቅርምት ዙርያ በዚህ ጉባዔ ላይ የተገኛችሁ በጉዳዩም ላይ በቂ እውቀት ያላችሁ ጠበብቶች አላችሁና የኤክስፐርት ምስክርነታችሁን  ለፓርላማ አባላት በማቅረብ ይህንን ውስብስብ የሆነ ነገር በማስረዳት እንደምትተባሩ አምናለሁ።  በየአቅጣጫው በያዝነው ስራ እንበርታ ለዚህ አንገብጋቢ ችግር መፍትሄ ለማስገኘት የየበኩላችንን እናድርግ በማለት ተሰብሳቢዎቹንና ለዚህ ስብሰባ ስኬት አስተዋጽኦ ያደረጉትን ሁሉ አመስግነው የእለቱ መርሃግብር በዚሁ ተጠናቋል።http://www.goolgule.com/

Saturday, March 8, 2014

ህዝብን በመጨቆን ሀገርን መምራት አይቻልም!

የፖለቲካ ስርአትና የአንድ ሀገር እድገት ቀጥተኛ የሆነ ግንኙነት አላቸዉ። አንድ አገር ትክክለኛ ባልሆነ የፖለቲካ አገዛዝ ይበለፅጋል ብሎ ማሰብ የዋህነት ነው። ሃገራችን ኢትዮጵያም የወያኔ መንግስት ባነገሰው የተዛባ አገዛዝ ሳቢያ ህዝባችን ለከፋ ችግር መዳረጉ በገሃድ የሚታይ ሃቅ ነው። ታዲያ በዚህ ወያኔያዊ የተዛባ አገዛዝ እንዴት ከችግር ልንወጣ እንችላለን? አገራችን ኢትዮጵያ ምንም እንኳ የጥንት ስልጣኔ ባለቤት ብትሆንም በአየር ንብረትም ሆነ በተፈጥሮ ሀብት ጥሩ ከሚባሉት ሀገሮች አንዷ ብትሆንም እንደ እድል ሆኖ መሪዎች ግን አልተሳኩላትም። ለምን ኢትዮጵያ የረሃብ አገር ተባለች ለምን ዜጎቿ ተደስተው በነጻነት መኖርን እንደተመኙ ህልማችዉ ከንቱ ሆነ? ብዙዎች የሞቱላት አገር  አንገታቸዉ ለሰይፍ ደረታቸዉ ለጥይት የሰጡላት አገር ኢትዮጵያ በህዝቦቿ ታታሪነት አለም ያደነቃት ለምን ተዋርዳ ተገኘች!?
እውቀትን፣ ስልጣኔን፣ ጥበብን ለአለም ያበረከተች ሃገር ዛሬ ላይ በቤተ መንግስቱም ይሁን በቤተ ክህነቱ የተማሩ ሰዎችን ናፊቂ ሆናለች፡፡ ምክንያቱም ምሁራኑ በሃገራቸው ሊኖሩ የሚያስችላቸው እድል ስላልተመቻቸላቸው ሁሉም ጉዟቸው ወደ ውጭው አለም ስደት በመሆኑ ነው፡፡ በብዙ ሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ህዝቦች በረሃብ አለንጋ የሚገረፍባት ሲኦልም ከሆነች ዘመናትን አስቆጥራለች፡፡ እንዲሁም መለያየትን ወይም ዘረኝነት በግልፅ የምትሰብክ የዘረኞችና የጎሰኞች መሰማሪያ ሜዳ ሆና ክፉ አድራጊዎች እንደፈለጉ እየዘፈኑባት ትገኛለች፡፡ በቃል ከሚወራ ዲሞክራሲ፣ እድገት፣ ብልፅግና በስተቀር በተግባር የሚታይ አንዳችም መልካም ነገር የማናይባት አሳፊሪ ሃገር ሆናለች፡፡ በደልና ጭቆና በዝቷል ድህነትና ጉስቁልና ከመቼዉም በባሰ ተንሰራፍቷል እስርና ሰቆቃ ተራ ነገሮች ሆነዋል። በአሸባሪዎች ስም እራሳቸዉ ቦንቦች አጥምደው ህዝቦች እየፈጁ ሰላማዊ ዜጎች በአሸባሪነት እየተፈረጁ ለስቃይ እየተዳረጉ ነዉ። ዛሬ በሃገራችን አርሶም ሆነ ነግዶ መኖር አይቻልም። መኖር የሚቻለዉ ኢሕአዴግ ልማት ነዉ የሚለዉን መዝሙር በመዘመር ብቻ ነዉ።
የሁሉም ነገር መሰረት እንደሆነ የሚታመንበት ትምህርትን ብንመለከት እንኳ ትምህርት በኢትዮጵያ ሞቷል ለማለት በሚያስደፍርበት ጀረጃ ደርሷል። ከተለያዩ ሀገሮች ያለምንም ጥናት በኩረጃ የሚያመጧቸዉ የትምህርት ፖሊሲዊች ምንም እንኳን ብዙ ወጭ ቢወጣባቸዉም የሚሰራባቸዉ ለአንድ የትምህርት መንፈቀ አመት ብቻ ነዉ። በኢትዮጵያ ወያኔ ልማት ነዉ በሚል አባዜ የተለከፈ ትልቅ ቦታ ይሰጠዋል። ልማታዊ መንግስት፣ ልማታዊ፣ ዘፋኝ፣ ልማታዊ አስተማሪ፣ ልማታዊ የእምነት ዘርፍ፤ ወዘተ… በማለት ከወያኔ ጎን ካልተሰለፉ ኢ-ልማታዊ/ ሽብርተኛ የሚል ስም ይሰጣቸዋል ይህንንም ተመርኩዞ ለእንግልትና ለእስራት ይዳረጋሉ። ‘‘ዶሮ ጭንቅላቷ ላይ ስጋ ተሸክማ ወይ አትበላዉ ወይ አታስበላዉ‘‘ እንደተባለዉ ማንንታቸዉና እዉቀታቸዉን ትተዉ የወያኔ መዝሙር ብቻ በመዘመር የሚኖሩ ጥቂት ሰዎች በኢትዮጵያ ዉስጥ የማይጠበቅ ኑሮን ሲኖሩ ይታያሉ። የሚላስ የሚቀመስ በጠፋበት በአሁኗ ኢትዮጵያ ዘይትና ሽንኩርት ለመግዛት እንኳ አንድ ግለሰብ የወር ደሞዙ በቂ አልሆን ባለበት ግዜ እንዴት ጥቂት ባላባቶች ፎቆችና ቪላዎች ይገነባሉ? የህዝብ ንብረት ካአልተዘረፈ በቀር እነሱ ከየት አመጡት? ወይስ ኢትዮጵያ ሲባል እነሱን አይጨምርም?  ከአዉሮፓ መንግስታት የሰዉ ፍጥረት በረሃብና በህክምና እጥረት ህይዎቱን ለማዳን ተብሎ የሚላከው ገንዘብ እነሱ ዉስኪ ሲራጩበት ሊሞዚንና አሉ የተባሉ ምርጥ በአለም ከታወቁ ካምፓኒዎች የተሰሩ መኪናዎች ሲገዙበት ለህዝቡ ድህነት  ባህላችን መሆኑን ዘላለም በመተረክ ይኖራሉ። በስብሰባ ፍቅር ብቻ የተለከፉ ባለስልጣናቶቻችን ስብሰባዉን እንደጨረሱ አበል በሚል ስም ገንዘብ ይከፋፈላሉ። ይህንን እንስሳዊ የሆነ አስተሳሰብ አልደግፍ ያሉት ደግሞ ፀረ ልማትና አሸባሪ በሚል ስም ለእንግልት ይዳረጋሉ። አሸባሪነት ለምን የፖለቲካ መጠቀሚያ ሆነ? አሁን የታሰሩት ዉብ የኢትዮጵያ ልጆች አሸባሪዎች እንደሆኑ የሁል ግዜ ለጆሮ የሰለቸ ንዝንዝ ነዉ፤ ስለዚህ አሸባሪነት ለአምባገነናዊ መንግስት አለመዘመር ከሆነ ወደድክም ጠላህም መኖርም ሆነ መስራት የሚቻለዉ ይህንኑ ስትዘምር ብቻ ነዉ። ለዚችው በሺህ የሚቆጠሩ የነፃነት ታጋዮች የታሰሩባት; ረሃብ፣ ጦርነት፣ሞትና ግድያ መለያየት የሰፈነባት፤ ዜጎችዋ በሰላም ወጥተው በሰላም ለመግባት ለሚሸማቀቁባት ሃገር ለታሪኳ ሁለ መበላሸት ተጠያቂው ወይም ተወቃሹ ገዳዩ የወያኔ አገዛዝ ነው፡፡
ስለዚህ የኢትዮጵያ የድንቁርና ፣ የመለያየት፣ የጦርነት፣ ያለማወቅ፣ የግድያ ጭለማ እንዴት ይወገድ ወደሚለው መፍትሄ ሃሳብ ስንመጣ፤ በኢትዮጵያ ያለው የክፉ ነገሮች ሁሉ ጨለማ የሚወገደው በወለደቻቸው እና ባሳደገቻቸው ኢትዮጵያውያን ሃገር ወዳድ ልጆቿ ነው፡፡ ሀገራችን ኢትዮጵያ ሰላም ናፍቋት የሰላም ያለህ እያለች ነው፡፡ ውድ ልጆቿም አረመኔው የወያኔ መንግስት በየጊዜው እየቀሰፈባት እረፍትን ትሻለች፡፡ በመሆኑም ይህን አምባገነናዊ  የወያኔ ስርዐት በማስወገድ  ; በሃገራችን የእውቀትና የሰላም ብርሃን እንዲፈነጥቅ ; ዜጎቿም በሰላም ወጥተው በሰላም እንዲገቡ;  መብቶቻቸውም ሊጠበቁ የሚችሉበትን እንዲሁም የምንፈልገውን ነፃነት፣ እድገት፣ፍትህ፣ ዲሞክራሲ በኢትዮጵያ ለማምጣት የራሣችንን ቁርጠኝነት ማሣየት ይጠበቅብናል!!!
ድል ለጭቁኑ ህዝብ!!!http://ecadforum.com/

Friday, March 7, 2014

ከባዶ ጭንቅላት ባዶ እግር ይሻላል! (ግንቦት7)

Ginbot 7 weekly editorialየባህርዳር እና አካባቢው ሕዝብ ከባዶ ጭንቅላት ባዶ እግር ሺህ ጊዜ እንደሚሻል አካሉን ብቻ ሳይሆን ህሊናውንም ለትግራዩ ነፃ አውጪ ህወሓት ባርነት ላስገዛው “የብሔረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ብአዴን)” እያለ እራሱን ለሚጠራው ድርጅት መሪዎች ተናገረ።
ባርነት ክፉ ነው። በባርነት ላይ የጭንቅላት ባዶነት ሲታከልበት ደግሞ አለምነው መኮንንን የመሰሉ የብአዴን መሪዎችን ይፈጥራል። የብአዴን መሪዎች ለጌታቸው ህወሓት ያላቸውን ታማኝነት ለማሳየት ራሳቸውን ማዋረዳቸው ሳያንስ እንወክለዋለን የሚሉትን ሕዝብ በጅምላ መስደባቸው ብአዴን እንደ ድርጅት የሚገኝበት የተዋረደ ደረጃ ያሳያል።
ህሊና ያለው ባርያ ዛሬ ነፃ ባይሆንም ወደፊት ነፃ የመውጣት ህልም አለው። ዛሬ በጉልበተኛ የባርያ አሳዳሪ ነፃነቱን ቢያጣም የህሊና ነፃነቱን ያላስደፈረ ባርያ ለነፃነት መታገሉ የማይቀር ነው። እንደ ብአዴን መሪዎች በታማኝ ባርያነቱ እየፈነጠዘ ያለ ባርያ ግን ነፃ ሰው የመሆን ህልሙንም ጭምር አጥቷል። እንዲህ ዓይነቱ ባርያ በአካልም፤ በመንፈስም ባሪያ ነው። ነፃ ሰው የመሆን እድል የለውም።
የአማራ ሕዝብ ብአዴንን የመሰለ አሳፋሪ ድርጅት በታሪኩ ገጥሞት አያውቅም። በፋሽስት ጣልያን ወረራ ጊዜ ለጠላት ያደሩ ባንዶች እንኳን ከዛሬዎቹ ብአዴኖች የተሻለ ክብር ነበራቸው። እነሱም ከዛሬዎቹም በተሻለ በጌቶቻቸው ጣሊያኖች ይሰሙ ነበር። በገዢዎቹ ለመወደድ የራሱን ሕዝብ የሚዘልፍ፣ የሚሰድብና የሚያዋርድ እንደ ብአዴን ያለ አዋራጅ ድርጅት በአማራ ምድር አልታየም።
ለዚህም ነው የባህርዳር እና አካባቢው ሕዝብ የብአዴንና የወያኔን አፈናዎችን በጣጥሶ የካቲት 16 ቀን 2006 ዓ.ም. ቁጣውን በባዶ እግሩ አደባባይ በመውጣት የገለፀው። እግር ባዶ መሆኑ ጭንቅላት ባዶ የመሆኑ ያህል የሚያሳፍር አይደለም። ድህነት ወንጀል አይደለም። ነፃ አዕምሮና የሕዝብ ይሁንታ ያገኘ አስተዳደር ካለ ድህነትን ማሸነፍ ይቻላል።
ግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ፣ ፈታኝ ሁኔታዎችን ተቋቁመው የየካቲት 16 ቀን 2006 ዓ.ምን ሕዝባዊ ተቃውሞ ላደራጁና በተቃውሞውም ለተካፈሉ ሁሉ ያለውን አክብሮት ይገልፃል። ሕዝብ ብሶቱን የሚገልጽበት ሕዝባዊ ተቃውሞ ማደራጀትና መምራት መቻል ትልቅ ነገር ነው። ሕዝባዊ ተቃውሞዎች ወደ ሕዝባዊ እምቢተኝነት የማደግ እድል አላቸው። ስለሆነም ግንቦት 7 ለባህርዳሩ ሕዝባዊ ተቃውሞ አደራጆችና ተሳታፉዎች “እንኳን ደስ ያላችሁ” በማለት የትግል አጋርነቱን መግለጽ ይሻል።
ግንቦት 7፣ ብአዴንን ከአባላቱ ለይቶ ማየት ይሻል። ከዚህም በተጨማሪ የብአዴንን ከፍተኛ አመራር ከሌላው ለይቶ ይመለከታል። ብአዴን ነፍሳቸውን ሳይቀር ለወያኔ በሸጡ ሰዎች የሚመራ፤ ነፃ የመውጣት ተስፋ የሌለው ራሱ ባርያ የሆነ ድርጅት ነው። አባላቱ ግን ከዚህ የተለዩ ሊሆኑ እንደሚችሉ ግንቦት 7 ያውቃል።
ግንቦት 7፡ የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ከዚህም በፊትም ደጋግሞ እንደገለጸው፤ በተለያዩ ጊዜያት ራሳቸውን ከወያኔ ባርነት ነፃ ለማውጣት በወሰዱት እርምጃ መስዋእትነት የከፈሉ የብአዴን አባላት መኖራቸውን ያውቃል። ግንቦት 7 ለእነዚህ ቆራጦች ትልቅ አክብሮት አለው። ዛሬም ህሊናቸውን ሙሉ በሙሉ ያልሸጡ የብአዴን አባላት አሉ ብሎ ያምናል። እነዚህ ወገኖቻችን ራሳቸውን ነፃ ለማውጣት የግል፣ የወገንና የአገር ግዴታ አለባቸው ብሎ ያምናል።
ስለሆነም ዛሬም ይህንን አጋጣሚ ተጠቅመን ጥሪዓችንን እናድሳለን።
የብአዴን አባላት ሆይ!!! የገዛ ራሳችሁን፣ የአማራን ሕዝብ እና ኢትዮጵያን እያዋረደ ካለው ብአዴን ተላቀቁ፤ አሊያም እውስጡ ሆናችሁ ድርጅቱን ግደሉት። የብአዴን መኖር ለወያኔ ካልሆነ በስተቀር ለማንም አይበጅም። ነፃነት ካለ ድህነትን በሥራ ማሸነፍ ይቻላል። ሰው ባርያ ሆኖ በሀብት ቢንበሸበሽ ምን ይፈይድለታል?
የብአዴን አባላት ሆይ!!! ወደ ህሊችሁ ተመለሱ። ራሳችሁንም የበደላችሁትን ሕዝብ የመካስ እድል አድል አላችሁ ተጠቀሙበት። ይህንን ባታደርጉ ግን ለገዛ ራሳችሁ ፀፀት፤ ለልጆቻችሁ ሀፍረትን የምታወርሱ መሆኑን አትዘንጉ። ወያኔ መሸነፉ በጭራሽ የማይቀር መሆኑን እያወቃቸው በድህረ ጣልያን ወረራ ባንዶች ያገኙትን ምህረት እናገኛለን ብላችሁ አታስቡ።
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!http://ecadforum.com/

Thursday, March 6, 2014

የገዢዎቻችን መጨረሻና የተከተላቸው ሀቅ


የመጨረሻውን በማያውቁት ያዘቀዘቀ ጨለማ መንገድ እየተውዘረዘጉ መሪዉን በማስተካከል ከመጨረሻው ለመድረስ የሚጣድፉ መሪዎች፤ የድንቁርና ኒሻን ይገባቸዋል። በፈጠሩት የራሳቸው የመኖሪያ የገዢነት መኮፈሻ “ሀቅ” ተጀንነው በመቀመጥ፤ ፈንጠር ብሎ ርቆ ሌላውን ማየት ባለመቻላቸው፤ የተከተላቸውውን ሳይውቁት እጃቸውን ሠጥተዋል። የተለዬ የመሰለ የራስ “ሀቅ” የብዥታ ጭጋግ፤ ሩቅ ማየትን ነፈጋቸው። ማስተዋልን ከአእምሮ መዝገባቸ ሰወረው። መደናበርን አነገሠባቸው። ካይናቸው ፈት በተገተረው የእብሪታቸው መነፅር ዓለምን ግቢ ውጪ እያሉ በማስገደድ፤ ያለው የሌለ ሆኖ፣ ከተጨባጩ ይልቅ በምኞታቸው ዓለም ሲዳክሩ፤ የቆሙበት መሬት ከዳቸው። ከሕዝቡ መሆናቸው ቀርቶ ሕዝቡ የነሱ አገልጋይ ሎሌ ሆነና፤ የነሱ መኖሪያና የሕዝቡ መኖሪያ በአጥር ተለያዬ። መኖሪያቸው ዓለማቸው ሆነና ከሕዝቡ ዓለም ወጡ። ረጋ ብለው ያሉበትን ለመመርመር ጊዜ አጠራቸው። ያጠራቸው ጊዜ ጥሏቸው ሄደ። እናም ባሉበት ቆመው ቀሩ።
መንግሥትን ለመምራት፤ ከፍተኛ ብስለትና ጥንቃቄ ታላቅ መሣሪያ ናቸው። “ጠላት” እና “ወዳጅ” ብሎ በመፈረጅ፤ ወዳጅን መጥቀምና ጠላትን መጉዳት በሚሉት ጋቢ ከተሸፈኑና በዛሬ ወንበር ከረጉ፤ ነገ የራሷን ወዳጅና ጠላት አበጅታ ከጎን ብቅ ስትል፤ የሚይዙትን ታሳጣለች። ለሁሉ ጥሩ ነገሮች ባለቤት ወዳጅ ብሎ የፈረጀውን ወገን ያቀሰሰና ለሁሉ ነገር መጥፎ ባለንብረት፤ ጠላት ብለው የፈረጀውን ሠፈር የወነጀለ ገዢ፤ መጨረሻው አያምርም። የኛ ገዢዎች እንዲያ ነበሩ፤ አሁንም እንዲያ ባይ በጀርባችን ተሸክመናል። ፍርሃትን በሕዝብ በመዝራት ለመግዛት የተነሱት ገዥዎቻችን፤ ራሳቸው በፍርሃት ተውጠው ከሕዝቡ ራቁ። ሕዝቡን ጠላት አድርገው ፈረጁት። መውደቃቸው የጊዜ ጉዳይ ሆነ።
ገዢዎች ከአመጣጣቸው ማንነታቸውን መገንዘብ ይቻላል። አንድ የተለዬ ወገን ቦድነው የመጡ ክፍሎች፤ ያንኑ ምርኩዝ ይዘው እስከመጨረሻው ሲሄዱ አየናቸው። ያ አመጣጣቸው ለተከተሉት ፍልስፍናና የአስተዳደር መመሪያቸው መነፅራችን ነው። እናም እምነታቸውና ተግባራቸው ይኼንኑ አንፀባረቀልን። እብሪት የጉልበተኞች መመኪያ ሆነች። እብሪተኞች ዘለዓለማዊ ነን አሉ። በሥልጣን ላይ ሲሆኑ የረጋ አእምሮን መንገድ መጥረግ አቆሙ። በስሜትና በፍላጎት መብራት ጨለማውን ለማለፍ ተደናበሩ። የተፈጥሮ ሕግን ጠምዝዘው ሊዘውሩ ሞከሩ፤ ራቁታቸውን ተጋልጠው ቆማ። ንጉሡ ባሉበት ደነዘዙ፣ ደርጋማው መንግሥቱ ጭራውን ቆልፎ ሐራሬ ምሽግ ውስጥ ተደበቀ። ያሁኖቹ ደግሞ በተራቸው የት ይገቡ ይሆን?
እኔ ራሴ ባየኋቸው ሶስት የተከታተሉ ገዢዎቻችን፤ ይህ ሀቅ በጣም ጎልቶ ታይቷል።
በመጀመሪያ ንጉሠ ነገሥቱ፣ ራሳቸው በፈጠሩትና ባመኑበት “ከአምላክ የተቀባሁ ነኝ!” ባይ እብሪት፤ ሕዝቡን ለሳቸው የተሠጠ አገልጋይ በማድረግ፤ ጊዜ ሲለውጥና የዓለም ፖለቲካ መልኩን ሲቀያይር፣ ከኋላችን የነበሩትና አዲስ ነፃ የወጡ የአፍሪቃ ሀገሮች ቀድመውን ሲሄዱ፣ በሀገራችን በሚሠጠው ትምህርት የዓለምን ግስጋሴ የተገነዘበው የተማረው ክፍል የስልጣኔ ናፍቆቱ ሲያድግ፣ የዓለም ህዝብ የኑሮ ደረጃ ከፍ እያለ ሲወጣና የኛ ኑሮ ባለበት ከመዘፍዘፉ የተነሳ የኋሊት ጉዞ ሲጀምር፤ ያመኑበት መለኮታዊ ገዢነታቸው ዓይናቸውን አውሮ ማየት ተሳናቸው። እናም የግል ጠባቂ ብለው ያደራጁት የጦር ኃይል ያለበት የኑሮ ሁኔታ አላስጨነቃቸውም። ሁሉም በተዓምርና በሳቸው ምኞት ብቻ የሚመራ አድርገው ሲያዩት፤ ታሪክ ያልተገናኙ አድርጎ ከሥራቸው መሬት ካዳቸው። እናም ሲነቁ በጨለማ ተውጠው የሚጨብጡትን አጡ። ተነድተው የታሪካቸው የመጨረሻ ምሽት፤ ባልታወቀበት ቦታ ሆነ።
የኢትዮጵያ ሕዝብ በየካቲት ፲ ፱ ፻ ፷ ፮ ዓመተ ምህረት ባንድነት ተነስቶ የራሱን መንግሥት ለመመሥረት ሲዘጋጅ፤ ባቋራጭ የገባው የወታደሮች ቡድን አብዮቱን አኮላሸው። በሂደቱም አንድ አምበገነን ወጥቶ፤ የፈራቸውን፣ የጠላቸውን፣ በሕልሙ የሚያስበረግጉትን፣ ለሱ ሠጥ ለጥ ብለው፣ አሜን ጌታዬ ብለው ያልተገዙለትን በማሰር፣ በመግደልና በተለያዬ መንገድ በማጥፋት ሊገዛ ተነሣ። ሰዎችን እንደ ጠጠር በፈለገበት ማስቀመጥና ማዞር፣ ማሽከርከርና መጣል የዕለት ተዕለት ተግባሩ ሆነ። ራሱን ኢትዮጵያ፣ የሱን ተቃዋሚ የኢትዮጵያ ተቃዋሚ፣ እሱን ያልተቀበለ ኢትዮጵያን ያልተቀበለ በማድረግ ሊገዛን ፈለገ። በመሐል ቤት ራሱ በሚያልመው መነፅር ሀገሪቱንና የሀገሪቱን የፖለቲካ ሀቅ እየተመለከተ ከህዝቡ ተለዬ። ሕዝቡ ለማያባራ ጦርነት ልጆቹን መገበር እምቢ አለ። ሕዝቡም መጥፎ ነገር እንደነካ እንጨት ራቀው። እናም ብቻውን ቀረ። ዙሪያውን ሲከበበ፤ ጅራቱን ቆልፎ እንደሚሮጥ ፈሪ ውሻ፤ እግሬ አውጪኝ ብሎ ወደ ሐራሬ ፈረጠጠ።
በቦታው የተተካው ወገንተኛ አምባገነን ሕገወጥ መንግሥት ደግሞ፤ ራሱን ልዩና ብቸኛ ሆኖ የተፈጠረ አዳኝ በማድረግ፤ ለሁሉም ነገር እሱ ብቻ መፍትሔ አዋቂና ራሱ ብቻ ትክክለኛ ሆኖ በመቅረብ፤ እሱም እንደቀደሙት ሁሉ፤ ሕዝቡ ገዢው የሚለውን የሚሰማ፤ ገዢው የሚያዘውን የሚፈፅም አድርጎ እየገዛ ነው። በዚህ ተግባሩ ከሕዝቡ ተነጥሎ ተንሣፏል። ቀደም ያሉ ገዢዎቻችንን ያስቆጧቸው ወገኖች በሥራቸው እንዳቆጠቆጡት ሁሉ፤ በአዲሱ ገዥዎቻችን ላይም የሕዝብ ወገን የሆኑ ተቃዋሚዎች በየቦታው ተኮልኩለዋል። አሁንም ያለበትን ሀቅ ሳይሆን፤ የሚያልመውን እየተቀበለ እውነቱን ማየት አቃተው። ጊዜያዊ የመሰለያ አምስት ለአንድ ጥፋሮውንና ወታደራዊ ጥንካሬውን የማይበገር ምሽግ አድርጎ ወስዶታል። የሚታየውን በሀገሪቱ የሠፈነ የኅብረተሰብ ችግርና የኑሮ ሁኔታ እንዳያይ የራሱ ቅንጦትና ምቾት አውሮታል። እንደቀድሞዎቹ ራሱን ዘለዓለማዊ አድርጎ ወስዷል። እንደቀደሙትም ተራውን እየጠበቀ ነው።
ለኔ፤ የወገንተኛው አምባገነን ሕገወጥ ቡድን ነገ፤ ጉዳዬ አይደለም። ጉዳዬ፤ የኛ የኢትዮጵያዊያንና የሀገራችን የኢትዮጵያ ነገ ነው። እንደትናንቶቹና ዛሬ በዙፋኑ ላይ ቁጢጥ እንዳለው፤ ሌላ አምባገነን ገዢ እንዲተካ አልፈልግም። የእስከዛሬው አንገፍግፎኛል። ይህ ምን ጊዜም መረሳት የለበትም። ግፉ እንዲቀጥል በምንም ሁኔታ መንገድ አሠልጢዎች መሆን የለብንም። ታዲያ እኛ ምን ማድረግ አለብን? ብለን ራሳችንን መጠየቅ አለብን። መልሱን ደግሞ ነገ ሳይሆን ዛሬ መሥጠት 
አለብን። እጆቻችን አጣጥፈን መጪውን መጠበቁ፤ በተዓምር ኢትዮጵያዊያን የምንፈልገውን ሀቅ እንዲከተል አያደርግልንም። እናም እኔ ኃላፊነቴን መወጣት አለብኝ። ብቻዬን የምጥረው የትም እንደማያደርስኝ አውቃለሁ። ችግሩ የሁላችን የኢትዮጵያዊያን በሙሉ ነው። መፍትሔውም በሁላችን በኢትዮጵያዊያን ጥረት የሚገኝ ነው። እናም ለርስዎና ለመሰሎችዎ ጥያቄ አለኝ። ያሁኑ ወገንተኛ አምባገነን ሕገወጥ መንግሥት ሲወገድ ምን እንዲተካ ነው የሚፈልጉት? ይህ እንዴት ሊመጣ ይችላል? የኔና የርስዎ፤ የያንዳንዳችን አስተዋፅዖ ምንድን ነው ይላሉ?
የኔን ላጋራዎ
አሁን በሀገራችን ያለው ወራሪ ዓይነት ወገንተኛ አምባገነን ሕገወጥ መንግሥት ነው። ሀገራችንን ወደ ከፍተኛ አደጋ እየመራት ነው። የነገው የሀገራችን ዕጣ አደገኛ ሁኔታ ላይ ወድቋል። እኛ የዚህን ወገንተኛ አምባገነን ሕገወጥ መንግሥት የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ መከታተላችን፤ ኢትዮጵያዊያን የምንፈልገውን ሕዝባዊ አስተዳደር አያመጣልንም። የራሳችንን ተግባር ነው መወሰን ያለብን። ሀገር አቀፍ የሆነ ሁሉን ኢትዮጵያዊያንን ያጠቃለለ የሽግግር መንግሥት ተቋቁሞ፤ የዴሞክራሲያዊ አሠራር መሠረቱ ሲጣል ብቻ ነው አስተማማኝ የሆነ የወደፊት የሚኖረን። ለዚህ ደግሞ ሁላችንን የሚካትት ራዕይና ተልዕኮ ሊኖረን ይገባል። ይህ መንግሥት በሕዝቡ ግፊም ሆነ ራሱ በውስጡ በመንቀዙ መውደቁ አሌ አይባልም። ጥያቄው መቼ? ብቻ ነው።
በኔ እምነት፤ ኢትዮያዊነታችንን የተቀበልንና የሕዝቡን ትግል የምንደግፍ ሁሉ፤ በመጀመሪያ ማመን ያለብን፤ የምንፈልገው ተከታይ ሥርዓት፤ ለምናደርገው ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑን ነው። ምን እንፈልጋለን? በአንድነት ሆነን ተሰባስበን በምናደርገው የአደረጃጀት ተሳትፎ፤ በግል ወንም በቡድን ሥልጣን መያዝ ወይንም አንድን ርዕዩተ ዓለም የማራመድ ጉዳይ ቦታ የለውም። ቦታ ያለው፤ በአንድነት ሁላችን፤ ሀገራችን ከዚህ ወራሪ ከመሰለ አስተዳደር ነፃ ወጥታ፤ ሕዝቡ የወደደውን መንግሥት ለማቋቋም መሸጋገሪያ መንገድ ማዘጋጀቱ ነው። ሕዝቡ የወደደውን ከመምረጡ በፊት የመሸጋገሪያ ወቅት አለ። እናም የኛ የትግሉ ተሳታፊነት በትግል ዕሲውቶቻችን ይመራል። እናም የትግል ዕሴቶቻችን የሚከተሉት ናቸው፤
ሀ) ሕዝቡ ሉዓላዊነቱ ተከብሮለት፣ 
ለ) የሀገራችን አንድነት ተጠብቆ፣ 
ሐ) የሕግ የበላይነት ሠፍኖና፤ 
መ) የእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ዴሞክራሲያዊ መብቶች ተከብረው፤ 
የሚኖሩባት ሀገር እንድትሆን የሚያመቻች የሽግግር መንግሥት መቋቋሙ ነው።
እኒህ አራት የትግል ዕሴቶች ሁላችንም በታጋይ ክፍል የተሠማራነው የምንጋራው ስለሆነ፤ በነዚህ ዙርያ መሰባሰቡ ወደ አንድ ያመጣናል። እናም እነኚህን አራት የትግል ዕሴቶች የተቀበልን ኢትዮጵያዊያን፤ በኢትዮጵያዊነታችን መሰባሰባችን ግዴታ ነው።።
ታሪክ ጥሏቸው ሲጓዝ ባሉበት ቆመው የተያዙትን ገዢዎቻችንን እናጢን። ኃላፊነቱ የኛ ነው ብለን እስካልጨበጥንና ግዴታችንን እስካልተወጣን ድረስ፤ ሌሎች በሚያመጡት ለውጥ የኛን ፍላጎት እንዲሟላ እጃችንን አጣጥፈን መቀመጡ፤ በቀላሉ ጅልነት ነው። ከአፄው የከፋና የከረፋ ደርግ ተከተለ። ከደርግ የገማና የተግማማ ወገንተኛ አምባገነን ሕገወጥ ተከተለ። የከፋ አይመጣም እያልን የተሻለ ባጠገባችን አላልፍም አለ። የሚቀጥለውስ የመዓት ነው። እኛ ካላወቅንበት! ምን ይላሉ?http://www.ethiofreedom.com/