WE NEED FREEDOM!

WE NEED FREEDOM!

Friday, January 31, 2014

“ኢትዮጵያውያን ለምንድን ነው የውጭ ገበሬዎች የሚያስፈልጓቸው? ምንድን ነው ይዘውልን የሚመጡት?” አቶ ግርማ

"አንድም ሰው ከቀዬው እንዲፈናቀል አልተደረገም" ሚኒስትር ዴኤታ
displaced anuaks
  • “ሰፋፊ የእርሻ ኢንቨስትመንቶች እንደታሰቡት ውጤታማ አልሆኑም” መንግሥት
  • መንግሥት የውጭ ባለሀብቶች የመሬት ቅርምት ኢትዮጵያን አይመለከትም አለ
የውጭ ባለሀብቶች በግብርና ኢንቨስትመንት ላይ ለመሰማራት ሰፋፊ የእርሻ መሬቶችን ወስደው እያለሙ እንጂ፣ መሬት ለመቀራመት ብለው ወደ ኢትዮጵያ አልገቡም ሲል ግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
“መሬት መቀራመት ኢትዮጵያን ጭራሽ አይመለከታትም፤” ሲሉ የግብርና ሚኒስትሩ አቶ ተፈራ ደርበው ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አስታውቀዋል፡፡
ሚኒስትሩ የመሥሪያ ቤታቸውን የስድስት ወራት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ለፓርላማው ማክሰኞ ዕለት ሲያቀርቡ፣ ሰፋፊ መሬቶች ወስደው በግብርና ላይ ኢንቨስት እያደረጉ ስለሚገኙ የውጭ ባለሀብቶች ትክክለኛ ማብራሪያ እንዲሰጡ በተጠየቁበት ወቅት ነው ይህንን ያሉት፡፡
በፓርላማ ብቸኛው የተቃዋሚ ፓርቲ ተወካይ የሆኑት አቶ ግርማ ሠይፉ ለሚኒስትሩ ባቀረቡት ጥያቄ፣ የውጭ ኩባንያዎች ሰፋፊ መሬቶች አንዳንዶቹ እንደሚሉት ቤልጂየምን የሚያህል መሬት ተሰጥቶ እየተካሄደ ስላለው ኢንቨስትመንት በቂ ማብራሪያ በሪፖርቱ ስላልተካተተ እውነቱ ሊብራራ ይገባል ሲሉ ጠይቀዋል፡፡
በሰፋፊ መሬቶች ላይ የሚካሄድ የግብር ኢንቨስትመንት ችግር የለውም ያሉት አቶ ግርማ፣ በመንግሥት ላይ እየቀረበ ያለው ክስ አርሶ አደሮች እንዲፈናቀሉ ማድረጉ አንዱ ነው ብለዋል፡፡
forced displacementየውጭ ኩባንያዎቹ ብድር የሚያገኙት ከኢትዮጵያ መንግሥት መሆኑን የመገናኛ ብዙኃን እየዘገቡ መሆኑን በማስታወስ፣ “በኢትዮጵያ ገንዘብና በኢትዮጵያ መሬት ለምንድን ነው የውጭ ኩባንያዎች መጥተው የሚያለሙት?” በማለት ጥያቄ አቅርበዋል፡፡
“ኢትዮጵያውያን ለምንድን ነው የውጭ ገበሬዎች የሚያስፈልጓቸው? ምንድን ነው ይዘውልን የሚመጡት?” በማለት አቶ ግርማ የሚኒስትሩን ማብራሪያ ጠይቀዋል፡፡
በጉዳዩ ላይ ተጨማሪ ጥያቄ ያቀረቡት ብቸኛው የግል ተመራጭና የምክር ቤት አባል ዶ/ር አሸብር ወልደ ጊዮርጊስ ሲሆኑ፣ በሰፋፊ የግብርና መሬት ላይ በሚካሄደው ኢንቨስትመንት የምዕራባዊያን ኩባንያዎች እንዲሳተፉ ለምን የማስተዋወቅ ሥራ አይሠራም በማለት፣ የህንድና የቻይና (የምሥራቁ የዓለም አገሮች) ኩባንያዎች የጐላ ተሳትፎ ሚዛኑን መጠበቅ ይገባዋል የሚል መልዕክት ያለው ጥያቄያዊ አስተያየታቸውን አቅርበዋል፡፡
በጉዳዩ ላይ የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ኃላፊዎች በጋራ ምላሽ የሰጡ ሲሆን፣ ሚኒስትር ዴኤታው አቶ ወንድይራድ ማንደፍሮ በሰፋፊ መሬቶች ላይ ለሚካሄድ የግብርና ኢንቨስትመንት ሲባል አንድም ሰው ከቀዬው እንዲፈናቀል አልተደረገም ብለዋል፡፡
ሁለቱም ምስሎች በጋምቤላ አካባቢ ከሳተላይት የተወሰዱ ናቸው፡፡ ቀያዮቹ ነጥቦች በሙሉ በመሬት ነጠቃ ከቀያቸው የተፈናቀሉና ቤታቸው የፈረሰ አባወራዎችን ሲሆን ቢጫዎቹ ደግሞ ተፈናቃዮቹ በግዳጅ የሰፈሩበትን ነው፡፡
ሁለቱም ምስሎች በጋምቤላ አካባቢ ከሳተላይት የተወሰዱ ናቸው፡፡ ቀያዮቹ ነጥቦች በሙሉ በመሬት ነጠቃ ከቀያቸው የተፈናቀሉና ቤታቸው የፈረሰ አባወራዎችን ሲሆን ቢጫዎቹ ደግሞ ተፈናቃዮቹ በግዳጅ የሰፈሩበትን ነው፡፡
“የመንግሥትና የሕዝብ ሀብት የሆኑ ነፃ መሬቶችን ብቻ ነው ለሰፋፊ የግብርና ኢንቨስትመንት የምንሰጠው፡፡ ማንም ከቀዬው አልተፈናቀለም፤” በማለት አስረድተዋል፡፡
በሰፋፊ መሬቶች ላይ የሚደረግ የግብር ኢንቨስትመንት ከፍተኛ የገንዘብ አቅም እንደሚጠይቅ የተናገሩት ማኒስትር ዴኤታው፣ ከዚህ ጋር የተያያዙ ችግሮች መኖራቸውን ግን አልሸሸጉም፡፡
በሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱም ሆነ በባለሀብቶቹ ቀደም ብሎ ተይዞ የነበረው እምነት ኢንቨስትመንቱ ቀላል እንደነበር፣ ነገር ግን በተግባር ሲታይ ጊዜ የሚወስድና አቅም የሚጠይቅ እንደነበር ገልጸዋል፡፡
በአሁኑ ወቅት ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ለባለሀብቶቹ የሚሰጠውን የመሬት መጠን እየቀነሰ እንደሚገኝ፣ በአጠቃላይ ግን ትልቅ አቅም የሚፈጥር ዘርፍ እንደሚሆን አብራርተዋል፡፡
በዚህ ዘርፍ በፌዴራል መንግሥት ፈቃድ የተሰጣቸው ባለሀብቶች 43 መሆናቸውን አስረድተው፣ ከእነዚህ ውስጥ 15 የሚሆኑት ብቻ የውጭ ኩባንያዎች ናቸው ብለዋል፡፡ በመሆኑም በዘርፉ በአብዛኛው እየተሳተፉ የሚገኙት የአገር ውስጥ ባለሀብቶች መሆናቸውን አስረድተዋል፡፡
ሚኒስትሩ አቶ ተፈራ ደርበው በበኩላቸው በኢትዮጵያ ውስጥ መሬት መቀራመት የለም ብለዋል፡፡
አሁን ባለው የዓለም የዕድገት ሁኔታ የገንዘብ አቅም ያለው በምሥራቃውያን አካባቢ መሆኑን፣ ምዕራባውያኑ በዘርፉ ያልተሳተፉት የአቅም ችግር ስላለባቸው እንደሆነ ሚኒስትሩ ጠቁመዋል፡፡
“የመሬት መቀራመት ጉዳይ እየተነሳ ያለው ከዚሁ የዓለም ጂኦ ፖለቲካ አካባቢ ነው፡፡ ከምሥራቅ የዓለም አገሮች ወደ አፍሪካ እየመጣ ያለ ኢንቨስትመንት ስለማይወደድ ነው፤” ብለዋል፡፡
ሚኒስትሩም ሆነ የሥራ ባልደረቦቻቸው የውጭ ኩባንያዎቹ እያገኙ ስላለው ከፍተኛ ብድር ግን ማብራሪያ ሳይሰጡበት ታልፏል፡፡
የግብርና ሚኒስቴር የስድስት ወራት የሥራ አፈጻጸም እንደሚያስረዳው፣ በ2006 ዓ.ም. የመኸር ወቅት 253 ሚሊዮን 805 ሺሕ 340 ኩንታል ምርት ሊገኝ እንደሚችል፣ ይህም ካለፈው ዓመት ዘጠኝ በመቶ መጨመሩን ነው፡፡ http://www.goolgule.com/why-ethiopia-needs-foreign-farmers/

Thursday, January 30, 2014

የታመቀው የኢትዮጵያውያን ምሬት፡ የሕይወት ማሽቆልቆልና በፍርሃት መሽማቀቅ አፋጣኝ መፍትሄ ይሻል

January 29, 2014
ኢትዮጵያ በሕወሃት ዘመነ አመራር የታወቀችባቸው ብዙ ነገሮች ሊኖሩ ይችላሉ። ብዙ “እንዴ!”የሚይሰኙ ጥሩ አሳቦችም ፈልቀዋል – አፈጻጸማቸው እትይለሌ ቢሆንም። ከነዚህም መካከል መሠረተ ልማት፡ በጤናና በትምህርት መስኮች መሻሻሎች መታየታቸው ወዘተ መልካም ይነገርላቸዋል – የቢል ጌትስን የራስ ተጠቃሚነትና ኢምፓየር ግንባታ ወደጎን ትተን! በዕጦት ደረጃም በሀገራችን የስብዓዊ መብቶች አለመክበር፣ የፍትህ አለመኖርና ለአብዛኛው ሕዝባችን የምግብ ዕጦት ዋና ዋና ተጠቃሽ ችግሮች ናቸው።
Prime Ministers Katainen and Hailemariam (Credit: ERTA)
Prime Ministers Katainen and Hailemariam (Credit: ERTA)
ለምሳሌም ያህል፡ ሕገ መንግሥቱ በአንቀጽ 30 ስላማዊ ስልፍ የማድረግንና መንግስትን መቃወምን ግልጽ ቢያደርግም፡ እሁድ ዕለት የኢትዮጵያን መሬት ለሱዳን ለመሰጠት ለመቃወም: ለሚመለተው አሳውቀው ስላማዊ ስልፍ ለማዘጋጀት ተፍ ተፍ ሲሉ የአዘጋጁ የስማያዊ ፓርቲ አመራር አባላት ጎንደር ውስጥ ተይዘው ታስረዋል። በተመሳሳይ መንገድ ትግራይ ውስጥም የአረና አመራሮች ሕዝቡን ቀሰቀሳችሁ በሚል ውንጀላ አዲግራት ውስጥ አመራሩና አባሎቹ ክፉኛ ተደብድበዋል – ጉዳት የደረሰባቸውም ሕክምና ለመሻት ተገደዋል። ይህንኑ አስመልክቶ፡ አንዱ ተደብዳቢ መምህር አብርሃ ደስታ የሚከተለውን ጽፏል፡
    “ህወሓቶች በተግባራቸው ሊያዝኑ ይገባል። ህዝብን ፖለቲካ እንዲያውቅና ራሱ ከጭቆና እንዲከላከል ለማገዝ በምንሞክርበት ግዜ መንግስት ወደ ተራ የሽፍትነት ተግባር መሰማራቱ የሚያስደምም ነው … እኛ ለህዝብ ነፃነት ነው የምንታገለው። ትግላችን ሰለማዊ ነው። ወታደርና ፖሊስም የለንም። እኛ ያለን ህይወት ነው። ያለችንን ህይወት ለህዝብ ደህንነት ስንል መስዋእት አድርገናል። በህዝብ ፊት ተደብድበናል። በፖሊስና አስተዳዳሪዎች ፊት ተደብድበናል። እኛ መክፈል ያለብን ህይወትን ነው።”
ይህ በግልጽ የሚታየው የዛሬይቱ ኢትዮጵያ የስብዓዊ መብቶች አንጸባራቂ ሥዕል ነው። ይህ ሁኔታ በየቀኑ በተለያየ መልኩ ሀግሪቱ ውስጥ እየተካሄደ ያለ የመንግሥት ሕገ ወጥነት ነው!
በኤኮኖሚው መስክ ያለው ችግር ግዙፍ ነው። ድህነት ከመቀረፍ ይልቅ፡ ሥር እየስደደ መሆኑን ብዙዎች ያማርራሉ። ለጥቂቶች ግን ሀገሪቱ ምድራዊ ገነት ሆናለች። ሕዝቡ እየተደበደበም፡ በየቀኑ አልዋጥ ባይ ፕሮፓጋንዳ በግድ እየተጋተ ነው!
በዚህ ሁኔታ ውስጥ ነው ለብዙዎቹ የአዲስ አበባ መሽቀርቀር እንደአጠቃላይ የሃገሪቱ የልማትና ዕድገት መለኪያ ተደርጎ እንዲወሰድ የተቀነባበረ ጥረት የሚድረገው። የምርጫ ዘመን በመቃረቡ፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኢትዮጵያ በቅርቡ ስንዴ ለውጭ ገብያ ሻጭ ልትሆን ነው በማለት ጥር 18፣ 2014 አርሲ ሆነው ማስማታቸው ልብ ሊባል ይገባል። ነገር ግን ኢትዮጵያ በልማት ገና ሀ ሁ … ላይ ናት – በምግብ 40 በመቶ የሚሆነውን ሕዝቧን በቀን ሶስቴ ሳይሆን፡ አንዴም መመገብ ያልቻለች አገር ናት! ይህ በመሆኑ አይደል እንዴ የምዕራቡ ዓለም፡ በቋሚነት ከ10 በመቶ በላይ የሆነውን የኢትዮጵያ ሕዝብ ክዓመት ዓመት በዓለም አቀፍ እህል ዕርዳታ ሕይወት በመስጠት ላይ ያለው?
ከሁሉም ጎልቶ የሚነገርለትና የሕወሃት ስዎችም ቶሎ የሚስፈነጠሩበት የአገሪቱ ከትላልቅ ጦርነቶች መላቀቋ ነው። ስለዚህም የሕወሃት ስዎችና ደጋፊዎቻቸው በመመጻደቅ ሲናገሩ መስማቱ የተለመደ ሆኖአል። በዚህም መነሻነት፡ እንዲህ ይላሉ: ባለፉት 20 ዓመታት፡ ሕወሃት ለረዥም ዘመናት አገሪቱን ያደሙትን ጦርነቶች አቁሞ ልማት ላይ እንድታተኩር አደረገ የሚባለው በብዛት ይሰማል። የሕወሃት ስዎችም ይህ በተደጋጋሚ እንዲነገርላቸው ብዙ ጥረቶች አድርገዋል፡ እያደረጉም ነው። እራሳቸውም በተደጋጋሚ እራሳቸውን በዚህ ሲያሞካሹ ይሰማል፤ ለውጭ የፕሮፓጋንዳ ድርጅቶችም ይህንን እንዲያስተጋቡላቸው፡ ከፍተኛ ክፍያዎችን በየጊዜው ፈጽመዋል።
እስከዛሬ አጥግቢ ግንዛቤ ያላገኘው ግን፡ ድሮም ሆነ ዛሬ የጦርነቶች አጋጋይ ሕወሃት መሆኑ ነው። የኤርትራንና የትግራይን መገንጠል ጉዞ በተግባር ሲተረጉም ኖረ። ቀኑ ደርሶ ጅብሃ ሲገነጠል፡ ሕወሃት ባዶ የሥልጣን ወንበር ስለታየው፡ ኢትዮጵያዊነትን መረጠ። በትግል አጋሩ ጅብሃ ዘንድ ይህ እንደክህደት እንዳይታበት – በስላም ሂዱ፡ ኢትዮጵያ ከእናነተ ስላም እንጂ ሌላው ቀርቶ የባህር በር እንኳ አያስፈልጋትም አለ። ይህንን አስመልከቶ፡ በየካቲት ወር 1994 ስብሃት ነጋ ለዓለምስገድ አባይ በስጡት ቃለ መጠይቅ የሕወሃት ቀደምት ፓሊሲ መገንጠል ሆኖ እስክ 1985 መቆየቱን ያረጋግጣሉ። ከቃለ መጠይቁ ውስጥ በጣም አሰገራሚው ነገር ግን፡ ብዙ የሕወሃት ተዋጊዎች ኢትዮጵያዊነትን ገና ድሮ አሽቀንጥርረው የጣሉ በምሆናቸው፡ ዛሬም ቢሆን በተለይ ከአማራ ጋር ኢትዮጵያዊ ሆኖ መገኝትን በሙል ልብ አለመቀበላቸውን ነው ያመላከቱት [See Identity Jilted: Re-imagined Identity (1998)]።
ያለፈው አልበቃ ብሎ፡ ዛሬም ሕወሃት ሀገሪቱ ውስጥ ሽብርና ፍርሃት በማንገስ የውስጥ ግጭቶችን በመተንኮስ: የተለያዩ ብሄረስቦችን አባሎች በማፈናቀልና ችግሮችን በማባባስ ተጠቃሚ ለመሆን ሲምክር ይታያል – ድ/ር ቴድሮስ ፍጹም “እኔ ያለሁበት ፓርቲ ውስጥ ይህ አይደረግም!” ብለው ዝናቸውን አጋልጠው ቢገዘቱም። ነገሩ ግን፡ ዛሬም በምሥራቅ በተለያያዩ የኦሮም ክፍሎችና ኢትዮጵያውያን ሶማሌዎች መካከል፡ በደቡብም እንዲሁ በተለያዩ ጎሣዎች መካከል፡ አማራንና ኦርሞችን በማጋጭት፡ ጥላቻና መቃቃርን በዜጎች መካከል ለመፍጠር ብዙ ሲሞክር ቆይቷል። አንዳንድ ቦታዎችም፡ ለምሳሌ ቦረና፡ ተሳክቶለት ስሞኑን የብዙ ዜጎች ደም ፈሷል፤ ሕይወትም ተቀጥፏል። ቤት ንብረቶችም ተደምስሰዋል። ሌላው ቀርቶ፡ የሕክምና ባለሙያ የነበሩት የአገር አስተዳደር ሚኒስትሩ – የዛሬው የሃይማኖትች ጉዳይና የጸረሽብር ኤክስፐርቱ ዶ/ር ሽፈራው ተክለማርያም – ኬንያ በሥጋቷ ምክንያት (2012ን በማስታወስ) ልተቀስቅሳቸው ብትሞክርም፡ ነገሩ አውቆ የተኛ ቢነቀንቁት አይሰማ ሆኖ እሳችውም እንደክረምት ድብ ክፉኛ አሸልበዋል።
ለማንኛውም፡ በዓለም ላይ እንደሕወሃት የተሳካለት የለም – ዕድሉን ሃገራችንን ለማሻሻል በሚገባ አልተጠቀመበትም እንጂ! ስለሆነም ክሥራ ይልቅ ፕሮፓጋንዳ፡ ዕውነትን ተናግሮ ችግሮችን በጋራ ከመፍታት ይልቅ፡ ሁሉንም ስው ማሞኘት እንችላለን በሚል ትዕቢት ብዙ የሚያሳፍሩ ተግባሮች ሲያከናወን ይታያል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ፡ በበጎነታችው ለኢትዮጵያ ሕዝብ ደጉን የሚመኙ የውጭዎቹ የፖለቲካ፡ የዲፕሎማሲና ኅብረተስባዊ መሻሻሎችን አራማጆች ይህንን የሕውሃትን የሰላም ማስፈን የዋህ መስል ቅጽል በአመኔታ የሚጋሩት በሁለት ተክፈለው ይታያሉ፡ –
(ሀ) በእውነትም ጦርነትና የንጹሃን ዕልቂት መቆሙን፡ ኢትዮጵያ ክድህነት ተላቅቃ ማየት የሚሹ ወገኖች፤
(ለ) ጊዘው የበለጸጉት ሃገሮች ወደታዳጊ ሀገሮች ውስጥ ዘልቀው በመስፋፋትና በኢኮኖሚ ትብብር ስም የራሳቸውን ኤኮኖሚያዊ፡ የበላይነት ማቆየት የሚሹበት፡ ፖለቲካዊና ስትራተጂካዊ ጥቅሞቻቸውን የሚያበራክቱበት በመሆኑ፡ ከላይ ከተጠቀሱት ጋር ተዳብረው፡ የሕወሃትን ገድል መተረኩ፡ ለሚሹት ዓላማ አንድ ጥቅም ትስስሮሽ መፍጠር የሚያስችል መሣሪያ አድርገው የሚጠቀሙበት ወገኖችም እዚሀ ውስጥ ተስልፈዋል።
ከላይ የተመለከቱት ከተለያየ አግጣጫ ተነስተው ሁለቱም አንድ የሚገናኙበት መጋጠሚያ፡ ስለኢትዮጵያ በጎ ነገር እንዲስተጋባ ማድረጋቸው ነው። በተለይም በሁለተኝው ክፍል የሚገኙት፡ በተቻለ መጠን ስለኢትዮጵያ በጎውን በማጋነን፡ የሕወሃትን የስብዓዊ መብቶች ጽልመት፡ ጎስኝነት፡ ሙሰኝነት የሚሸፋፍን አመለካከት በምዕራባውያንም ሆነ ምሥራቃዊ ሚዲያዎች ላይ በጊዜው ያስደስኮሩላቸዋል።
በተጨማሪም፡ እነዚህ ሀገሮች ለኢትዮጵያ ግዙፍ ዕርዳታ መፍሰሱን ይደግፋሉ። ነገር ግን ይህ ዕርዳታ በብዙ መስኮች – በተለይም በግብርናው – መስክ የሀገሪቱን ችግሮች፡ በምግብ ምርት እራስን ከማስቻል ይዘት ስሌለው፡ ትኩረታችውም ሆነ ጥረታቸው – በዘለቄታ ሀገሪቱን ከምግብ ዕርዳታ ተመጽዋች ነጻ ለማድረግ አላስቻለም። በመሆኑም፡ እየተደረገ ያለው፡ ትላንት እንደነበረ ሁሉ ዛሬም ኢትዮጵያ አንድ ሶስተኛ መንግሥታዊ በጀቷን በዓለም አቀፍ ዕርዳታ ተመጽዋችነት ላይ የተመሰረተ ሆኖ የውስጥና የውጭ ፖሊሲዋን በማክራየት እንድትቀጥል አስገዳጅ ሁኔታ ተፈጥሮባታል።
በአሁኑ ወቅት፡ በተለያዩ ምክንያቶች (የስብዓዊ መብቶች አለመከበር ችግር፡ የየራሳቸው የሀገሮቹ የኢኮኖሚ ችግሮች) መንስኤነት፡ ከለጋሽ ሀገሮች በቀጥታ የሚገኝው ዕርዳታ በክፍተኛ ድረጃ ቀንሷል (ክአሜሪካና እንግሊዝ በስተቀር)። በዚህም ምክንያት የዓለም ባንክ ለኢትዮጵያ የሚስጠውን ብዙውን የዕርዳታና ብድር ጫና ድርሻ ተሸካሚ ሆኖአል።
ለምሳሌ፡ ሌላው ቀርቶ ስብዓዊ ዕርዳታን እንኳ በተመለከተ፡ 12 የአውሮፓ ኅብረት ሀገሮች (እንግሊዝን አይጭምርም) በ2012 ለኢትዮጵያ በባይላተራል መንገድ ለዕርዳታ ያዋጡት €24 ሚልዮን ሲሆን፡ በ2013 ይህ መዋጮ ወደ €12.4 ሚልዮን ወርዷል። ከነዚህም መካከል ትልቁን ቅናሽ ያደረገችው ጀርመን ናት – ከ€8.2 ሚልዮን ወ €4.2 ሚልዮን ዝቅ በማድረግ። በመሆኑም፡ከዚህም ከዚያም አስባስቦ የበጀት ምንጮች በማስባስብና ተጨማሪ ምክንያቶች በመፍጠር (ነፍስ ወክፈ መልሶ ማቋቋም) በ2013 እንዳደረገው፡ የአወሮፓ ኮሚሽን በ 2011-2013 12 ሚልዮን ኢትዮጵያውያን ለመርዳት እንዲቻል €130 ሚልዮን ለግሷል።
አሁን ለሁሉም ለጋሾች ከባድ የሆነው “የልማት” ዕርዳታውም እንዲሁ በበዙ ጥያቄዎች ላይ መውደቁ መሆኑ ይሰማል።
በዓለም ዙሪይ ያለፉው ሩብ ምዕተ ዓመት የልማት ጊዜ በመሆኑ፡ ብዙ ታዳጊ አገሮች ከፍተኛ ተጠቃሚ ሆነዋል። ኢትዮጵያ ይህ ዕድል ቢገጥማትም፡ መሣሪያ ያነገቡት የሕወሃት ሰዎችና አጫፍሪዎቻቸው ግንባር ቀድም ተጠቃሚዎች የሆኑበት ሥርዓት በመዘርጋቱ፡ የትላንቱ ጦረኞችና የዛሬዎቹ የስላም ደጋፊ-መስል የአንድ ብኄረስብ ሰዎች፡ ሆን ብለው ዕኩልነትን የሚጻረር የፖለቲካ፡ የኤኮኖሚ፡ የደህንነትና ማኅበራዊ ፓሊስዎችን በኢትዮጵያ በማካሄድ ላይ ይገኛሉ።
ይህ ግን ዘላቂ መሠረት ስሌለው፡ ዛሬ የኤኮኖሚው የጥንድ ዕድገት ውደሳው ጋብ ብሎ፡ ሀገራችን የመንግሥት ብልግናና የሃስት ፕሮፓጋንዳ ከሚመገቡት መካክል ወድቃለች። በዚሁም ምክንያት (ሽፋኑ የውሃ ዕጥርረት፡ ድርቀት፡ የሃይማኖትና የብኄረቦች አለመቻቻልና ግጭቶች ላይ ቢመካኝም)፡ ተደጋጋሚ ዓለም አቅፍ ጥናቶችኢትዮጵያ ከሚወድቁት የአፍሪቃአገሮች (Failed States) መካከል ተደምራ፡ የወደፊት ጽዋዋ አስፈሪ እንደሚሆን ቀንደኛ ደጋፊዎቿ ድምዳሜ ላይ መሆናቸውን በግልጽ የምንሰማበት ዘመን ላይ ደርስናል።
ድሮስ ቢሆን፡ የሕዝብ ዓመኔታ ያጣ መንግሥት፡ መሣሪያውን ደግኖ በኅይል ለመግዛት ከመሞከር ውጭ ምን አማራጭ አለው? ጊዜው የጥላቻ፡ የክፋትና የቂም በቀል በመሆኑ፡ በአንድ በኩል፡ የሕወሃት ስዎች ዘረፋ ላይ የተሰማሩ ሲሆን፡ በሌላ በኩል ደግሞ፡ የኢትዮጵያውያንን ስብዓዊ መብቶች በመግፈፍና መርገጣቸውን በማባባስ፡ ሃገሪቱን ወደ ቀውስ ጎዳን እየገፉ ናቸው። በዚህ ሁኔታ ውስጥ እንዴት ዕድገት ይኖራል?
እንዲያውም፡ የራሱን የአገዛዝ ዘመን ለማራዘም ሲል፡ የኢትዪጵያ ሕዝብ ፍላጎትና አመለካከት ሳይጠየቅ ኤርትራን በፊርማው እንድትገነጥል ያደረገ፡ አገሪቱን የባሀር በር ለማሳጣት የደፈረ የመንግሥታዊ ባህልና ኃላፊነትና ግንዛቤ የሌለው ሕወሃት፡ ለሱዳን የኢትዮጵያን መሬት ቆርጦ ለመስጠት ዝግጅት ላይ መሆኑ ሕዝቡን በቃ! የሚል ድምዳሜ ላይ ማድረሱ አያጠራጥርም!
በዓለም ታሪክ ውስጥም ሕወሃት “ታዋቂ” የሚሆነው፡ ራሱን ሥልጣን ላይ ለማቆየት፡ የሀገርን ልኡላዊነትና መሬት ቆርሶ ለጎረቤት ሀገርና ለከፍተኛ ብድር ስጭና ገንዘብ ለዋጭ አሳልፎ የሚሰጥ በመሆኑ ነው።
ዛሬም ሆነ ነገ፡ ለሀገራችን ዘላቂው መፍትሄ ግን መንግሥት የሕዝብን ፍላጎት ለማክበር መቻሉና ለዚህም ተጠያቂነት ያለበት ሥርዓት መዘርጋቱ ነው። ይህንን ለማድረግ፡ አሁንም ትንሽ የተስፋ መስኮት አለ – የሕውውሃት ስዎች ኃላፊነት የሚስማቸው ቢሁን። ይህ ለሕወሃትና ግብረአበሮቹ ተቀባይ ሳይሆን ቢቀር፡ ቀሪው ምርጫ ሕዝቡ እየተረገጠ መቀጠል፡ ወይንም እነርሱ ከመድረኩ መወገድ ነው።
እስካሁን በዚህ ድህረ ገጽ ይህንን አሳብ አላራመድንም ነበር። የሁኔታው አስከፊነት ግን አሁን የወቅቱ አስፈላጊ እርምጃ አድርጎታል!http://ecadforum.com/Amharic/archives/10852/

Sunday, January 26, 2014

የወያኔ የውሸት ዘገባዎች ሲጋለጡ

January 26, 2014
Ginbot 7 weekly editorial“ኦክስፋም” በመልካም ሥራቸው ከታወቁ ትላልቅ ዓለም ዓቀፍ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች አንዱ ነው። በቅርቡ አንድ መቶ ሀያ አምስት አገሮችን ያካተተ ከምግብ አቅርቦትና አጠቃቀም ጋር የተያያዘ ጥናት ውጤት ይፋ አድርጓል። ጥናቱ አራት ዝርዝርና አንድ አጠቃላይ አመላካቾች አሉት።
1. አመላካች አንድ: የምግብ እጥረት
ይህ አመላካች “በየአገሮቹ ምን ያህል ለበላተኛው የሚበቃ ምግብ አለ?” የሚለውን ይለካል። በጥናቱ ውጤት መሠረት በምግብ እጥረት እጅግ የተጎዱ የመጨረሻዎቹ አስር አገሮች የሚከተሉት ናቸው: – ቡሩንዲ፣ የመን፣ ቻድ፣ ኢትዮጵያ፣ ማዳጋስካር፣ ናይጄሪያ፣ ላኦስ፣ ባንግላዴሽ፣ መካከለኛዉ አፍሪካ ሪፑብሊክ እና ህንድ። ኢትዮጵያ አገራችን ከመጨረሻ አራተኛ ናት።
2. አመላካች ሁለት: ለምግብ የመክፈል አቅም (Affordability)
ይህ አመላካች “የአገሩ ሕዝብ በአገሩ ዋጋ ምግብ ገዝቶ ለመብላት ምን ያህል አቅሙ ይፈቅድለታል?” የሚለውን የሚመልስ ነው። አሁንም ከመጨረሻ እንጀምር። አንጎላ፣ ዚምባቡዌ፣ ቻድ፣ ጉያና፣ ኢትዮጵያ፣ ናይጄሪያ፣ ኮንጎ፣ ኬንያ፣ ጋምቢያ እና ኢራን የየአገሩ ሕዝብ ምግብ መሸመት የሚቸገሩባቸው አገሮች ናቸው። አገራችን ኢትዮጵያ ከመጨረሻ አምስተኛ ናት።
3. አመላካች ሶስት: የምግብ ጥራት
ይህ የምግብ ይዘትንና የአያያዝ ንጽህናን የሚመለከት ሲሆን ኢትዮጵያ፣ ማዳጋስካር፣ሞዛምቢክ፣ ቻድ፣ ቶጎ፣ ዛምቢያ፣ ማሊ፣ ናይጄሪያ፣ ባንግላዴሽ፣ ሌሶቶ ከመጨረሻው እስከ አስረኛ ደረጃ ይዘዋል። ኢትዮጵያ በምግብ ጥራት የመጨረሻዋ አገር ናት።
4. አመላካች አራት፡ የሰውነት ውፍረት እና የስኳር በሽታ
ይህ አመላካች ከልክ ያለፈ ውፍረት ዓለም ዓቀፍ የጤና ችግር እየሆነ በመምጣቱ የገባ አመልካች ነው። ኢትዮጵያ ከፍተኛ ጥሩ ውጤት ያመጣችሁ በዚህ አመላካች ብቻ ነው። ኢትዮጵያ አብዛኛው ሕዝቧ ቀጫጫ ነው፤ የስኳር በሽታም እንደሌላው አገር የተስፋፋባት አገር አይደለችም።
5. አማካይ ውጤት
የእነዚህ አራት አመላካቾች ድምር ውጤት አጠቃላይ ውጤትን ይሰጣል። በአጠቃላይ ውጤት: ቻድ፣ ኢትዮጵያ፣ አንጎላ፣ ማዳካስካር፣ የመን፣ ቡሩንዲ ናይጄሪያ፣ ሞዛምቢክ፣ ዚምባቡዌ፣ ሴራሊዮን ከመጨረሻ እስከ አስረኛ ወጥተዋል። ኢትዮጵያ ከመጨረሻ ሁለተኛ ነች።
ይህ ምንን ያመለክታል?
ወያኔ ባለፉት አስር ዓመታት በተከታታይ ከ11% በላይ ኢኮኖሚውን አሳድጌዋለሁ ሲለን ነበር። እድገቱ ያተኮረው ገጠር፤ ምንጩም ግብርና ነው ብሎን ነበር። ሐቁ ግን ከላይ የተመለከተው ነው።
እርግጥ ነው የወያኔ ሹማምንት በከተሞች ሕንፃዎችን ይገነባሉ፤ በገጠሮች በመቶዎች ሄክታር የሚለካ ለም መሬት ይዘው ፈጣን ገንዘብ በሚያስገኙ የአበባ፣ የጫትና የቃጫ ምርት ላይ ተሰማርተዋል። ከራሳቸውም አልፈው ሀብታም የውጭ አገራት ሸሪኮቻቸውን በአገራችን ለም መሬት ይበልጥ ያበለፅጓቸዋል። የእነሱ የግላቸው፣ የቤተሰቦቻቸው፣ የዘመዶቻቸው እና የሸሪኮቻቸው ኢኮኖሚ እየተመነደገ መሆኑን እናውቃለን። ይህን በገዛ ዓይኖቻችን የምናየው ሀቅ ነው።
ሆኖም ግን የእነሱ ኢኮኖሚ ማደግ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ማደግ አለመሆኑ እናውቃለን። አገራችን ከጓረቤት አገሮች ጋር ስትነፃፀር ወደ ኋላ እየቀረች መሆኑ ያንገበግበናል። በቅርቡ አክስፋም በጥናት ያረጋገጠዉ የኢትዮጵያ ገበሬዎች በየቤታቸው ከወዳጆቻቸው ጋር በምስጢር የሚያወሩትን እውነት ነው።
ከሳምንት በፊት ደግሞ “ኢኮኖሚክ ኢንተለጀንስ ዩኒት” የተሰኘው ታዋቂ የምርምር ተቋም አንድ የጥናት ውጤት ይፋ አድርጎ ነበር። በዚህ የጥናት ውጤት መሠረት በዓለም በከፍተኛ ፍጥነት እያደጉ ያሉ አስር አገሮች በቅደም ተከተል ሞንጎሊያ፣ ሴራሊዮን፣ ቱርክሜንስታን፣ ቡታን፣ ሊቢያ፣ ኢራቅ፣ ላኦስ፣ ቲሞር-ሊስቲ፣ ኤርትራ እና ዛምቢያ ናቸው። በዝርዝሩ ውስጥ ኢትዮጵያ አገራችን የለችበትም።
በዓለም አቀፍ መድረኮችም የወያኔ መረጃዎች ውሸትነት እየተጋለጡ መሆናቸው በጎ ምልክት ነው። የሚያሳዝነው ግን ይህንን ሀቅ የሚያዉቁ ምዕራባዉያን ለጋሽ አገሮች አሁንም ወያኔን እየረዱና እየደገፉ ሥቃያችን የሚያራዝሙብን መሆኑ ነው።
ለዚህም ነው ግንቦት 7፡ የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ዘላቂ መፍትሔ ሊመጣ የሚችለው በአገራችን መሠረዊ የሆነ የአስተዳደር ለውጥ ሲኖር ነው ብሎ የሚያምነው። የወያኔ አገዛዝ በዲሞክራሲያዊ አስተዳደር እስካልተተካ ድረስ የኢትዮጵያ አብዛኛው ሕዝብ መደህየቱ፤ ጥቂት ሀብታሞች ደግሞ በብዙሀኑ ድህነት መበልፀጋቸው አይቀርም። የወያኔ ውሸቶች ለኢትዮጵያ ድሀ ምግብና መጠለያ አይሆኑለትም። ለኢትዮጵያ ዘላቂ ጥቅም ማምጣት የምንችለው ወያኔን አስወግደን በምትኩ ለሕዝብ ሁለተናዊ እድገት የሚጨነቅ መንግሥት መምረጥ ስንችል ብቻ ነው።
ስለሆነም ግንቦት 7፡ የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ በውሸት እድገት እያደናቆረን፤ በተግባር ግን እያደኸየን ያለውን ዘራፊውን ወያኔን አስወግደን በሕዝብ ነፃ ምርጫ የተመረጠ መንግሥት እንዲኖረን ትግላችን እናጠንክር ይላል።
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!http://ecadforum.com/Amharic/archives/10816/

Friday, January 24, 2014

ከቃሊቲና ቂሊንጦ እስር ቤቶች በላይ የሚያንጸባርቁ ከዋክብት (ዳዊት ከበደ ወየሳ፣ አትላንታ)

January 23, 2014
(ይህ ጽሁፍ የርዕዮት አለሙ የልደት በአል በአዲስ አበባ በተከበረበት ወቅት; ከውጭ አገር ንግግር እንዳደርግ በተጋበዝኩበት ወቅት… የስራ ባልደረቦቼን እስክንድር, ውብሸት እና ርዕዮትን በማሰብ የተዘጋጀ ነው)
ይህ ሳምንት የታላቁ ማርቲን ሉተር ኪንግ የልደት በአል በመላ አሜሪካ የሚከበርበት ነው:: በአሜሪካ ከክርስቶስ ልደት ቀጥሎ ስራ እና ትምህርት ቤት ተዘግቶ ልደቱ የሚከበርለት አንድ ሰው ቢኖር ማርቲን ሉተር ኪንግ ብቻ መሆኑን ልብ ይበሉ:: የማርቲን ሉተር ኪንግ የልደት በአል በሚከበርበት ወቅት በህይወት ዘመኑ ለጥቁር ህዝብ ነጻነት ያደረገው አስተዋፅኦ ይታወሳል:: በህይወት በነበረበት ወቅት ለሰው ልጅ እኩልነት ተሟግቷል; የነጻነት ቀንዲልን ለኩሷል:: ሆኖም እኩልነት እና ነጻነትን ሳያጣጥም በበርሚንግሃም እስር ቤት ተጥሎ ፍዳውን እንዲቆጥር ተፈርዶበት ነበር:: በመጨረሻም የሰውን ልጅ ክብር እና ነጻነት በማይደግፉ ሰዎች ህይወቱ ማለፉ ይታወቃል – መልካም ስራዎቹ ግን አላለፉም::Reeyot Alemu, the 31 year-2012 Courage in Journalism Award winner.
ዛሬም በአገራችን ስለፍትህ, ስለነጻነት የሰበኩና የደሰኮሩ; የጻፉና የመሰከሩ… ለሃቅ ቆመው፣ ግፍ የተሰራባቸው፣ ከአገር የተሰደዱና የወጡ፤ በግፍ ሰንሰለት ለጨለማ እስር የተዳረጉ ወገኖቻችን ብዙ ናቸው:: እስክንድር፣ ውብሸት፣ ርእዮት፣ አንዷለም እና ሌሎች ኢትዮጵያውያን ራሳቸውን በሰብአዊነት መሰረት ላይ ስላነጹ እና ሃሳባቸውን በነጻነት ስለገለጹ መጨረሻቸው እስር እና እንግልት ሆኗል::
እንደ እውነቱ ከሆነ ሃሳብን በነጻነት መግለጽ… ብሎም የህዝብ ልሳን ሆኖ ለህዝብ የቤዛነት ዋጋ መክፈል የሚያስከብር እንጂ የሚያሳስር አልነበረም:: በመሆኑም ለነጻ ፕሬስ መክፈል የሚገባቸውን ዋጋ ከመጠን አሳልፈው የከፈሉት፤ ርዕዮት አለሙ፣ እስክንድር ነጋ እና ውብሸት ታዬ… ሶስቱም ከአገራቸው አልፈው በአለም አቀፍ ደረጃ እውቅና አግኝተዋል:: በአለም አቀፍ ደረጃም በልዩ ልዩ አለም አቀፍ የጋዜጠኞች ማህበራትና ተቅውውማት ለሽልማት ታጭተው አሸናፊ ሆነዋል::
የ’ነዚህ የስራ ባልደረቦቼ ብዕር… ህዝብን ሳይሆን የተወሰኑ ወገኖችን አሸብሮ ሊሆን ይችላል:: እነርዕዮት አለሙ በዚህ አይነት ሰበብ አስባብ በቃሊቲ እና በቂሊንጦ እስር ቤት ታግተው፤ ነጻነታቸውን አጥተውና ህክምና ተነፍገው ይታሰሩ እንጂ፤  ለእውነት የቆሙ ወገኖች ግን ለመልካም ስራቸው ሽልማትን አልነፈጓቸውም::
ማርቲን ሉተር ኪንግ በበርሚንግሃም እስር ቤት ታስሮ ቢማቅቅም የአሜሪካም ሆነ የአለም አቀፉ ማህበረሰብ አልዘነጋውም:: ቆይቶም ቢሆን የአለም አቀፉ ኖቤል ተሸላሚ እስከመሆን ደርሷል:: ዛሬ በእስር ላይ የሚገኙት የነጻው ፕሬስ ጋዜጠኞች የኖቤል ተሸላሚ ባይሆኑም አለም ግን አልረሳቸውም:: ከታሰሩበት የጨለማ ወህኒ ቤት ጀርባ፤ ከብረት ፍርግርግ እና ከግድግዳዎቹ ባሻገር በመቶዎች፣ በሺዎች እና በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች እነዚህን ጋዜጠኞች በመልካም ስራቸው ያስታውሷቸዋል; ይዘክሯቸዋል:: ስለሆነም የጻድቃን ሞት፤ የሰማዕትነት ጽድቅ ተደርጎ እንደሚቆጠረው ሁሉ… የነ እስክንድር፣ ውብሸትና ርዕዮት እስር፤ ከቶውኑ ዋጋ ቢስ እና ፍሬ አልባ ሊሆን አይችልም::
ኢትዮጵያ ውስጥ በነበርኩበት ወቅት በፕሬስ ጉዳይ ተደጋጋሚ የሆነ እስር ደርሶብኛል:: በ’ነዚህ የእስር እና እንግልት ጊዜያት ግን… ከጨለማው እስር ቤት ማዶ ለምን እንደታሰርኩ የሚረዱ ሺዎች በመኖራቸው ሁልጊዜ እጽናና ነበር:: በተደጋጋሚ እስር ቤት እየመጣ የሚጠይቀኝ እና የዋስ መብቴን አስጠብቆ ከእስር እንድወጣ ያደርገኝ የነበረው ወላጅ አባቴ፤ “የታሰርከው ሰርቀህ ወይም ሌላ ወንጀል ሰርተህ ሳይሆን፤ እውነትን ስለተናገርክ ነው:: ስለዚህ አንገትህን ቀና ልታደርግ እንጂ ልትሸማቀቅ አይገባህም::” የሚል አጽናኝ ቃል ሁሌ ይነግረኝ ነበር:: ዛሬ አባቴ በህይወት የለም:: ቃሉ እና ምክሩ ግን አብሮኝ አለ:: በእስር ላይ ለሚገኙ የነጻው ፕሬስ ጋዜጠኞች፤ “አንገታችሁን ቀና አድርጉ!” የሚለውን መልዕክት አጋራቸዋለሁ::
ዛሬ በጋዜጠኞቻችን ላይ የተለያዩ ክሶች ተመስርቶባቸው መታሰራቸው ሳያንስ; ከታሰሩም በኋላ በሃሰት ሊወነጅሏቸው የሚሹ ብዙ ግራ ዘመም ሰዎች መኖራቸውን ታዝበናል:: በአሜሪካ ከፍተኛ የአየር ሽፋን አግኝቶ ዲሞክራቶችን በመሳደብ የሚታወቀው ራሽ ሊምቦ የተባለ ጋዜጠኛ በቅርቡ ኔልሰን ማንዴላ በሞት ሲለዩ… “ብታምኑም ባታምኑም ኔልሰን ማንዴላ አሸባሪ ነበሩ::” ብሎ ሰፊ ሙግት ፈጥሮ ነበር:: ይህ አባባሉ ለኛ እና ለሌሎች አፍሪቃውያን ሊገርመን ይችል ይሆናል:: ነገር ግን የራሳቸው አመዛዛኝ ህሊና ያልፈጠረባቸውና ይህን ሰው በጭፍን የሚከተሉት ሰዎች “አዎ ማንዴላ አሸባሪ ነበሩ” ብለው ቢሉ ሊገርመን አይገባም::
ዛሬም ባገራችን በተመሳሳይ መልኩ የነርዕዮት አለሙን መልካም ስም ጥላሸት ለመቀባት እላይ ታች የሚሉ ሰዎች ሊኖሩ ይችላሉ… እኛ ግን እንላለን:: “ወንጀል አልሰራችሁምና አንገታችሁን ቀና አድርጉ!” ስማችሁ ከቃሊቲና ከቂሊንጦ እስር ቤቶች በላይ፤ በጠራው ሰማይ ላይ ያንጸባርቃል፤ ቃለ ሃቃቹህ በአየር ናኝቶ… ኢትዮጵያዊያን ባሉበት ሁሉ በመላው አለም ላይ ተሰራጭቷል::
የማርቲን ሉተር ኪንግ ልደት ሲከበር መልካም ስራዎቹ እንደሚወደሱ ሁሉ፤ ዛሬም ሆነ ወደፊት የነርእዮት አለሙ ልደት ሲከበር መልካም ስራዎቻቸው በተደጋጋሚ ይነሳሉ ይዘከራሉ:: ዛሬ ማንዴላን አሸባሪ ብለው የሚከሱ ሰዎች እንደመኖራቸው መጠን; በተመሳሳይ መልኩ ለነርእዮት አለሙ ተመሳሳይ ስም የሰጡና ያሰጡ… ለመስጠት እና ለማሰጠት የሚጥሩ ሰዎች አሉ:: እኛ ግን የተለኮሱ ሻማዎች ይዘን ልደት ስናከብር; የብርሃናችን  ጮራ፤ ሌሎች የፈጠሩትን የጨለማ ድባብ ሰንጥቆ… አንዳች ብርሃን እንደሚፈነጥቅላቸው በማመን ነው:: ዛሬ የርዕዮት አለሙን የልደት ቀን ስናከብር፤ ያለፍትህ የታሰሩትን ፍትህ የሚፈልጉትን፤ ነጻነት የተጠሙትን ነፍሶች በማሰብ ጭምር ነው::
መልካም ልደት – ርዕዮት!http://ecadforum.com/Amharic/archives/10805/

Thursday, January 16, 2014

“ወሬ አይደለም፤ አገር ቤት አንገባለን” ሌንጮ ለታ

ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፤ “መረጃ የለኝም”
odf lencho
የኦሮሞ ነጻ አውጪ ግንባር ከፍተኛ አመራርና ጸሐፊ የነበሩት አቶ ሌንጮ ለታ አዲስ ያቋቋሙትን ድርጅት ይዘው አዲስ አበባ እንደሚገቡ አስረግጠው ተናገሩ። አቶ ሌንጮ ድርጅታቸው ኢትዮጵያ ገብቶ ለመታገል መወሰኑ ለምን ወሬ እንደሚባል እንዳልገባቸውም አመላክተዋል። በሰላማዊ መንገድ ለመታገል ኢትዮጵያ መግባታቸውን ኦነግ እንደሚቀበለው ተጠይቀው “ኦነግን ጠይቅ” በሚል ጠበቅ ያለ መልስ ሰንዝረዋል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ እንደሌለው አመልክቷል።
ጥር 5 ቀን ከጀርመን ድምጽ የአማርኛ ፕሮግራም ጋር ቃለ ምልልስ ያደረጉት አቶ ሌንጮ “ኖርዌይ ተቀምጠን ምን እናደርጋለን? ሃገር ቤት ገብተን እንታገላለን” ሲሉ ወደ አገር ቤት ለመመለስ መወሰናቸውን ግልጽ አድርገዋል። “ይሳካል?” በማለት ጠያቂው ላቀረበው “ይሳካል አይሳካም ተብሎ ወደ ትግል አይገባም” በማለት አቶ ሌንጮ ማምረራቸውን በሚያሳብቅ ሁኔታ መልስ ሰጥተዋል።
ህወሃት የዘረጋውን የፌዴራል ሲስተም እንደሚቀበሉትና የኦሮሞ ህዝቦች ጥያቄም በዚያው ውስጥ ሊመለስ እንደሚችል ያመለከቱት አቶ ሌንጮ፣ “በታሪክ፣ በባህል፣ በቋንቋ የተመሰረተ ሳይሆን በህግና በህገመንግሥት በተደነገገ የህዝቦች አንድነት እናምናለን” ብለዋል። የግለሰብ መብት ከብሔር መብት መቅደም አለበት፣ የብሔር መብት አስቀድሞ ሊከበር ይገባዋል በሚል ሁለት አቋም ከሚያራምዱት የተለየ ፕሮግራም እንዳላቸውም አቶ ሌንጮ አስታውቀዋል። የግለሰብም ሆነ የቡድን መብት መከበር አለበት የሚል ፕሮግራም ያለው አዲሱ ድርጅታቸው በዚህ አቋሙ ከሌሎች እንደሚለይ አመልክተዋል።
በምርጫ የመሳተፍን ጉዳይ አስመልክቶ የእሳቸው ድርጅት ብቻ ሳይሆን ሁሉም ተቃዋሚ ሃይሎች ወደ ምርጫ ቢገቡ ፍላጎታቸው መሆኑንን አቶ ሌንጮ ተናግረዋል። ይሁን እንጂ ከምርጫ በፊት ብዙ ጥያቄዎች እንዳሉ አመልክተዋል። ዴሞክራሲን ኢትዮጵያ ውስጥ ለማስፋፈት ምርጫ ብቻውን መፍትሔ እንዳልሆነም ጠቁመዋል። ህዝብን አገር ቤት ገብቶ ማስተማር፣ መቀስቀስና ማብቃት በዋናነት አስፈላጊ እንደሆነም አስምረውበታል።
ከኢህአዴግ ጋር ድርድር ስለማድረጋቸው ለተጠየቁት፣ እስካሁን የተደረገ ድርድር እንደሌለ አቶ ሌንጮ ጠቁመዋል። አያይዘውም ከኢህአዴግ ጋር ብቻ ሳይሆን ከተቃዋሚ ድርጅቶች ጋርም የመደራደር እቅድ እንዳላቸው አመልክተዋል። አቶ ሌንጮ በተደጋጋሚ አገር ቤት መሄዳቸው መገለጹንም በማንሳት አስተባብለውታል። አቶ ሌንጮ ድርድር ስለመደረጉ ባያምኑም በተለያዩ ጊዜያት በኖርዌይና በተለያዩ አገራት ከኢህአዴግ መልዕክተኞች ጋር አሁን ይፋ ባደረጉት ጉዳይ ዙሪያ መነጋገራቸው መዘገቡ ይታወሳል። ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣም በቅርቡ ኢህአዴግ ብሔር ተኮር ከሆኑ ድርጅቶች ጋር ድርድር እያደረገ መሆኑንና ከሌሎች ማናቸውም ፓርቲዎች ጋር ለመደራደር ሃሳብ እንደሌለው ምንጮቹን ጠቅሶ መዘገቡይታወሳል።
አቶ ሌንጮ የሚመሩት ድርጅት ወደ ኢትዮጵያ ለመግባት መወሰኑን አስመልክቶ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ የሆኑት አቶ ዲና ሙፍቲ “መረጃ የለኝም፤ የድርጅት ሰዎች ብትጠይቅ የተሻለ ነው” በማለት ዜናውን ይፋ ላደረገው የጀርመን ድምጽ ሬዲዮ ተናግረዋል።lencho and melesየሚመለከታቸውን አካላት ለማግኘትና በሪፖርቱ ለማካተት እንዳልተቻለ ከሪፖርቱ ለመረዳት ተችሏል። አብዛኛው የኦነግ ደጋፊዎች የነበሩ በድርጅቱ የትግል ጉዞና ውጤታማ አለመሆን መማረራቸውን የተለያዩ ድረገጾች በስፋት ይዘግቡ ነበር።
ለአቶ መለስ ቅርብ እንደነበሩ የሚነገርላቸው አቶ ሌንጮ “አገር ቤት ገብተው ይሳካላቸው ይሆን?” የሚለውን ለመናገር “ህገ መንግሥቱንና ህገ መንግሥታዊ ስርዓቱን ተቀብዬ በሰላማዊ መንገድ ለመታገል ተስማምቼና ወድጄ ወደ አገር ቤት ለመግባት ችያለሁ” በማለት ኢቲቪ ዜናውን ይፋ ሲያደርገውና “ያሳዘነውን መንግስትና ህዝብ ይቅርታ እንጠይቃለን” ሲሉ ከተደመጠ በኋላ እንጂ ከወዲሁ አስተያየት መስጠት እንደሚቸግራቸው አስተያየት እንዲሰጡ የጠየቅናቸው ተናግረዋል። “ውሳኔውን ተፈጥሯዊ ጫና” ነው ያሉም አሉ።http://www.goolgule.com/lencho-letta-returning-back-to-ethiopia/


መረጃ ነፃነት....
(ይድነቃቸው)


“ሕዝቡ እኔ ማን እንደሆንሁ ይላል?” በማለት እየሱስ ክርስቶስ መረጃ ይጠይቃል፤ ደቀመዛምርቶችም ስለሱ
የተባለውን አንድም ሳያስቀሩ ይነግሩታል፡፡ እሱም መልሱ እንዲህ ይላቸዋል “እናንተስ እኔ ማን እንደሆንሁ
ትላላችሁ?” አላቸው ፡፡ እነሱም መለሱለት፡፡ ሙሉ ታሪኩ ሉቃስ 9ቁ 18 ላይ ይገኛል ፡፡

መረጃ አይናቅም አይደነቅም ማለት እንዲህ ነው፡፡ በመሰረቱ ክርስቶስ ሰዎች ስለሱ ምን እንዳሉ ብቻ ሳይሆን
ምን እያሰብ እንደነበር የሚያውቅ አምላክ ነው፡፡ ግን መጠየቅ እና መመለስ አሳብን መግለፅ የሰው ልጅ
ተፈጥሯዊ ባህሪ ነው፡፡ ለዚህም ነው ክርስቶ እንደሰው በምድር በተመላለሰበት ወቅት መረጃ ይጠይቅ
የነበረው እሱም ስለራሱ መረጃ ይሰጥ የነበረው፡፡ እርግጥ ነው ክርስቶስ ይህን ሲጠይቅ የራሱ ምክንያት
አለው፡፡

በመሆኑም ሃሳብ መግለፅ ተፍጥራዊ መብት ነው ወደሚለው ዓለም አቀፍ ስምምነት በመደረሱ የመናገር ሃሳብን የመግለፅ ነፃነት
የዲሞክራሲ ዋና የድም ስር ነው የተባለው፡፡ ስለዚህም ተሰባስቦ መቃወም እንዲሁም መደገፍ ፣ አንድ ሰው የሚመስለውን ሃሳብ
በፈለገው መንገድ መግለፅ፣ የመምረጥና የመመረጥ፣ መንግስትን የመተቸት፣ በራስ ፍቃድ የመናገረ እና ያለመናገር ፣ በዓልንና
አይማኖትን መከተልና ማስፋፋት እንዲሁም ህግ ለሁሉም የሚሰራ ስለመሆኑ መረጋገጥ እና የመሳሰሉት ሁሉ ተግባራዊ የሚሆነው
ተአቅቦ ያልተደረገበት የመናገርና የመረጃ መብት ልውውጥ ተግባሪዊ ሲሆን ብቻ ነው፡፡

ለመደርደሪያነት የዚህን ያኸል ከተባለ ወደ ዋናው ጉዳይ አስፈቅደን ሳይሆን ፈቅደን እንገባለን፡፡ ያነሳነው አሳብ ‹‹ መረጃ ›› እንደመሆኑ
መጠን ያለማንም ጣልቃ ገብነት ተፍጥሯዊ መብታችን በፈለግነውና በፈቀድነው መንገድ እንገልፃለን፡፡ እኛ ስል ለመረጃ ነፃነት
የቆምነው ሁላችንም ማለቴ ነው፡፡

ሰው በመናገሩ አና በመፃፉ ብቻ ለእስር እና ለስደት የሚዳረግበት አገር በዋነኝነት ከሚጠቀሱት ውስጥ ኢትዮጵያ አንዶ ናት፡፡ ነገር ግን
ማንኛውም ሰው ያለማንም ጣልቃ ገብነት የአመለካከት እና ሐሳብን በነፃ የመያዝና በማንኛውም የማሰራጫ ዘዴ በሀገር ውስጥም ሆነ
ከሀገር ውጪ የመግለፅ ነፃነት አለው፡፡የሚለው በኢትዮጵያ ህገመንግስቱ አንቀፅ 29 ተፅፎ ይገኛል፡፡ በእርግጥ ይህ መብት ገደብ
ሊጣልበት እንደሚችል በህገ መንግስቱ ላይ ተገልፆ የተቀመጠ ሲሆን ገደብ ግን መሠረታዊ የሆነውን መረጃን የመስጠት እና የማግኘት
እንዲሁም አስተሳሰብ ላይ ወይም አመለካከት ላይ ውጤት እንደማይኖረው በህገመንግስቱ ተገልፆ ይገኛል፡፡

ይሁን እንጂ አሳብን በነፃ ማሰብና ማንሸራሸር በአገራችን ወቅታዊ ሁኔታ እጅግ አዳጋች ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡ አልፎ ተርፎ በአስተሳሰብ
ወይም በአመለካከት ላይ ተፅኖ እስከመፍጠር ተደርሶኦል ፡፡ ነገር ግን እንዲህ አይነቱ ሁኔታ ለህግም ሆነ ለሞራል ተቃራኒ እንደመሆኑ
መጠን የፈጀውን ፈጅቶ ወደነበረበት መመለሱ የማይቀር ሃቅ ነው፡፡ ነፃ አሳብ የሚንሸራሸርባቸው ነፃ ጋዜጦችና መፅሔቶች ምን ያህል
አሉ ? ያሉት ጋዜጦች እና መፅሔቶች እየደረሰባቸው ያለው ማስፈራሪያና ዛቻ ደረጃው ምን ያኸል ደርሶአል የሚለውን መመልከት
ተገቢ ነው፡፡ ለዚህም ማሳያ የሚሆነው በቅርቡ በወጣው አዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ አክራሪነትና ፅፈኝነት የሚያበረታቱና የሚያሰራጩ
በማለት በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ለህዝቡ ተገቢውን መረጃ እያስተላለፉ ያሉ የእትመት ውጤቶችን ከገቢያ ለማውጣትና ፈርጆ
ለመክሰስ እየተደረገ ያለው ዝግጅት ሌላው ማሳያ ነው፡፡ጋዜጠኞችን በማሰቃየት፣በማሰር እና እንዲሰደዱ በማደረግ ኢትዮጵያ በዓለም
ላይ በሁለተኝነት ደረጃ ላይ ትገኛለች ፡፡መንግስትን ተችቶ የፃፈና ፁሁፉ የወጣበት ጋዜጣ ወይም መፅሔት ጨምሮ ሁሉም ለእስር
የሚዳረግበት ወይም አደገኛ ዛቻና መስጠንቀቂያ የሚሰጥበት ደረጃ ላይ ተደርሷል፡፡

በዲሞክራሳዊ ሥርዓተ ዜጎች የሚኖሩት ግልፅ በሆነ የሃሳብ ልውውጥ ነው፡፡ የትኛውም አይነት ሃሳብ ከማንም ሊመጣ ይችላል ቁም
ነገሩ መሆን ያለበት የሚመጣው ሃሳብ የሚመከተው በምንድነው የሚለው ነው፡፡ ለነፃ ንግግር ችግር የተሻለው መንገድ የበለጠ ነፃ
ንግግር ነው፤ በመናገር መብት ላይ የሚደረግ ማናቸውም ተፅእኖ ሲውል ሲያድር በእያንዳንዱ ግለሰብ የመናገር መብት ላይ ስጋት
ሊያስከትል ይችላል፡፡ለዚህም ነው ወደነበረበት መመለሱ የማይቀር ነው ለማለት የሚያስደፍረው፡፡ምክንያቱ ደግሞ ማንም ሰው በስጋት
ውስጥ መኖርን ስለማይፈልግ ነው፡፡

በመሆኑም በአገራችን እየከሰመ ያለው ሃሳብን በነፃ የመግልፅ እና መረጃ የማግኘት መብት በገዥው መንግስት መልካም ፍቃድ ላይ
የተመሠረት ወደመሆን ደረጃ ተሸጋግሯል፡፡ለዚህም እንደማሳያ ከሰሞኑ የህዝብ ሳይሆን የገዥው መንግስት አንደበት በሆነው በኢቲቪ
በተላለፈው የዘጋቢ ፊልም ግለሰቦችም ሆነ በአገር ውስጥ ያሉ የተቃዋሚ ፓርቲዎች በተለይ ሰማያዊ እና አንድነት ፓርቲ ለኢሳት መረጃ
ከመስጠት እንዲቆጠቡ ምክር መሰል ማስጠንቀቂያ ተላልፏል፡፡

ለዚህም እንደምክንያት የቀረበው ኢሳት የተባለው የመገናኛ ብዙሃን በሽብርተኛ ድርጅት የሚደገፍ ነው የሚል ምክንያት ነው፡፡ ኢቲቪ
በኢህአዴግ እንደሚደገፍ ሁሉ ኢሳት በማንም ሊደገፍ ይችላል፤ ቁም ነገር ሆኖ መታየት ያለበት ኢቲቪ ሆነም ኢሳት የሚያስተላልፉት
መልዕክት ምንድነው ፡፡ በተጨማሪ መልዕክቱ ለህግም ሆነ ለሞራል ምን ያኸል ተቃራኒ ነው የሚለውን ነው፡፡ በተጨማሪ ኢቲቪ
እንዲሁም ኢሳት በህግ መደመጥ እንዲሁም መሰማት የተከለከሉ የመገናኛ ብዙሃን ናቸው ወይ ተብሎ መጠየቅና መልስ ሊሰጥባቸው የሚገባ አሳቦች ናቸው፡፡ ይሁን እንጂ ወደ መልሱ ስናመራ ኢቲቪ እንዲሁም ኢሳት በህግ የተከለኩ አይደሉም ዋንኛው እና አስፈላጊው
ነገር ይሄ ነው ሌላው የህጉ ደጋፊ ሃሳብ ነው፡፡

በመሆኑም ከዚህ በኋላ የህግ ጉዳይ ሳይሆን የፍላጎት ምርጫ ነው የሚሆነው፡፡ የፈለጉትን መስማት እና ማዳመጥ እንዲሁም በፈለጉት
የመገናኛ ብዙሃን መንገድ ሃሳብን መግለፅ እና መረጃን ማግኘት ግለሰብ ከሆነ እንደግለሰቡ፣ ተቋም እንደተቋም እንዲሁም ፓርቲ እንደ
ፓርቲ የመምረጥ የራስ መብት ነው፡፡ ይህ ደግሞ አንዱ የዲሞክራሲ መገለጫ ነው፡፡ በዚህም መሠረት ከኢቲቪ ኢሳት ከአዲስ ዘመን
አዲስ አድማስ የዝወትር ፍላጎታቸው ለሆነ እንዲሁም በተመሳሳይ ከኢሳት ኢቲቪ ከአዲስ አድማስ አዲስ ዘመን ለመረጡ ምርጫቸውን
ማክበረ ነው፡፡

ሌላው እና አሳሳቢ ሊሆን የሚገባው ሰው የመረጠውን መስማትና ማዳመጥ እንዲሁም ማንበብ መብቱ እንደጠጠበቀ ሆኖ ግለሰበ
ወይም ተቋም ሃሳቡን እንዴት የመግለፅ መብት እና ግዴታ አለበት የሚለው ነው፡፡ ይህን በተመለከተ ተቋም ወይም ግለሰብ ሃሳብን
ወይም መረጃን በማንኛውም መንገድ የመገልፅ ሙሉ መበት በህግ የተጠበቀ ነው ፡፡እንዲኹም የዚህ መብት ተቃራኒ የሆኑ ማናቸውም
ነገሮች ተቀባይነት እንደሌላቸው በህገመንግስቱ ተደንግጎ ይገኛል፡፡ በዚህም መሰረት በኢሳት ሆነ በማናቸውም የመገናኛ ብዙሃን ሃሳብን
መግለፅ እና መረጃን መስጠጥ በራሱ ወንጀል ወይም ጥፋት አይደለም ይህ የሆነው ደግሞ መብት ከመሆኑ አንፃር ነው፡፡

ከዚህ ጋር ተያይዞ መታየት ያለበት ሃሳብን በመግለፅ እና መረጃን በመስጠት ዙሪያ ግዴታ ሊያመጣ የሚችለው ምንድነው የሚለው
ነው፡፡ ግለሰቡ ወይንም ተቋሙ በግልፅ በህግ የተከለከለ መረጃ ወይም ሃሳብ የገለፀ እንደሆነ ግዴታው ተጠያቂነትን ስለሚያመጣ በህጉ
መሠረት ተጠያቂ ይሆናል፡፡ ይህ የህግ ተጠያቂነት አዱላዊነት የሌለበት ለሁሉም በሁሉም ቦታ እኩል የሚሰራ ነው፡፡ ይህም ማለት
በህግ የሚያስጠይቅ ንግግር በኢሳትም ሆነ በኢቲቪ እንዲሁም በቢቢሲ ያደረግ በህግ ከመጠየቅ ንግግር ያደረገበት የብዙሃን መገኛኛ
ሊታደገው አይችልም እንደማለት ነው፡፡

በመሆኑም በኢሳት ሃሳብን መግለፅ እንዲሁም መረጃ መስጠት አልፈልግም ማለት መብት ነው፡፡ ነገር ግን በኢሳት አሳባችሁን
አትግለፁ መረጃም አትስጡ ማለት ከፍላጎት የመነጨ ሃሳብ ብቻ ሳይሆን የለየለት የእብሪት ተግባር ነው፡፡ እንዲህ አይነቱ አሰፋሪ
ምኞት እና ተግባር የሕግና የዲሞክራሲያዊ መብት ካለማወቅ የሚመነጭ አስተሳሰብ ብቻ ሳይሆን ተምሮ ያለመለወጥ ልክፍትም ጭምር
ነው! በተለይ በመንግስት ደረጃ ሲታሰብ እጅግ በጣም ያሳፍራል፡፡

Wednesday, January 15, 2014

የህዝባዊ አንድነትና ኃይል የወያኔ ሕወሐት ማጥፊያ መድሃኒት



ከሮባ ጳዉሎስ
January 14, 2014
ካለመታደል ሀገራችን ዛሬም ሰላም ፍትህና ዲሞክራሲ የሰፈነባት በልማትና በእድገት ጎዳና የምትራመድ ሀገር አልሆነችም። ለዚህም በርካታ ምክንያቶች ቢኖሩም እንደ ዓቢይ ምክንያት ተደርጎ የሚቀርበው የህዝብን ይሁንታን ያገኘ፡ ህዝብን በእኩልነት የሚዳኝ፡ ህዝባዊና ዲሞክራሲያዊ የሆነ መንግሥት አለመመስረቱ፡ አገርና ህዝብ የሚተዳደሩበት ዲሞክራሲያዊ ህገ መንግሥት አለመኖሩ ነው። እስከዛሬ በተጨባጭ እንደታየው በ ኢትዮጵያ ሕዝብ ጫንቃ ላይ የተፈራረቁበት ገዥዎቹ በየበኩላቸው አንዱ ከሌላው የሚለዩባቸው ባህርያት ቢኖራቸውም ሁሉንም ግን አንድ የሚያስመስሏቸው ባህርያትም አሏቸው። እነሱም ሁሉም በኃይል ሥልጣን መያዛቸው፡ አምባገነንነታቸው፡ የከፋፍለህ ግዛ ፖሊሲ ማራመዳቸው፡ በህዝብ መካከል የጋራ መተማመንና ከበሬታን ለመፍጠር፡ ሁሉም ዘላቂ ሰላምና መረጋጋትን በሀገሪቱ ለማስፈን አለመቻላቸው ደግሞ ዛሬ ለሁሉም በግልጥ እየታየ ያለ ነው። በዚህም የተነሳ በሀገራችን ለብሔራዊ ክብርና ነፃነት፡ ለዲሞክራሲ፡ ለማህበራዊ ፍትህ፡ ለሰላምና ለእኩልነት የሚታገሉ ኃይሎች የሰላማዊ ለውጥ በሮች ስለተዘጉባቸው የአ መፅን ጎዳና እንዲከተሉ የሚጋብዝ በር ተቀዶ ይገኛል።
በሌላ በኩል ደግሞ በሀገሪቱ ውስጥ የፖለቲካ መረጋጋት ንእዲፈጠር፡ ሕዝቡም አስተማማኝ ሰላምና ፀጥታ አግኝቶ ያለስጋት ለመኖር እንዲችል፡ የዳኝነት ተቋሞች ነፃ ሆነው የሚሠሩበት፡ የህግ የበላይነት የተረጋገጠበት ሁኔታ እንዲፈጠርና፡ ህዝቡም በህግና ሥርዓት መኖር ላይ እምነት እንዲያድርበት ለማድረግ እንዲቻል፡ ለዲሞክራሲያዊ ሥርዓት የሚታገሉ ኢትዮጵያዊ ተቃዋሚ ኃይሎች በተናጠልም ሆነ በኅብረት በርካታ ጥረቶች ተደርገዋል። ሆኖም እስከዛሬ የተደረጉት ጥረቶችን ሁሉ በማምከን ወያኔ የሰላምና የእርቅ መሰናከል ከመሆኑም ባሻገር በንፁሃን ዜጎች ደም ሰላምን አጠልሽቶታል። ወያኔ ስለ ሰላምና እርቅ ሊሰማም ሊነጋገርም እማይችልበት የደም ስካር ላይ ደርሷል።
ብአዴን ቢመጣ ኦህዴድ ቢመጣ ደህዴን ቢመጣ የሚለወጥ ነገር አይኖርም። ጠንከር ያለ ለለውጥ የተዘጋጀ – አስከ ሞት የቆረጠ -ጠቅላይ ሚኒስተር ስልጣን አገኘ ማለት የህወሃት የበላይነት እና ፈላጭ ቆራጭነት ፍላጎት ፈተና ይገጥመዋል ማለት ስለሆነ! ህወህት የበላይነቱን ለማሰጠበቅ የፈጠራቸው የመንግስት ስልጣን አደረጃጀት አና ተቋማት ዛሬም በሙሉ ሃይላቸው አሉ። የህወሃት ፈላጭ ቆራጭነት ሳይዳከም ለውጥ አይመጣም። የህወሃት ፈላጭ ቆራጭነት መሰረቱ ደሞ ከምንም በላይ ወታደራዊ ሃይሉ ላይ የተመሰረተ አንደሆነ የአደባባይ ሚስጥር ነው። በደህነንት ቢሮ ያሉትን የህወሃት አመራሮች ከታች ያሉት ማዳክም የሚችሉበትን አጋጣሚ አና ሁኔታ ተጠቅመው አስካላዳከሙት ደረስ የህወሃት የስልጣን የበላይነት ትርጉም ባለው ሁኔታ እክል ሊገጥመው አይችልም።
ሌላ ሌላውን ትተን መሰረታዊ የሆነ ህገ-መንግስታዊ ማሻሻያ ያስፈልጋል፣ የፍትህ ስርዕቱ የፍትህ ስርእት መመስልም መሆንም አለበት፣ የነጻው ፕሬስና ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት ህዳሴ አንመራለን አየተባለ በመካከለኛው ዘመን አና ከዛ በፊት ከነበረው አንደነበረው በሰይፍ አና በሰደፍ መያዝ የለበትም። አነኚህ ወሳኝ ርምጃዎች በአዝጋሚ ለውጥ ይመጣሉ ብየ አላስብም። የአዝጋሚ ለውጥ ዲስኩር (ፍላጎት ካለ ፍላጎትም) ጭራሽ ወደማይቀልበስ የባርነት ዓለም አና ዘመን የመውሰጃ ከፓለቲካ ዘዴ ሊሆን ይችላል። ጋዜጠኞችና የተቃዋሚ ፓለቲካ መሪዎች ዘብጥያ ሲጣሉ ሙስሊም ኢትዮጵያውያን የፈጠሩትን ዓይነት ጫና መፍጠር ስላልተቻለ አንኳን መሰረታዊ የፕሬስ ነጻነት አና በነጻነት ያለገደብ የመደራጀት መብት የሚከበርበት ፍንጭ ሊገኝ ቀርቶ የታሰሩትን ጋዜጠኞች አና የፓለቲካ መሪዎች ማስፈታት አንኳን አልተቻለም። ጭራሽ መብታቸው ተረግጦ ያላግባብ አስር ቤት የተጣሉ ኢትዮጵያውያን ዛሬ ድረስ “አሸባሪ” አየተባሉ አየተፌዘባቸው ነው ያለው። አቶ ኃይለማርያምም ፌዙን በጠቅላይ ሚኒስትርነት ማዕረግ አያስተጋቡት ነው።
ከበቀለበት የተጋጋበት አንዲሉ የ”በሳሉ መሪ ራዕይ” ዜማ ከህወሃት አባላት በእህት ድርጂቶች የፓለቲካ አላዋቂዎች አና መሪዎች ይበልጥ ተዜመ! በአቶ ኃይለማርያም ደሳለኝም ተሰማ። ችግሩ የለውጥ ጥያቄ ማድበስበሻ ሆኖ ለረዢም ጊዜ ሊቆይ አይችልም። በውሽት ላይ የተመሰረተ ፐሮፓጋንዳ ስር ሊይዝ አይችልም።አንዴት ይሄን ማየት አቃታቸው?!የሕዝባችን መከራና ሰቆቃ እየከፋ ሄደ። የተጨቆነዉ ሕዝብ ተነሳስቶ ለመብቱ ሲታገል ጨቋኝ መንግሥታት ለዉጥ እንዲያደርጉ ይገደዳሉ፤ ካለዚያ በተባበረዉ የሕዝብ ኃይል ተንኮታኩተዉ ይወድቃሉ። የታገለዉ ለዉጥ ያመጣል፤ ያልታገለዉ ቁጭ ብሎ በባርነት ሲገዛ ይኖራል፤ ቁጭም ባለበት ይሞታል ማለት ነው። የለዉጥ ባለቤት ሁሌ ሕዝብ መሆን አለበት። ህዝቡ ትግሉን በሚገባ እንዲያቀናጅ የትግል መሪ ይፈልጋል። ስለዚህ የተቃዋሚ የፖሊቲካ መሪዎች ታላቅ ኃላፊነት ይጠበቅባቸዋል። ያገራችንን ጭብጥ ሁኔታ ስንመረምር ግን በሁለቱም በኩል ታላላቅና ተደጋጋሚ ድክመቶች ታይተዋል። አምባገነን መንግሥታት ለዘለዓለም ካልገዛን ሲሉ የተቃዋሚ ድርጅቶች ኅብረታቸዉን ማጠናከር ስላልቻሉ የጨቋኝ መንግሥታትን ዘመናት ሲያራዝሙ ቆይተዋል።ወያኔ/ኢሕአደግ ለዘለዓለም ሊገዛ አይችልም፤ ለሁሉም ጊዜ አለዉና።ትግሉ ይበልጥ መፋፋም፡ ይበልጥ መጨስ፡ መጋጋም፡ መንደድ ይጠበቅበታል።
ትግሉን ለማፈንና አቅጣጫውን ለማሳት የወያኔ መንጋ እየተሯሯጠ ነው። በውጭ ያለውንም የሕዝብና የድርጅቶችን ተቃውሞ ቢቻለው ለማዳፈን፡ ካልሆነለት ደግሞ ለማዳከም፡ በአሁኑ ወቅት የወያኔ ከፋፋይ ቡድን በየቦታው በመንቀሳቀስ ላይ እንደሚገኝ እያየን ነው። ይህ ቡድንም፡ ምሁር ነን፡ አስታራቂ ነን፡ ሽማግሌ ነን ወይም ታጋይ ነን በሚሉ መሰሪዎችም እየተደገፈ ነው። የሕዝብ ክንድ ይላላ፡ ይደክም ዘንድ፡ በከፋፋይ ሴራ የተሰማሩትን ነቅቶ መጠበቅ፡ ትግሉን መከላከል ብቻ ሳይሆን ወያኔ ለባሾችን፡ ሰላዮችን ሳንፈራ እየመነጠርን ማጋለጥ ይኖርብናል። ዘረኛው ቡድንና ጭፍሮቹ የሕዝቡን ትግል ለመከፋፈል ከመቼውም ጊዜ በበለጠ እየጣሩ ናቸውና። ሕዝብ አንድነቱን ጠብቆ፡ የወያኔን ቡድን ለአንዴም ለሁሌም ለማስወገድ አስፈላጊውን መስዋእ ትነት እየከፈለ ባለበት ወቅት የፖለቲካ ድርጅቶችን እገዛና አመራር ይጠይቃል። የሕዝብ አሸናፊነት አጠራጣሪ ባይሆንም፡ አሸናፊ ለመሆን ግን መታገል መቅደም እንዳለበት ምን ጊዜም መረሳት የለበትም። ለዚህ መሠረቱ ግን ከራስ ጋር እየታረቁ፡ ከወገን ጋር እየተስማሙ በጋራ ዓላማና ብሔራዊ እጅንዳ ዙሪያ ተሰባስቦ በጋራ መታገል ብቻ ነው።
በዓለም ታላቅ ዝና ያተረፉት የግ/ቀ/ኃ/ሥና በአፍሪቃ አህጉር መሬትን ያንቀጠቀጠዉ የደርግ መንግሥት ቀናቸዉ ሲደርስ እንዴት እንደመነመኑና እንደከሰሙ መዘርዘር አይኖርብኝም፤ በታሪክ ፊት ተቀምጧልና። በሩቁም በእነ አሜሪካ ለረዥም ዓመታት ሲረዱና ሲደገፉ በነበሩት በእነ ሞቡቱ፤ የሻህ ንጉሥ፤ ሆስኒ ሙባረክ፤ ወዘተ ላይ በመጨረሻ የደረሰዉን ዉርደት መገንዘብ ያስፈልጋል። ተቃዋሚ የፖሊቲካ ድርጅቶች ነን የሚሉትና በተግባር ግን የጭቆናን ዘመን የሚያራዝሙ በሙሉ ካለፉት ስህተቶች ገና ሊማሩ አልቻሉም፤ ・ድር ቢያብር እንበሳ ያስር・ የተባለዉን ቅዱስ አሳብ ደጋግመዉ መናቃቸዉ ያስተዛዝባል። ቁርጥ ያለ አቋም ያስፈልጋል፤ ከዛፍ ዛፍ መዝለል ዬትም አያደርስም። ለጊዜያዊ ጥቅማ ጥቅሞች በርካሽ መገዛትና አገርን መሸጥ በሰማይም በምድርም ያስጠይቃል። ቀኑ ሲደርስ ራቆታችንን ወደምድር እነደመጣን ሁሉ ራቆታችንን ወደዚያዉ እነደምንመለስ አንርሳ!!!

Tuesday, January 14, 2014

የባለሥልጣናት ሃብት ተመዝግቦ አያልቅም እንዴ?

    የሃብታቸው መጠን ይፋ የሚደረገው  ከስልጣን ሲወርዱ ይሆን? (ያመለጡን አሉ!)
በሃብት ምዝገባው ላይ የትዳር አጋርም  ሊካተት ይገባል (መነጣጠቅ ተጀምሯላ!)
“Grand corruption” አለ የሚባለው ገንዘብ ሚኒስቴር ሲዘረፍ ነው እንዴ?
የእነቴሌ “የእንኳን አደረሳችሁ” መልዕክት “ፅድቁ ቀርቶብኝ--” ያሰኛል!
ኢትዮ- ቴሌኮም በየበዓሉ የሚልከው የ “እንኳን አደረሳችሁ” መልካም ምኞት አሁን አሁን “ሙስና” እየመሰለኝ መጥቷል፡፡(ግራንድ ኮራፕሽን ሳይሆን ሚጢጢዬ ሙስና!) ለነገሩ ቢመስለኝም እኮ አይፈረድብኝም፡፡ ለምን መሰላችሁ? ዓመቱን ሙሉ በብዙ የአገልግሎት አሰጣጦች ችግር ሲያማርረን ከርሞ --- በዓል ሲደርስ እንደ ደህና አገልጋይ “እንኳን አደረሳችሁ” የሚለን ሊደልለን ካልሆነ በቀር ሌላ ምን ሊሆን ይችላል? (“ደለለኝ --- ደለለኝ” ነው ያለችው ድምፃዊቷ) ነፍሷን ይማረውና! እውነቴን እኮ ነው… ኔትዎርክ ሳይኖር፣ ኢንተርኔት ተቋርጦ፣ የቢሮና የቤት ስልክ ጠፍቶ… እንዴት ነው “እንኳን አደረሳችሁ” የሚለን? (ያውም ለእኛ አሻፈረኝ በሚለን ኔትዎርክ!) እኔ የምለው ---- እኛና ቴሌ የምንተዋወቀው በስልክ አገልግሎት አይደለም እንዴ? (ከዚያ ውጭ የት ስንተዋወቅ ነው!) ከሁሉም የሚገርመኝ ደሞ ”ከመጪው ዘመን ጋር አገናኛችኋለሁ” የሚለው ፉከራው ነው፡፡ (“ፅድቁ ቀርቶብኝ በቅጡ በኮነነኝ” አሉ!) እንኳንስ ከመጪው ዘመን… ከዛሬ ጋር እንኳን መች ተገናኘን! (ማን ነበር “አቅምን አውቆ ማደር ጥሩ ነው ታላቅ ችሎታ ነው” ያለው?!) አሁንማ ከምንፈልገው ሰው ጋር መገናኘት አይደለም--- ሂሳብ ለመሙላትም ኔትዎርክ ማግኘት መከራ ሆኗል (ቴሌኮም በነፃም እንኳን ገንዘብ አልቀበልም እያለን እኮ ነው!) እስካሁን የውሃና የመብራት መ/ቤቶች ለገና በዓል “እንኳን አደረሳችሁ” ማለት አለማለታቸውን እርግጠኛ አይደለሁም፡፡ ምናልባት ሳልሰማቸው ብለውን ከሆነ ግን የእነሱንም ከ“ሙስና” ለይቼ አላየውም፡፡ ለምን ብትሉ… ገንዘብ የምንከፍልበትን ዋናውን አገልግሎት በቅጡ ሳናገኝ በየበዓሉ “እንኳን አደረሳችሁ” ማለት ለእኔ ተራ መደለያ ነው፡፡
(የመረረው ደንበኛ አታውቁም!?) ለነገሩ እዚህ አገር እኮ ቀድመው የሚናደዱት አገልግሎት ሰጪዎቹ እንጂ ደንበኞች አይደሉም፡፡ እኛ ደህና አገልግሎት የሚሰጠን አጣን ብለን ከመናደዳችን በፊት እነሱ ቀድመውን ይናደዱብናል (“ራሱ በድሎ ራሱ አለቀሰ” አለች አስቱ!) እናላችሁ---የበዓላት ጊዜው ድለላ ቀርቶብን አንዴም ክፍያው ተቋርጦ የማያውቀውን የውሃና የመብራት አገልግሎት ሳይቆራረጥ፤ሳይጠፋ እናገኝ ዘንድ ለብዙ መቶኛ ጊዜ እንማጠናለን፡፡ (“Where is my beef?” አለ ፈረንጅ!) ምን እንደሚገርመኝ ታውቃላችሁ? ሦስቱም የመንግስት ተቋማት ለአገልግሎታቸው መቋረጥ የሚሰጡት ሰበብ ሁሌም ተመሳሳይ ነው - እንደሰነፍ ተማሪ እየተኮራረጁ፡፡ (አዲስ ሰበብ መፍጠር ሮኬት ሳይንስ ሆነ እንዴ?) እናላችሁ ---- ውሃም መብራትም ኔትዎርክም የሚጠፉትና የሚቆራረጡት በ“ልማቱ” የተነሳ ነው፡፡ መብራት ለምን ይቋረጣል? ግድቦች እየተሰሩ ስለሆነ! ኔትዎርክ ለምን ይጠፋል? ኔትዎርክ እየተስፋፋ በመሆኑ! ውሃ ለምን ትጠፋለች? አዲስ የውሃ መስመር እየተዘረጋ ነዋ! ሰላማዊ ሰልፍ ለምን ታገደ? ልማቱን ለማፋጠን! እኔ የምለው ግን ---- ነባሩ አገልግሎት ሳይቋረጥ፣ እኛም ሳንማረር --- ልማቱን ማስፋፋት እንዴት አቀበት ይሆንብናል? ሳስበው ግን አቀበት ሆኖብን አይመስለኝም፡፡ በልማት ሰበብ የስንፍናን ካባ ደርበን ለሽ ስላልን ነው፡፡
(ልማትና እንቅልፍ መቼም ተስማምተው አያውቁም!) አሁን የምፈራው ግን ምን መሰላችሁ? ለምን ሙስና ያለቅጥ ዓይን አወጣ ብለን ስንጠይቅ ---“የፀረ- ሙስና ዘመቻው ስለተጧጧፈ” የሚል ምላሽ እንዳንሰማ ነው፡፡ (ነገሩ ሁሉ እኮ ምፀት ሆኗል!) እኔ የምላችሁ ግን… ለምንድነው ግን ጦቢያን እንዲህ የጠላናት? ብንጠላትማ ነው… በየመንግስት መ/ቤቱ ቱባ ቱባ ሹማምንቶች የአገር ሀብት ዘርፈው የተያዙት! ብንጠላትማ ነው--- ከአገርና ከህዝብ ላይ እየዘረፍን የ15 ሚ.ብር ዶዘሮች ስንገዛ ቅንጣት ታህል የማይቆረቁረን! ብንጠላትማ ነው… ከመንግስትና ከባለሀብት ላይ እየነጠቅን በሚስትና በዘመዶቻችን ስም በየባንኩ ብዙ ሚሊዮን ብሮችና ዶላሮች የምናከማቸው! ብንጠላትማ ነው… በሙስና ገንዘብ መንትፈን በየቦታው ግራውንድ ፕላስ 2 ምናምን የምንገነባው! የጠላነው ግን ጦቢያን ብቻ እንዳይመስላችሁ… ራሳችንንም ነው!! ቤተሰቦቻችንንም ነው!! ልጆቻችንንም ጭምር ነው!! በሙስና ተይዘን የመገናኛ ብዙሃን ዜና መክፈቻ ስንሆን ቀድመው የሚያፍሩብን እኮ ቤተሰቦቻችን ናቸው፡፡ ልጆቻችን ናቸው፡፡ ወዳጆቻችን ናቸው፡፡ የኢትዮጵያ ህዝብ ነው፡፡ የሾመን መንግሥት ነው። የመለመለን ፓርቲ ነው፡፡
የማታ ማታም የጠላናት ጦቢያ---- በተራዋ አንቅራ ትተፋናለች፡፡ “እኒህ ከእኔ ማህፀን አልወጡም!” ብላ ትክደናለች (“ሰው የዘራውን ያጭዳል” አለ ታላቁ መፅሐፍ!) አሁን አሁንማ ወዳጆቼ… በመዲናዋ ዙሪያ እንደ እንጉዳይ የፈሉትን አማላይ ህንፃዎች ስመለከት ልቤ ድንግጥ ማለት ጀምሯል (“ከሙስና ነፃ” የሚል ታፔላ ይለጠፍባቸው!) ምን ህንፃዎቹ ብቻ… በኢቴቪ ብቅ እያሉ ስለ ኪራይ ሰብሰባቢዎች ፀረ - ልማት እንቅስቃሴ የሚደሰኩሩንን የመንግስት ሹማምንቶችም መጠራጠር ከጀመርኩ እኮ ቆየሁ! (ከቫይረሱ ነፃ የሆነውና ያልሆነው አይለይማ!) እንዴ…አንዳንዶቹ እኮ “አገሩን የሚወድ ሰው ሙስና አይፈጽምም” ብለው በነገሩን ማግስት ነው “ቫይረሱ” እንዳለባቸው በኢቴቪ የዜና እወጃ የምንሰማው! (ዕድሜ ለፀረ - ሙስና ኮሚሽን!) እኔ የምለው ግን ---- የፀረ ሙስና ኮሚሽን በአገራችን Grand corruption የለም የሚል ነገር የተናገረው በግምት ነው እንዴ? በጥናት ላይ ተመስርቶ እንዳልሆነማ ራሱ እያሳየን እኮ ነው፡፡ (Grand corruption ቀላል አለ እንዴ!) የገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ቁንጮ ቁንጮ ሃላፊዎች ሲፈጽሙ የከረሙትን ሙስና ምን ልንለው ነው? (መቼም “ግራንድ ኮራፕሽን” ነው ለማለት የገንዘብ ሚኒስቴር ሙሉ በሙሉ መዘረፍ ያለበት አይመስለኝም!) እኔ የምለው ግን----የመንግስት ባለስልጣናት ሃብት ተመዝግቦ አያልቅም እንዴ? ለነገሩ የአንዳንዶቹን የሃብት መጠን ለመመዝገብ እኮ አመትም የሚበቃው አይመስልም፡፡
ቦቴው፣ ዶዘሩ፣ ቪላው፣ በየባንኩ ያለው ገንዘብ፣ የጦር መሳሪያው፣ (የጦር መሳሪያም እንደ ሃብት ይቆጠራል እንዴ?) እኔማ አንዱ ወዳጄ “የባለስልጣናት ሃብት ተመዝግቦ አልቋል” ሲለኝ --- እንግዲያውስ ከስልጣን ሲወርዱ ይሆናል ይፋ የሚደረግልን ብዬ ጠረጠርኩ፡፡ (አንዳንዶቹ እኮ ሃብታቸው ሳይታወቅ እያመለጡን ነው!) በነገራችሁ ላይ የባለስልጣናቱን የሃብት ምዝገባ ጉዳይ ያነሳሁት ክፉ አስቤ አይደለም፡፡ ባለስልጣን ባየሁ ቁጥር “የሙስና ቫይረስ ይኖርበት ይሆን?” እያልኩ በመጠርጠር ሃጢያት እንዳልገባ ሰግቼ ነው፡፡ ከደሙ ንፁህ የሆኑ ባለስልጣናትስ ለምን ያለምግባራቸው ይጠርጠሩ? እናላችሁ ---- የባለሥልጣናቱ የሃብት መጠን ቶሎ ተጠናቆ ይፋ ቢደረግ በጥርጣሬ ዓይን ከመተያየትና መረጃ ላይ ካልተመሰረተ ሃሜትና አሉባልታ እንድናለን፡፡ ሃሜት እኮ ሃጢያት ነው! መረጃ እንደ መንፈግ ግን አይሆንም!! የሃብት ምዝገባው ገና ካልተጠናቀቀ---- ይህችን ማዳበሪያ ሃሳብ ተቀበሉኝ (መዝጋቢውን አካል ማለቴ ነው!) ምን መሰላችሁ… በሃብት ምዝገባው ላይ የትዳር አጋርም መካተት አለበት የሚል ሃሳብ ስላለኝ ነው (መነጣጠቅ ተጀምሯላ!) በመጨረሻ አንድ የቤት ሥራ ጣል አድርጌ ልሰናበት፡፡ ይሄ የሥነ ዜጋ (ሲቪክ ኤጁኬሽን) ትምህርታችን እንደገና ይቀረፅ ይሆን እንዴ? (ሙስናው ቅጥ አጣ ብዬ እኮ ነው!)
ዲታ መንግሰትና ምስኪን ህዝብ
(ግርማ ሠይፉ ማሩ)

የ“አባት ቤት ሲዘረፍ አብረህ ዝረፍ” የሚባል አባባል አለ፡፡ ይህን አባባል ሰረዳው ዘራፊዎችን ማስቆም ካልቻልክ
በዘረፋወ በመሳተፍ የድርሻህን ማንሳት ችግር የለውም የሚል እንደምታ እንዳለው ነው፡፡ ከዚህ በመነሳት
ይመስለኛል በአብዛኛው የመንግሰት በሚባለው ንብረት ላይ በዘረፋ ላይ የተሰማሩ ሰዎች ድርሻቸውን እንደወሰዱ
እየተሰማቻው ይህን በማድረጋቸው አንድም ቅሬታ አይታይባቸውም፡፡ ይልቁንም የጀግንነት ሰሜታቸው ሀይሎ
ይህን ዘረፋ የሚጠየፉትን እንደ ጅል መቁጠር እየተለመደ መጥቶዋል፡፡ በዘረፋው ላይ ያልተሳተፉም ቢሆኑ ይህ
የመንግሰት የሚባለው ንብረት ሲዘረፍ ከመመልከት ዘለው ለምን አይሉም፡፡ አንድ አንዶች ደግሞ በመዝረፍ
ባይሳተፉም በማዘረፍ እየተሳተፉ ይገኛሉ፡፡ የአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን ለመዝረፍም ለማዘረፍም ጥሩ ማሳያ ነው ብዬ ነው
የማምነው፡፡
የአዲሰ አበባ መንገዶች ባለስልጣን አሰርቶት ከአገልግሎት ውጭ ሆኖ የነበረው ከመሰቀል አደባባይ ቃሊት ያለው መስመር አሰፋልቱ
እየፈረሰ ሰፊ ጉድጓድ እየተማሰ አደሲ ቁፋሮ እየተካሄደ ሰመለከት ከባከነው ገንዘብ ይልቅ ያብከነከነኝ ተጠያቂነትን እንዲያረጋግጡ፣
ካልቻሉም እራሳቸው የሚጠየቁት ጠቅላይ ሚኒስትራችን የሰጡት ማብራሪያ ትውስ ብሎኝ ለምን መዋሸት ያስፈልጋል ብዬ ጉዳዩን
ማንሳት ወደድኩ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመዝረፍ ተሳትፈዋል ለማለት መረጃም ማስረጃም የሌለኝ ቢሆንም ሲዘረፍ ዝም ብሎ
በመመልከት እና ሲከፋም ለማዘረፍ ከለላ እየሰጡ መሆናቸው ግን የአደባባይ ሚስጥር ነው፡፡
ከመስቀል አደባባይ ቃሊቲ ድረስ ያለው መንገድ አንድ ዓመት እንኳን ሳያገለግል በመንገዱ አሰፋልት መሆን ምክንያት የተማሪዎችን
ህይወት መቅጠፍ ሳይበቃው ይህን ሊከላከል ይችላል የተባለ የብረት አጥር ግንባትን ጨምሮ ከፍተኛ ገንዘብ ከንቱ ቀርቶዋል፡፡ በዚህ
ጉዳይ ዋነኛ ተጠያቂ መሆን ያለበት የአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን ሲሆን፤ የባለስልጣኑ መስሪያ ቤት ሃላፊ ጉዳዩን፤ የባቡር መስመሩ
ድንገት በመምጣቱ ነው የሚል አስተያየት መስጠት ዕቅድ አልባ መንግስት መሆኑን ማሳያ ነው፡፡ ይህ በሚመለከት ሃሳቡን ያጋራኝ
በመንገድ ዘርፉ ኃላፊ የሆነ ሰው የነገረኝ ደግሞ፤ በባቡር ኮርፖሬሽን ቦርድ ውስጥ የአዲስ አበባ መንገዶች መስሪያ ቤት ኃላፊ ያሉበት
መሆኑን አስተያየታቸውን አሰገራሚ ያደርገዋል ነው ያለኝ፡፡ ይህ ብቻ አይደለም ኃላፊው ባቡር መስመሩ መንገዱን ሊጠቀምበት ይችላል
የሚል ግምት ነበር ብለዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትራችንም የዚህ ሰበብ አውቀው ይሁን ሳያውቁ ሰለባ የሆኑ ይመስለኛል፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ
ማስተባበያ በሰጡበት ወቅት ባለ ሞያ መሐንዲስ መሆናቸውን ጠቅሰው ከላይ ያለው አሰፋልት ብቻ ስለሚነሳ ከሰር ያለው ሙሊት ስራ ላይ
ይውላል በዚህ የተነሳ ብክነቱ ዝቅተኛ ነው ብለው ለኢትዮጵያ ህዝብ ገልፀው ነበር፡፡ የነበራቸው መረጃ ይህ ከሆነ አሁን እያየን ያለው
ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዳሉት ሳይሆን እንደ አዲስ ተቆፍሮ ሌላ እየተሞላ ነው፡፡ አሁንም ጉዳዩ ቀላል ነው ሊሉን አይችልም፡፡ ጠቅላይ
ሚኒስትራችን ዋሽተውናል፤ አልዋሸውም የሚሉ ከሆነ ደግሞ በሹሞቻቸው ተታለዋል፡፡ ሰለዚህ የተሳሳተ መረጃ የሰጧቸውን ይጠይቁልን
ወይም እራሳቸው ኃላፊነቱን ይውሰዱ፡፡ ይህ የጠቅላይ ሚኒሰትሩ አሰተያየት የህዝብ ሀብት ብክነት ሲነገራቸው እርምጃ ከመውሰድ ይልቅ
ከለላ መስጠታቸው ተባባሪነታቸውን ነው የሚያሳየው፡፡ አሁንም አሰቸኳይ እርምጃ እንዲወስዱልን እንጠይቃለን፡፡
በቅርቡ ደግሞ ከፍተኛ ወጪ የተደረገበት ግንባታ ከተከናወነ በኋላ መፍረሱን አስመልክቶ መስሪያ ቤቱ ኃፊዎች የሰጡት አሰተያየት
አሁንም ያስገርማል፡፡ ዲዛይን ለውጥ በመደረጉ የተነሳ ግንባታው መፍረሱን አረጋግጠው፤ እንደዚያም ቢሆን ወጪው የሚመለከተው
ግንባታውን የሚያከናውነው የቻይና ድርጅት ነው፡፡ ለዚህም ምክንያቱ ኮንትራቱ ሰሰጥ ዲዛይንም ግንባታንም የሚጨምር የኮንትራት
ዓይነት ስለሆነ ነው ብለውናል፡፡ እንዲህ ከሆነ ደግሞ ይህ ኮንትራት የተሰጠበት ዋጋ እንደፈለጉ አባክነውም ቢሆን አትራፊ ያደርጋቸዋል
የሚል እንደምታ በጆሮዋችን ያቃጭላል፡፡ ድሮም ቢሆን ገንዘብ ይዞ መጥቶ ዲዛይንም ግንባታም ለመስራት የሚገባበት ውል ሰላማዊ
እንደማይሆን ልባችን ያውቀዋል፡፡ ለማነኛውም ይህ የባቡር ፕሮጀክት ተጠናቆ ሰራ ሲጀምር ወጪውን በግራም በቀኝ አሰበን በወቅቱ
ካለው ዋጋ አንፃር ማየታችን የግድ የሚል ነው፡፡ ከዚህ አንፃር ዋነኛ ዘራፊው የቻይና መንግሰት ሲሆን አዘራፊው ደግሞ የብድር ስምምነት
የገባው የፌዴራል መንግሰትና የባቡር ኮርፖሬሽን ነው፡፡ የእነዚህ አካላት ሀለቃ ደግሞ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ናቸው፡፡
ከመንገድ ጋር በተያያዘ የማንረሳቸው በባቡር ግንባታ ስም የህዝብን ሃብት ያባከኑት ከሾላ ገበያ፣ በለም ሆቴል ወደ ቀለበት መንገድ
ማቋረጫ መንገድ፤ በደሳለኝ ሆቴል ሳርቤት የሚወስዱት መንገዶች አገልግሎት ሳይሰጡ መፍረሳቸው የአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን
ሃላፊዎችን እንቅልፍ ይሰጣቸው እንደሆነ ማወቅ ያስፈልጋል፡፡ ምን ችግር አለው ለዘመናዊ ባቡር ሲባል ነው ብለው በሚዲያ የሚሰጡት
መልስ ውሃ የሚቋጥር አይሆንም፡፡ አሁንም በድፍረት ሚዲያ እየወጡ ይህን መልስ የሚሰጡ ሰዎች ትዝብት ላይ ከመውደቅ ባለፈ ይህ
ሰበብ ግብር ከፋዩን ዜጋ እንደማያሳምነው መረዳት ይኖርባቸዋል፡፡ ይህን የሚዲያ ዘማቻ አሁንም አላቆሙም፤ ልብ ማለት ግን የተሳናቸው
ይመስለኛል፡፡
በከተማችን በከፍተኛ ወጪ እየተገነቡ ያሉት የትራፊክ መብራቶች ለመፍረስ አንድ ወር ሲቀረው የሚሰሩ መሆናቸው የዚህ መብራት
ባለቤት ማን ነው? የሚል ጥያቄ ያስነሳል:: የመንገድ ማካፈያዎች፣ አደባባዮች የሚሰሩት በጥቃቅን በተደራጁ ይሁን በኮንትራክተር
መፍረሳቸው እየታወቀ የሚገነቡበት ምክንያት ግራ የሚያጋባ ነው፡፡ የጥላሁን ገሠሠ አደባባይ የሚባለው የተጠናቀቀው እንደሚፈርስ
ግርማ ሠይፉ ማሩ ታውቆ ሌሎች መንገዶች መፍረስ ከጀመሩ በኋላ ነው፡፡ ይህን ተግባር ለማከናወን ውል ተገብቶ እንኳን ቢሆን ገንብቶ ከማፍረስ ተደራድሮ
ሀብት እንዳይባክን ማድረጊያ “አስገዳጅ ሆኔታዎች” የሚል የውል አንቀፅ እንዳለ ይታወቃል፡፡ ይህ የኮንትራት አስተዳደር ሀሁ ነው፡፡
በግርግር የሚባክነው ግን ከፍተኛ የሆነ የህዝብ ሀብት መሆኑ ተዘንግቷል፡፡ ህዝብና መንግሰት የተለያዩበት ሀገር የመንግሰት ሀብት
የሚባለውን መዝረፍ ለፅድቅ እንደሚደረግ ተግባር ይወሰዳል፡፡
 በነገራችን ላይ በመርዕ ደረጃ የመንግሰት የሚባል ነገር የለም፡፡ መንግሰት ህዝብ በመወከል ለህዝብ የጋራ ጥቅም የሚውል የጋራ የሚባሉ
ንብረቶች ሊኖሩት ይችላሉ፡፡ ከዚህ ጋር ተሰማሚ የሆነው የህገ መንግሰት አንቀፅ 89፡3 “መንግሰት መሬትንና የተፈጥሮ ሀብትን በህዝብ
ስም በይዞታው ስር በማድረግ ለሕዝብ የጋራ ጥቅምና እድገት እንዲውሉ የማድረግ ኃላፊነት አለበት፡፡” ይላል፡፡ በተቃራኒ ደግሞ
የሚቆመው አንቀፅ 40፡3 “የገጠርም ሆነ የከተማ መሬትና የተፈጥሮ ሀብት ባለቤትነት መብት የመንግስትና የህዝብ ብቻ ነው” በማለት
መንግሰት እራሱን ከህዝብ የተለየ ሌላ አካል አድርጎ ያስቀምጣል፡፡ አሁን በተግባር ያለውም የመንግሰት ባለቤትነት እንጂ የህዝብ
ባለቤትነት አይደለም፡፡ ለመንግሰት ንብረት ዜጎች የማይቆረቆሩት የመንግሰት የሆነ የእነርሱ ባለመሆኑ ነው፡፡ የእኛ መንግሰት ከህዝብ
ይበልጣል፤ ለዜጎች የሚያስፈልገውን እየነፈገ ለራሱ ጡንቻ ማደበሪያ የሚሆነውን ሀብት፣ ንብረት ያፈራል፡፡ በዚህም ህዝብን ይጨቁናል፡፡
ይህም ሆኖ የመንግሰት የሆነ የማንም ስለአልሆነ ቀዳዳ ያገኘ ሁሉ ይዘርፋል ያዘርፋል፡፡
አሁን እዚህም እዚያም የሚባክነው ገንዘብ በእኔ እምነት የህዝብ ንብረት ነው፡፡ መንግሰትም በህዝብ ስም የማስተዳደር ስራ እንዲሰራ
የተቀመጠ እንጂ ንብረት እንዲያፈራ የተቀመጠ አካል አይደልም፡፡ የህዝብን ንብረት ሲያስተዳድር የሚያባክን ደግሞ ሃላፊነቱን በአግባቡ
ባለመወጣቱ ምንም ዓይነት ሰብብ ሳያቀርብ ቦታውን መልቀቅ ይኖርበታል፡፡ እንቢ ካለም ባለቤት የሆነው ህዝብ ማስለቀቅ ይኖርበታል፡፡
ምን ያደርጋል ህዝቡ ይህ የሚሰራው ስራ በገንዘቡ ወይም በስሙ ልጆቹና የልጅ ልጆች በሚከፍሉት ዕዳ መሆኑን እንዲዘነጋ እና መንግሰት
በቸርነት የሚሰራው እስኪመስል ድረስ የተሳሳተ ፕሮፓጋንዳ ሰለባ እየሆነ ነው፡፡ የዚህ ፕሮፓጋንዳ ዓላማ አንድና አንድ ነው፡፡ መንግስትን
ከተጠያቂነት ማሽሽ፤ ንብረት ሲያባክንም የራሱን ንብረት እንዳባከነ እንዲቆጠር ማድረግ፡፡ ከተቻለም የመንግሰት ንብረት መዝረፍ ነውር
እንዳልሆነ ማስጨበጥ ናቸው፡፡
ልብ በሉ የባቡር መስመር፣ የመንገድ. የቴሌ፣ የመብራት መሰረተ ልማቶች የሚገነባልን ዲታ መንግሰት ነው ያለን፡፡ መንግሰት ቸርነቱ የበዛ፣
እንዲሁም ደግ ሲሆን መንግሰት ለህዝቦቹ የሚያስብ አንድ አካል ነው፡፡ ህዝብ ደግሞ እነዚህ ሁሉ የመሰረተ ልማቶች የሚያስፈልጉት
ምሰኪን ከመንግሰት እጅ የሚጠብቅ፡፡ የሚገርም ነው!! የገዛ ንዘቡን እና ንብረቱን እንዲያስተዳድር የተቀመጠ አካል አዛዥ ናዛዥ ሲሆን፤
ባለ ገንዘቡ ደግሞ ምስኪን ተመፅዋች የሚኮንበት ጥቂት ሀገሮች ካሉ አንዷ ምስኪኗ ኢትዮጵያና ህዝቦቿ ናቸው፡፡
ቸር ይግጠመን!!!!

 http://www.ethiomedia.com/14store/ditta_mengist.pdf

Sunday, January 12, 2014

የሳዑዲ ጉዳይ፡ የአስከሬኑ ሽኝት – ከነብዩ ሲራክ

እጣ ፈንታ …
(ፎቶ ፋይል)
(ፎቶ ፋይል)
ዘመኑ በፈቀደው የአረብ ሃገር ስደትን በኮንትራት ስራ የሳውዲን ምድረ በዳ የባለ ጸጎች ሃገር የረገጠከው ራስክን ደግፈህ ፣ ወላጅ ቤተሰብ፣ ዘመድ አዝማድ ወገኖችህን ለመደገፍ ነበር ። በሳውዲ ቆይታህ በትዕግስት ስታልፍ ያስብከውን ሁሉ ባይሳካም ጋብቻ መስርተህ ሌላዋን የኮንትራት ሰራተኛ ስደተኛ እህትክን ባንድ አቅፈህ ፣ ራስክን በሙያ አንጸህ የተረጋጋ ኑሮን በመኖርህ ላይ እንዳለህ ሳታስበው በውስጠ ደዌ በሽታ ተወጋህ ! ክፉውን ሁሉ የስደት ህይወት በትዕግስት ገፍተህ ደስተኛ ሆነህ ኑሮን ትገፋ እንደነበር አህትህና ባለቤትህ ቅሪት ገላህን ወደ ሃገር ለመሸኘት ለስንብት ስንጓዝ አጫውተውኛል። ፎቶህን አይቸ በህይወት ዘመንህ በአንድ አጋጣሚ አውቅህ እንደነበር ሳውቅ ደነገጥኩ ፣ ድንጋጤየን ዋጥኩት ! ነፍስህን ይማረው ወንደም አለም
ስንብት …
ወደ አልሰሜ እናትና ዘመድ አዝማድ የሚላከውን በድን አካልክን ለመሰናበት በሔድንበት አጋጣሚ በዚያው የሬሳ ማቆያ ጽህፈት ቤት ሃላፊውን ስንት የኢትዮጵያውያን ሬሳ አለ ብየ ጠየቅኩት ። የደስደስ ያለው አረብ ሲመልስ ” አሁን እንኳን ብዙ አይደሉም ፣ ከዚህ በፊት ብዙ ነበር ። እዚህ ማቆያ ውስጥ ፈላጊ ያልመጣላቸው ከአስር የማያንሱ የኢትዮጵያውያን ሬሳ ይገኛል!” ሲል ዘርዘር አድርጎ መለሰልኝ ። ጠያቂ ስለሌላቸው ፣ ስማቸው ስላማይገኝ ሬሳዎች እጣ ፈንታ ብቻ ሳይሆን የሬሳው ማንነት ታውቆ የሚያስቀብር ጠያቂ ከጠፋ በማዘጋጃ ቤትና በፖሊስ እንደሚቀበሩ ያጫወተኝ … ሊሰሙት የሚከብድ እውነት !
ከሬሳው ማስቀመጫ መስሪያ ቤት ሃላፊ ጋር ላፍታ ባደረግነው ቆይታ የሰማሁት አሳዛኝ ነባራዊ ሁኔታ ውስጤን አደማው ። ሬሳውን ወደ ምንቀበልበት የጓዳ በር ለየራሳችን ቆዛዝመን ደረስን: ( ታሞ ፣ እህት ሚስቱ አስታምመውት ፣ ማንነቱ ታውቆ እና ወደ ሃገር መላኪያ ገንዘብ ተገኝቶ ዛሬ ወደ ሃገር ለመሄድ ተዘጋጅቷል ፣ ከምሽቱ 9:45 … የብርቱ ወዳጀ አብሮ አደግ ከፈን ከተቀመጠበት ማቀዝቀዣ ወጣ … በተዘጋጀው የእንጨት ሳጥን ሆኖ ወደ አንቡላንስ ከመሸኘቱ በፊት በስትሬቸር እየተገፋ መጣና ለስንበት ፊቱ በአንድ የፊሊፒን የሬሳው ክፍል ሰራተኛ ተገለጠ … ያ ዘንካታ አይኑን ጨፍኖ ታጋድሟል …አንጀንታቸው የሚላወሰውን እህት ፣ ሚስት፣ ጓደኞች እና ጎረቤቶች ሃዘናቸውን እንደፈለጉ ጮኸው በማይገልጹበት ግቢ የወንድማቸውን በድን ተሰናበቱት … በሬሳው ክፍል ሃላፊ ባጫወተኝ አሳዛኝ ታሪክ ተጽናንቸ የነበርኩት እኔም እህት የወንድሟን ፣ ሚስት የባሏን ግንባር እየሳሙ በታመቀ የሃዘን ስሜት ድምጻቸውን አርቀው እያነቡ ሲሰናበቱት ሳይ ብርክ ያዘኝ !
ሽኝት …
በእርግጥም እኒህኞቹ ወገኖችም ሆኖ ታሞ አስታመውት የሞተው ወንደም እድለኛ ነው! ነገ የሃገሩን አፈር ፣ ታሞ እያለ እናቱን ናፍቆ ሁለቴ ለመሄድ ተነስቶ በተመለሰበት አውሮፕላን ዛሬ በድኑ በውድ ዋጋ ተጭኖ ይደርሳል ! እናት እና ልጅ ተነፋፍቀው አልተገናኙም: ( እናም አልሰሜ እናት አለም ነገ ሬሳ ለመቀበል በጠዋት መርዶ ይጠብቃታል 
ህይወት እንዲህ ነው የሞተውን ነፍስ ይማር ! እናት እና መላ ቤተሰብ ጽናቱን ይስጣችሁ ሌላ ምን ይባል?  https://www.zehabesha.com/amharic/archives/11844                  

የአሰብ ጉዳይ:- “ጦርነት ፈርተን ግን ሀገራችንን አሳልፈን አንሰጥም” 

ገና በጠዋቱ “ዓሰብን ማስመለስ አለብን የምትለው እንዴት ነው? ወደ አላስፈላጊ ጦርነትና ደም ማፋሰስ ልታስገቡን ፈለጋቹ?” የሚል አስተያየት አዘል ጥያቄ አገኘሁ።
asab port
መጀመርያ ወደ ጭንቅላታችን መምጣት ያለበት ጉዳይ ‘የዓሰብ ወደብ የማነው?’ የሚል ነው። ዓሰብ የኢትዮጵያ ልአላዊ ግዛት (ንብረት) ስለመሆኑ ታሪካዊ፣ ፖለቲካዊና ሕጋዊ (በዓለም አቀፍ ሕግ መሰረት) ማረጋገጫዎች አሉን። ዓሰብ የኛ ስለመሆኑ የሚያጠራጥር ምንም ምክንያት የለም። ማስረጃዎቹ (ማረጋገጫዎቹ) እዚሁ ፌስቡክ ላይ ባልፅፋቸውም በወደቡ ባለቤትነታችን ጥርጣሬ አይግባቹ። ስለዚህ ጥያቂያችን ፍትሐብሄር ነው።
ሁለተኛ ጉዳይ ዓሰብ የኛ ቢሆንም አሁን ያለው ግን በኤርትራ ቁጥጥር ስር ነው። ንብረት ሃብታችን ተነጥቀናል ማለት ነው። ጥያቄው መሆን ያለበት ‘ዓሰብ ወደብ ለኢትዮጵያ ያስፈልጋል?’ የሚል ነው። መልሱ: ‘አዎ! ያስፈልጋታል’ ነው። የባህር በሯን የተነጠቀች ብቸኛዋ ትልቅ ሀገር ኢትዮጵያ ናት። በአሁኑ ግዜ የባህር በር የአንድ ሀገር የህልውና በር ነው። የህልውና በሩ መዘጋት የለበትም። ስለዚህ ኢትዮጵያ ንብረቷ (ወደቧ) የማስመለስ መብትም ታሪካዊ ግዴታም አለባት።

ሦስተኛ ‘እንዴት ነው ወደቡን ማስመለስ የምንችለው?’ የሚል ጥያቄ ማየት ተገቢ ነው። ምክንያቱም ዓሰብ የኢትዮጵያ ቢሆንም በመሪዎቻችን ሐላፊነት የጎደለው ዉሳኔ ምክንያት ለኤርትራ ተሰጥቶ ይገኛል። ‘ወደባችን አለ አግባብ ለኤርትራ በመሰጠቱ ምክንያት ዓሰብን የማስመለስ ጉዳይ ከባድ ሊያደርገው ይችላል’ የሚል ሐሳብ ቢነሳ አግባብነት አለው። ጦርነትም ሊያስከትል ይችላል የሚል ስጋት ሊቀቅ ይችላል።
ግን ማትኮር ያለብን ስለ ጦርነት አይደለም፤ ስለ ዓሰብ ንብረትነት እንጂ። ዓሰብ የኛ መሆኑ ለዓለም አቀፍ ማህበረሰብ ማረጋገጥ (ማሳመን) ይኖርብናል። በዓሰብ ጉዳይ ፅኑ አቋም ይዘን የኢትዮጵያም የኤርትራም ህዝብ እንዲገነዘበው መጣር አለብን። የዓለም ህዝብ ይሁን መንግስትታት ይደግፉናል። ምክንያቱም የባለቤትነት መከራከርያ ነጥባችን ጠንካራ ነው። የዓለም አቀፍ ሕግም ይደግፈናል። ዓሰብ የኢትዮጵያ ስለ መሆኑ የሚመሰክግሩ የተለያዩ ዓለም አቀፋዊ ስምምነቶችም አሉ።
አራተኛ ዓሰብ የኛ መሆኑ ቢናረጋግጥና ለዓለም መንግስታትና ማህበረሰብ ቢናሳውቅ እንኳ እንዴት ዓሰብን መመለስ እንችላለን? የኤርትራ መንግስትኮ ፍቃደኛ አይሆንም፣ ጦርነት ሊነሳ ይችላል … ወዘተ የሚሉ ጉዳዮች መነሳታቸው አይቀርም። ግን ችግር የለውም። ዓሰብ የኛ መሆኑ ካረጋገጥን ‘ንብረታችን መልስልን’ ብለን የመጠየቅ መብት አለን። የኤርትራ መንግስት ፍቃደኛ ላይሆን ይችላል። ጦርነትም ሊከፍት ይችላል።
እኛ ጦርነት አንፈልግም። ሕጋዊ ንብረታችን (ወደባችን) በሰለማዊ መንገድ እንዲሰጠን ነው የምንጠይቀው። አዎ! ጦርነት አንፈልግም። ጦርነት አንፈልግም ማለት ግን ጦርነት ከፍተን በሃይል የሌላ ሀገርና ህዝብ ንብረት አንወርም ማለት እንጂ ጦርነት ፈርተን ልአላዊ ግዛታችን (ሃብታችን) ለሌሎች ሃይሎች አሳልፈን እንሰጣለን ማለት አይደለም። ጦርነት አንፈልግም ማለት ጦርነት እንፈራለን ማለት አይደለም። አዎ! ጦርነት ስለማንፈልግ ሌሎች ህዝቦችን አንወርም። ጦርነት ፈርተን ግን እናት ሀገራችን አናስደፍርም።
ጦርነት ስለማንፈልግ ዓሰብን በሰለማዊ መንገድ የምንረከብበት መንገድ እናመቻቻለን። የኤርትራ መንግስት ጦርነት ሊከፍትብን ይችላል ብለን ግን ሃብት ንብረታችን ከመጠየቅ ወደኋላ አንልም። ጦርነት ተፈርቶኮ የሀገር ግዛት አሳልፎ አይሰጥም። ጦርነት ተፈርቶኮ ልአላዊ ግዛትን ከማስከበር ወደኋላ አይባልም። በባድመ ጉዳይ ጦርነት ዉስጥ የገባነው ጦርነት ስለምንፈልግ ሳይሆን ልአላዊ ግዛታችን የማስከበር፣ ሀገራችን ከወራሪዎች የመከላከል ሀገራዊ ግዴታ ስላለብን ነው። ጦርነት ፈርተን እጃችንና እግራችን አጣጥፈን የባድመን መሬት ለሻዕቢያ ወራሪዎች አሳልፈን አልሰጠንም።
(በኋላ በፖለቲካዊ ዉሳኔ፣ በመሪዎቻችን ግድየለሽነት ምክንያት ባድመን መስዋእት ከፍለን በደም አስመልሰን ሲናበቃ በእስክርቢቶ ለወራሪዎች ተላልፎ ተሰጠ እንጂ። በጦርነት የተመለሰ ንብረት በድርድር ሲከሽፍ በታሪክ ለመጀመርያ ግዜ ነው። የባድመ ጉዳይ …!)
ምንም እንኳ ጦርነት ባንፈልግም ሃብት ንብረታችን ግን አሳልፈን አንሰጥም። ጦርነት መስዋእት ይጠይቃል። ግን ለሀገራችን መስዋእት ብንከፍል ችግሩ ምንድነው? ለሀገራችንኮ መሞት አለብን። በምንክያት መስዋእት መሆን እንቻላለን። ደግሞኮ ኢህአዴጎች የዓሰብን ጉዳይ ስናነሳባቸው ‘ጦርነት ናፋቂዎች’ ይሉናል። እኔ ግን ለሀገር መስዋእት ብንከፍል ጉዳት የለውም ባይ ነኝ። እንኳንም ለሀገራችን ኢትዮጵያ ለሶማሊያም እየሞትን ነው። ይቅርታ ለሶማሊያም እየሞትን አይደለንም። ምክንያቱ ላልታወቀ ጉዳይ ነው በሶማሊያ እየሞትን ያለነው። ወታደሮቻችን በሀገረ ሶማሊያ እየሞቱ ያሉ ለምን ዓላማ ነው? ዜጎቻችን ዓላማው ለማይታወቅ ጉዳይ በሶማሊያ ከሚሞቱ ለሀገራችን ቢሞቱ አይሻልም ነበር? ኢህአዴጎች ‘ጦርነት ጥሩ አይደለም’ ይሉናል። ጦርነት ጥሩ አለመሆኑ ቢያውቁ ኑሮ ለምን በሶማሊያ ያሉ ወገኖቻችን ወደ ሀገራቸው አያስገቡም?
አዎ! ጦርነት ጥሩ አይደለም። በተቻለ መጠን ጦርነትን ማስወገድ አለብን። ጦርነት ፈርተን ግን ሀገራችንን አሳልፈን አንሰጥም።

Thursday, January 9, 2014

ስልጣኑን መከታ እያደረገ ሰራተኞችን የደፈረው ስራ አስኪያጅ ተጋለጠ! ከስራውም ታገደ

አብርሃ ደስታ

በ8 ወር የስልጣን ቆይታው 14 ሴቶችን ስልጣኑን መከታ በማድረግ ፆታዊ ጥቃት ያደረሰው የማይጨው ሆስፒታል ዋና ስራ
አስኪያጅ( CEO) ከአምስት ቀናት በፊት( በባሇፇው እሮብ) በሀኪሞችና ሰራተኞች ከፍተኛ ተቃውሞ ከስራው እንዲታገድ
ተደርጓል፡፡

አቶ ብርሀኑ ይባላል እንደብዙዎቹ የክልለ የሆስፒታልች ስራ-አስኪያጅ በተፋጠነ የኤች .ኦ (Accelerated Health
Officer) በ1 ዓመት ከምናምን ትምህርት ጤና መኮንነት የተሰጠው ነው፡፡ ከዚህ በፉት “ዐዲሹሁ” በተባለ ጤና-ጣብያ ስራ-
አስኪያጅ ሁኖ ሰርቷል፡፡ እዛ በሚሰራበት ጊዜም ብዙ ተመሳሳይ ሀሜቶች ይሰሙ ነበር፡፡ብዙ ሴት ሰራተኞች ላይ ስልጣኑን መከታ በማድረግ ፆታዊ ጥቃት እንዳደረሰ ብዙ ሀሜቶች እንደነበሩ ተሰምቷል፡፡ ሌሊ ቀርቶ ለኢ.ህ.አ.ዲ.ግ ድርጅታዊ ስልጠና ጦላይ በሄደበት ወቅትም አንዶን ሰልጣኝ ሴት ደፍሮ በእርቅ እንደለቀ ተሰምቷል፡

ይህ የአስገድዶ መድፈር ሱሰኛ የማይጨው ሆስፒታል ሐላፊ ሁኖ የተሸመው የዛሬ 8 ወር አካባቢ ነው፡፡

አቶ ብርሀኑ ሆስፒታሉን እግሩ ከረገጠበት ጊዜ አንስቶ የሆስፒታሉ ሰራተኞችን ሲሆንለት እያባበለ፣ አንዳንዴም ስልጣኑን በመመካት እያስፈራራ እስካሁን በውል የታወቁ 14 ሰራተኞችን ፆታዊ ጥቃት አድርጓል ተብሏል፡፡ ከዚሁ ውስጥ አንዷን ነርስ በጉልበት በቢሮው ቆልፎ እንደደፈራት ተሰምቷል፡፡

በፖለቲካዊ ታማኝነት መስፈርት የሚሾሙ ፍፁማዊ የሆነ ስልጣን የተሰጣቸው የሆስፒታል CEOዎች በተለይ በዚህ ክልል የጤና ሴክተሩን ያቀጨጨና ትልልቅ ባለሙያዎችንም ፈፅሞ ከሃላፊነት እንዲርቁና ባለው እንዲህ ዓይነቱ ምግባረ-ብልሹትና የአሰራር ግድፈቶች ሙያቸውን በተገቢ እንዳይተገብሩ ገድቧቸው እንዳለ ከብዙ ከፍተኛ ሐኪሞች በተደጋጋሚ የሚሰማ ነው፡፡ ይህ አሁን የምናወራበት ጉዳይም አንድ ማሳያ ሁኖ ሊጠቀስ የሚችል ነው፡፡

እንደማንኛውም ሆስፒታል በሆስፒታሉ ሜዲካል ዳይሬክተር የሚመራ የስልጠና ኮሚቴ ነበር፡፡ ሰውየው ከመጣበት ጊዜ ጀምሮ ይሀንን ኮሚቴ አፍርሶ ስልጣኑን ለራሱ ይዞታል፡፡ ስልጠና በመጣ ቁጥር ማንንም ሳያማክርና ያለወረፋቸውን የፈለጋትን ሴት ሰራተኛ እየመረጠ ለስልጠናዎች እየላከ ለዋለላቸው ውለታም በገላቸውን እንዲመልሱለት ማስገደድ፣ ማባበል ዋና መለያ ባህርይው ሁኖና ብዙ የውስጥለውስጥ ሹክሹክታዎች እያስተናገደና ሆስፒታሉ እየታመሰ ቆይቷል፡፡

ይህ ስራ-አስኪያጅ የሆስፒታሉን መንፈስ አደፈረሰው፡፡ ከሰራተኛው ሁሉ መናጨት ጀመረ፡፡ የሀኪሞችም ስራ ማስተጓጎል ስራው አደረገው፡፡ የወረዳውና የዞኑ ሐላፊዎች እንዲሁም የሆስፒታሉ አመራር ቦርድ በሆስፒታሉ እየተከሰቱ ያሉ ችግሮችን ቢሰማም እርምጃ ለመውሰድ ግን ዳተኛ ነበር፡፡

ነገሮች በዚሁ እየቀጠሉ ባለበት ሁኔታ አሁንም እንደሁልጊዜው የ1 ወር ሞያዊ ስልጠኛ ዕድል ይመጣና አንድን የሆስፒታሉ ነርስን ማንንም ሳያሳውቅ ይልካታል፡፡ የ1 ወር ስልጠና ጨርሰች፡፡ ስልክ ደውሎም “ግድየለም ስልጠና ላይ ስትደክሚ ስለነበርሽ አንድ ሳምንት አርፈሽ ነይ: በኔ ይሁንብሽ” ይላታል፡፡

ተመልሳ ስራ የጀመረች ቀን እንደለመደው ያንን ውለታውን በገላዋ እነድትመልስ ይጠይቃታል፡፡ ይበልጥ የሚገርመው እቺ ሰራተኛ ባለትዳርና የልጆች እናት ናት፡፡ አልተስማማችም፡፡ “አለዚያ አንድ ሳምንት ያለፍቃድ አሳልፋ መጣች” ብየ እቀጣሻለሁ ብሎ ማስፈራራት፡፡ ወይ ፍንክች፡፡ በዚህ ሁኔታ ነገሩ ይፋ ተሰማ፡፡ አንድ ሁለት እያሉ በፍርሀት ጉዳቸውን አፍነው ዝም ያሉት ሌሎች ጥቃት የደረሰባቸው ሴቶችም እየተግተለተሉ በግልፅ መውጣት ጀመሩ፡፡ 14 ደረሱ፡፡

የሆስፒታሉ 6 ሓኪሞች፣ ጥቃቱ የደረሰባቸው ሴቶች አንድ ላይ ሁነው የሆስፒታሉን የበላይ አመራር ቦርድና የዞኑ አስተዳዳር እንዲያነጋግራቸው ጠሩ ይህ ጉዳይም ይፋ ወጣ፡፡

ታድያ የሚገርመው ቦርዱ፡ “ይህ ሰው ለረዥም ጊዜ ታማኝ የፓርቲው ነባር አባል እንደሆነ ነው መንግስት የሚያውቀው፡፡ እኛ አሁን እርምጃ ለመውሰድ ይከብደናል፡፡ ስለዚህ ነገሩ በደምብ እስቲጣራ በቦታው ይቆይ፡ የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሐይሌ አስፍሀ ለስራ ወደ ውጪ ስለሄዲ ሲመለሱ እርምጃ ይወስዱበታል” ብሎ ምላሹን ሰጠ፡፡

ሓኪሞቹና ተበዳዮቹ ክፉኛ ተቆጡ፡፡ በዚሁ ሁኔታ ወደ ስራ እንደማይመለሱ በየቀኑ የሴት ልጅ በሚደፈርበት ሆስፒታል ሊሰሩ እንደማይችሉና ዛሬውኑ እንደሚለቁ አስረግጠው ተናገሩ፡፡ቦርዱም አማራጭ በማጣት ያለፈው እሮብ ቀን(ከ5 ቀን በፊት) ከስራው ታግዶ እነዲቆይ አድርጓል፡፡

የተበደሉትንም ሴት ሰራተኞችም “መጀመርያ አስተዳደራዊ እርምጃ ይወሰድበትና ወደ ህጉ ደግሞ ቀጥላችሁ ትሄዳላችሁ” ተብለው እየተጠባበቁ ይገኛሉ፡፡

እስካሁን የተመሰረተበት ክስ ግን የለም፡፡

የቀደምቶቹን ወንጀል ለማጋለጥ መቃብር ሲምስ የኖረው ወያኔ በራሱ ጦር ካምፕ ውስጥ የተገኘውን አስከሬን መደበቅ ለምን አሰፈለገው?

አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ፈረንሳይ ለጋሲዮን በሚገኘው የክብርዘበኛ ጦር ካምፕ ውስጥ ማንነታቸው ያልታወቁ የ6 ዜጎች አስከሬን ለመንገድ ሥራ በተሠማሩ ቆፋሪዎች አማካኝነት መገኘቱ የሰሞኑ አሳዛኝ ዜና ነው።
አንድ አይነት ቀለም ባላቸው ብርድ ልብሶች ተጠቅልለው ከተገኙ 6 አስከሬኖች የመጀመሪያዎቹ ሁለት ሰለባዎች ታስረውበት የነበረው የእጅ ሰንሰለታቸው እንኳ እንዳልወለቀና ከተቀሩት የአንዱ እጆች ደግሞ የፍጥኝ ወደ ኋላ እንደታሰሩ መገኘታችው ግድያው በቅርብ እንደተፈፀም አንዱ አስረጂ ነው።
በእንዲህ አይነት ጭካኔ የተገደሉ ዜጎች አስከሬን መገኘት በመንግሥት ተብየው አካል ካለመገለጹም በላይ ግቢውን በማስተዳደር ላይ የሚገኘው 3ኛ ክፈለ ጦርም ሆነ በግብር ከፋይ ገንዘብ የሚተዳደሩ መገናኛ ብዙሃን እስከዛሬ አንድም ቃል መተንፈስ አለመፈለጋቸው ጉዳዩን እጅግ የሚያሳዝን ብቻ ሳይሆን የሚያስገርምም አድርጎታል። ይባስ ተብሎም በመንገድ ሥራ ቁፋሮው የበለጠ አስከሬን ሊወጣ ይችላል በሚል ስጋት አካባቢው በፖሊስ እንዲታጠር ከተደረገ በኋላ ሥራውም እንዲቋረጥ ተደርጓል።
በፓለቲካ መስመር ልዩነት ምክንያት ደርግ ያለ ርህራሄ የጨፈጨፋቸውን ከመቃብር እያወጣ ዘመድ አዝማድ በማላቀስ የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት ሲዳክር የኖረ አገዛዝ በእንዲህ አይነት አሳዛኝ ሁኔታና አጋጣሚ የተገኘውን የጅምላ አስከሬን አይቶ አንዳላየ ለማለፍ መሞከሩ ለምን ይሆን?
አብዛኛው የአዲስ አበባ ነዋሪ እንደሚያስታውሰው የክብር ዘበኛ ጦር ካምፕ በመባል የሚታወቀው የጃን ሜዳ 3ኛ ክፍለ ጦር ግቢ ድህረ ምርጫ 97 ወያኔ ለጅምላ እስር ቤትነት ከተጠቀመባቸው የማጎሪያ ቦታዎች አንዱ ነበር። ከዚያን ጊዜ በፊትና በኋላም ቢሆን ካምፑ በወያኔ ጠላትነት ተፈረጀ በጸጥታ ሠራተኞች ከታገቱ በኋላ አድራሻቸው እስከዛሬ ተሰውሮ ላሉ በርካቶች በምስጢር እስርቤትነት በማገልገል ላይ ከሚገኙ ወታደራዊ ካምፖች አንዱ እንደሆ ይታወቃል።
ዘመድ አዝማዶቻቸው ይመለሳሉ ብለው ሲጠብቋቸው ሳይመለሱ እንደወጡ የሚቀሩ በርካታ ዜጎች አሉ። በእንዲህ ሁኔታ ወጥተው ከቀሩ መካከል ከሰሞኑ የስድስቱ መቃብር በአጋጣሚ ተገኝቷል። የተገነዙበት ብርድ ልብስ ይነትብና ምንም ዓይነት ብልሽት ሳይደርስበት መገኝቱ ግዲያው በህወሃት ዘመነ መንግስት ስለመፈፀሙ ጥሩ ማስረጃ ነው። ለህወሃት ሰው መግደል ሥራ እንጂ ወንጀል አይደለም። በህወሃት ነፍሰ ገዳይ ይሞገሳል ይሾማል እንጂ አይወቀሰም አይጠየቅም። የስድስቱ ስዎች አስከሬን ሲገኝ መንግስትነኝ የሚለው ህወሃት አይቶ እንዳላየ መሆን ብቻ ሳይሆን ሌሎች አካላትም የሥፍራውን ሚስጢር እንዳያዩ ከልክሏል።በቁጥጥሩ ሥር ያሉ መገናኛ ብዙሃንም ዜናውን እንዳይናገሩ ታግደዋል። ህወሃት ከሚሰራቸው አስገራሚ ወንጀሎች መካከል አንዱይሄው ነው። ይሄ ግድያ በሌላ አካል ተፈፅሞ ቢሆን ኑሮ በረከት ስምዖንና እና ሺመልስ ከማል እየተፈራረቁ ያደነቁሩን ነበር።ይሄ የራሳቸው የእጅ ሥራነውና አይነገርም። የሄንንም የሚናገር እንደ ኢሳት ያለ ነፃ ሚዲያ ካለም ይታፈናል። አሸባሪም እየተባለ ይፈረጃል።
ግንቦት ሰባት የፍትህ የነጻነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ እነዚህ ዜጎች በህወሃት ተግድለው እንደተጣሉ ያምናል። ውሎ አድሮ እውነቱ እስከሚወጣ ድረስ ግን ዜጎች በሙሉ ይሄን ግድ በተመለከተ መረጃ የመሰብሰብና የማሰረጫት ሥራችውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ እናሳስባለን። ይሄን ወንጀል የፈፀሙ አካላት መጠየቅ አለባቸው። የዜጎች ደም እንዲሁ በከንቱ ፈሶ መቅረት የለበትም።
ለኢትዮጵያ ህዝብ መብትና ጥቅም እንታገላለን የሚሉ የፖለቲካና የስቪክ ድርጅቶች እንዲሁም ለሰው ልጆች የሰብአዊ መብት የሚሟገቱ ሁሉ የተገኘው አስከሬን በአስቸኳይ ተመርምሮ ማንነታቸው ለቤተሰቦቻቸውና ለወዳጅ ዘመዶቻቸው እንዲገለጽ፤ ተጨማሪ አስከሬን ሊገኝ ይችላል በሚልስጋት የመንገድ ቁፋሮውን ከሰዎች እይታውጪ ለማካሄድ እንዲቋረጥ የተደረገው ሥራ ለህዝብ እይታ ግልጽ በሆነመንገድ በአስቸኳይ እንዲጀመር የመጠየቅ ሃላፊነታቸውን እንዲወጡ ግንቦት 7 ያሳስባል::
በዚህአጋጣሚ ወያኔ ሥልጣን ከተቆጣጠረበት ጊዜጀምሮ በሱማሌ፣ በጋምቤላ፣ በአዋሳ፣ በጎንደር፣ በአዲስ አበባና ሌሎች የአገራችን ክፍሎች በጠራራ ጸሃይ ካስጨፈጨፋቸው በተጨማሪ በፖለቲካ እምነታቸው ምክንያት ታግተው በየእሥርቤቱ የተወረወሩትንና ከታገቱበት ዕለት ጀምሮ እስከ ዛሬ የደረሱበት ያልታወቁ ወገኖቻችንን ዝርዝር በአስቸኳይ ያሳውቅ ብለን አንመክረውም።እኛ ግን ህወሃት የደበቀውን ወንጀል ሁሉ ህዝብ እንዲያውቀው ለማድረግ ያለምንም ማቅማማት ጠንክረን እየሰራን ነው። መንግስት ነኝ ብሎ በሥልጣን ላይ የሚወጣ ማንኛውም አካል የህዝብ አገልጋይ እንጂ ነፍሰገዳይ እንዳይሆን የጀመርነው ትግል ተጠናክሮ ይቀጥላል።
እንግዲህ ህወሃት በህዝባችንና በአገራችን ላይ የሚፈጽመውን ሰቆቃ ለማስቆም ግንቦት 7 የጀመረውን የነጻነት ትግል አጠናክሮ እንደሚቀጥል እያስታወቅን እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ እንዲህ በየቦታው ተገድሎ ከመጣል ራሱን ለመታደግ ሲል የነፃነቱ ትግል አካል እንዲሆን ጥሪያችንን አሁንም ደግመን እናቀርባለን::
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ !!

በጅዳ እና አካባቢው የኢትዮጵያውያን ክራሞት


saudi ethio j


ካሳለፍነው ወር ጀምሮ ወደ ሃገራቸው እንዲገቡ በተደረገው ጥሪ እጃቸውን የሰጡ መኖሪያና የስራ ፈቃድ የነበራቸው ዜጎች ባቀረቡት ቅሬታ “ወደ ሃገር እንዳንገባ ተደርገን እየተጉላላን ነው!” ብለውኛል። በቀን በሚሰጠው ደረቅ ብስኩትና ጥራቱ ባልተጠበቀ ሩዝ መጉዳታቸውን የገለጹልኝ ሲሆን መፍትሔ የሚሰጠን የኢትዮጵያ መንግስትም ሆነ የሳውዲ መንግስት ተወካዮች አጥተው ቀን በጸሃይ ፣ ማታ በብርድና በቁር እንግልት እንደደረሰባቸው ተናግረዋል። ወደ ሃገር እንግባ ብለው በተደረገው ጥሪ እጃቸውን የሰጡት መኖሪያና የስራ ፈቃድ የነበራቸው ዜጎች እዚህ በጅዳ ሽሜሲ ብቻ ሳይሆን በሪያድ እስር ቤቶች እንዳሉ እንግልት እየደረሰብን ያሉ ነዋሪዎች ምሬታቸውን ገልጸውልኛል።
ሁከት በጅዳ የንጉስ አብድልአዚአዚዝ አውሮፕላን ማረፊያ-
ከጅዳ መካው የሽሜሲ መጠለያ ተነስተው ወደ ሃገር ለመሳፈር  በጅዳ የንጉስ አብድልአዚአዚዝ አየር መንገድ ማረፊያ አውሮፕላን ማረፊያ የደረሱ ቁጥራቸው 1500 በላይ የሆኑ ኢትዮጵያውያን “የያዛችሁት እቃ ከሚፈቀደው ኪሎ በላይ ነው!” በሚል የተፈጠረው አለመግባባት  ማክሰኞ ከቀትር በኋላ መጠነኛ ሁከት ተቀስቅሶ እንደነበር እና ከሰአታት በኋላ መረጋጋቱን ተደጋጋሚ መረጃ ደርሶኛል።  የማክሰኞው ሁከት መነሻ የተመላሾችን የተከማቸ እቃ ለማየት ወደ ቦታው የደረሱትን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሃላፊ በቦታው መድረሳቸውን ተከትሎ ሲሆን በእንግልቱ የተበሳጩት ዜጎች ሁከት መቀስቀሳቸው በአይን እማዘኞች ተደጋጋሚ የስልክ ጥሪ  ለመረዳት ችያለሁ። የአይን እማኞች አክለውም ዜጎች ከሃላፊው ጋር ሊጋጩ ሲሉ በጸጥታ አስከባሪዎች ብርታት መትረፋቸውን ከቦታው  በሰአቱ የደረሰኝ መረጃ ያስረዳል። ግርግሩ ለሰአት ያህል የቀጠለ ቢሆንም በሰውና በንብረት ላይ ጉዳት አልደረሰም። ሁኔታውን ለማረጋጋት በቦታው የተገኙ ፈጥኖ ደራሽ ፖሊሶች ማረጋጋት ከፈጠሩ እና ሁኔታው ከተረጋጋ በኋላ የአየር መንገዱን ሃላፊ ለጥያቄ ወስደዋቸው እንደነበርና ሃላፊውን ለማስለቀቅ የጅዳ ቆንስል ሃላፊዎች እና ጅዳ የመጡት የሪያዱ አንባሳደር ወደ ቦታው በመንቀሳቀስ ከሰአታት በኋላ ሃላፊውን ይዘው ምሽት ላይ መመለሳቸውን ተጨባጭ መረጃ ደርሶኛል።saudi ethio j1
የሃላፊውን ለጥያቄ መቅረብ ተከትሎ በጉዳዩ ዙሪያ ያነጋገርኳቸው አንድ ውስጥ አዋቂ ሲናገሩ “  በአውሮፕላን አቅርቦት እጥረት እና እቃችን ሳንይዝ ወይም በአደራ ተቀብሎ ወደ ሃገር የሚያስተላልፍልን እስካላገኘን ወደ ሃገር አንገባም ያሉትን ዜጎች ጉዳይ እንዲመለከቱ በቆንስላው ጥያቄ ወደ አየር ማረፊያው ያቀኑት የአየር መንገዱ ሃላፊ ስለ ዜጎች መጉላላት መረጃ እንዳልነበራቸውና በቦታው ሲደርሱ ከሁከቱ ጋር ተያይዞ ግራ ተጋብተው ታይተዋል።” በማለት ሲያስረዱ በቆንሰሉና በአየር መንገዱ ሃላፊዎች መካከል የመረጃ ክፍተት መኖሩን ገላልጠው አጫውተውኛል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ከዚህ በፊት ከ40 ኪሎ በላይ እቃ መውሰድ አትችሉም የተባሉ ዜጎች እቃ ሃጅ ተርሚናል በሚባለው የአየር መንገዱ ማረፊያ ቦታ በብዛት ተዝረክርኮ እነወደሚገኝና የብዙዎች እቃ አድራሻ እንደሌለው የአይን እማኞች ገልጸውልኛል።  “አድራሻ ያለውን እቃም በሚመለከት የጅዳ ቆንስል ሰብስበን እንልከዋለን የሚል ቃል ከመስጠት ባለፈ ምንም አይነት ተጨባጭ እርምጃ እንዳልወሰዱም” በማለት እማኞች ገልጸውልኛል።
ከአስር ቀናት ያላነሰ እንግልታቸውን  በማስረዳት የተገፊ ድምጻቸውን እንዳሰማላቸው እንባቸውን እያዘሩና በብስጭት ያስረዱኝ ወገኖች በበኩላቸው “የአውሮፕላኑን ወጭ የሳውዲ መንግስት ከቻለ የኢትዮጵያ መንግስት እቃችን ይዘን እንድንገባ ለምን አላመቻቸልንም?  ሌላው ቢቀር መንግስት በሻንጣው መጫንና ለሳምታት ብስኩት እየተሰጠንና በውሃና ምግብ ግዠ የያዝነውን ገንዘብ ስናጠፋና ስንሰቃይ በዚህ ካልረዳን ወገኖቸ ማለቱ አልገባንም! ዜጎች አይደልንም?” ሲሉ በማጠየቅ በተጎዳ ሰሜት ገልጸውልኛል። ከዚህ ጋር በተያያዘ አንድ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ወንድም እንደገለጹልኝ  ዜጎችን ማጓጓዙ እንደ በፊቱ በፍጥነት ባይከወንም አልፎ አልፎ መቶና ከመቶ በላይ ዜጎች በተገኘ የበረራ ክፍት ቦታ እየተላኩ መሆኑን በማስረዳት  ከቀን ወደ ቀን እየተባባሰ የመጣውን ይህንን ችግር የቆንስሉ ሰራተኞች በተደጋጋሚ ለቆንስል ሃላፊዎች ማሰማታቸውን በመግለጽ መፍትሔ ግን እስካሁን አለመሰጠቱን አክለው ገልጸውልኛል።
የካርጎ መዘጋት መዘዝና የነዋሪዎች ሮሮ-saudi ethio j2
የአየር መንገድ የካርጎ አገልግሎት ለወራት መሰናከል ተከትሎ በኢትዮጵያ አየር መንገድና በእቃ አቅራቢ የካርጎ ኤጀንቶች በደል ደረሰብን የሚሉ ዜጎች  ቅሬታ እያሰሙ ነው። ይህ ችግርም በነዋሪዎችና በካርጎ ኤጀንሲ ሰራተኞች መካከል ውዝግብ ማስከተሉ አልቀረም። የአየር መንገድ ወደ ኢትዮጵያ የሚደረገው ጉዞ ከስድስት ወራት በላይ ምክንያቱ ግልጽ ባልሆነ ምክንያት ከተዘጋ በኋላ ሰሞኑን ስራ መጀመሩ እየተሰማ ነው። ያም ሆኖ በጅዳ ዙሪያ ያሉ የካርጎ ኤጀንሲዎች “ወደ ኢትዮጵያ የካርጎ ግልጋሎት በተለያዩ አቅጣጫዎች እንሰጣለን!” በሚል ከፍተኛ ገንዘብ ለእቃው ማስጫኛ እየተቀበሉ እቃውን ቢረከቡም ከስድስት እሰከ አስር ወራት ለሚቆይ ጊዜ እቃውን በመጋዘ ቃላቸውን ጠብቀው እንዳላደረሱላቸው የመጫኛ ማስረጃቸውን እያሳዩ ቅሬታቸውን የገለጹልኝ በርካታ ዎች ናቸው። የሳውዲ ውጡ ህግ ከተነገረ ጀምሮና ከዚያም ወዲህ በተሰጠው የሰባት ወር የምህረት ጊዜ ጠቃሚ የሚሏቸውን ጥሪት እቃቸውን ለካርጎ ቢያስረክቡም አንድም በካርጎው መዘጋት በተጓዳኝ በካርጎ ኤጀንሲዎች ለአንድ ኪሎ እስከ 10 ሪያል በመክፈል እቃቸውን ቢያስገቡም እቃቸውን ደህንነት በማያውቁበት ደረጃ በንብረታቸው ላይ ብክነት እንዳስከተለባቸው እያዘኑ ሮሯቸውን አጫውተውኛል።
በጀዛን የዜጎች እንቢታ እና የህግ ታሳሪዎች ሮሮ -
በጀዛን “ወደ ሃገር እንግባ!” የሚሉ ነዋሪዎችን ጥሪ ተከትሎ የመጓጓዣ ሰነድ ለመስራት የጅዳ ቆንስል መስሪያ ቤት ተወካይ ዲፕሎማት ወደ ቦታው ያቀኑ ቢሆንም “ድረሱልን!” ሲሉ የነበሩ ዜጎች የውሃ ሽታ መሆናቸውን የኮሚቴውን በፊስ ቡክ መኖሩን የሚያሳውቀን የወገን ለወገንsaudi ethio j3የህዝብ ግንኙነት ፊስ ቡክ ጠቁሞናል።  በጀዛን የሚገኙ የህግ እስረኞችም በህግ ተይዘው ፍርድ ከተሰጣቸው በኋላ ለአመታት የሚጉላሉ እና በጥርጣሬ ተይዘው ፍርድ ቤት ያልቀረቡ ዜጎች የድረሱልን ጥሪ ዛሬም አላቆመም። “ትኩረቱ ሁሉ ወደ ሃገር ተመላሾች መሆኑ ብቻ ሳይሆን ድሮም ተረስተናል አሁንም ተረስተናል!” እያሉ ነው!  በጀዛን ዙሪያ ባሳለፍነው ሳምንት መረጃ ያቀበለን የወገን ለወገን ደራሽ የህዝብ ግንኙነቱ ገጽ ባስተላለፈው መረጃ ወደ ሃገር ቤት ለመሄድ ሰላላሳዩት ዜጎች ትኩረት በመስጠት የዜጎችን ወደ ሃላፊዎች ለመቅረብ እና ለመሸኘት ፍላጎት አለማሳየታቸውን ሲገልጽም “እነሆ ግዜው ደረሰና የሁለቱም ሃገር መንግስታት ሁኔታዎችን አስተካክለው በሰማት (አሻራ) የሚሰጡበት ቦታ ተበጅቶላቸው ከቆንስላ ፅ/ቤት ተወካይ በቆንስል አህመድ የሚመራ ቡድን ለዜጎቻችን እዚያው እንዲሰራላቸው በማሰብ ወደ ጂዛን ተጓዙ። አሁንም እዚያው ናቸው። ነገር ግን ነገሮች እንደታሰቡ እየሄዱ አይደለም። ታስቦላቸው የተሄደላቸው ወገኖች እየወጡ አይደለም የሚል አሳሳቢ ዜና ሰማን። አሁን ባለው ሁኔታ ወደ ማቆያ የሚገቡት ሰዎች በቀን መቶም እንደማይደርሱ ተገለፀልን። ከጂዳ ለዚህ ጉዳይ የተንቀሳቀሰው ልኡካን አሁንም ለማገልገል ይጠብቃል፡ ምንም የሚታይ ነገር ግን የለም። በጂዛን አጎራባች ወደ ሆኑ ከተሞችም ከአካባቢው ማህበረሰብ አምስት አምስት ሰዎች ለቅስቀሳ ተልከዋል። ቢሆንም ወገናችን ዜጎቻችን የሚወጡ አይነት አይደለም። በጣም ሚገርም ነው።” ይላል።  የህግ ታሳሪዎች በበኩላቸው የቆንስል ሃላፊዎችን አነጋግረዋቸው “ለእናንተ ጉዳይ አልመጣንም!” እንዳሏቸው ገልጸውልኛል። የህዝብ ግንኙነቱ ዜጎች ወደ ኋላ ስላፈገፈጉበት ጉዳይም ሆነ በደል ደረሰብን ስለሚሉ ህጋዊ ታራሚዎች የሰጠው መረጃ የለም ። በወገን ለወገን ደራሽ ኮሚቴ ለአንድ ወር በስራ አስፈጻሚነት የሰራሁ መሆኑ የሚታወስ ሲሆን ለቆንስል ሃላፊዎች ያቀረብኩት የዜጎች አቤቱታ እንዲታረም በተደጋጋሚ አሳስቤ የነዋሪውን አቤቱታ በጀርመን ራዲዮ በማቅረቤ በተወሰደ የ “በዲሲፕሊን!” እርምጃ ከኮሚቴው አባልነት በተጽዕኖ መነሳቴ ይታወሳል!
የውጭ ጉዳይ ልዑካን በጅዳ:-
በሳውዲ አረቢያ የሪያድ ኢንባሲ አምባሳደርን ጨምሮ ሶስት አባላትን የያዘው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቡድን ከሶስት ቀናት በፊት ጅዳ ገብተዋል። ልዑካኑ በእስካሁኑ ቆይታቸው የኢህአዴግ የድርጅት አባላትንና የጅዳ ቆንስል ሃላፊዎችን በዝግ ያነጋገሩ ሲሆን የውይይታቸው ትኩረት በመጡበት የዜጎችን ወደ ሃገር መግባት ጉዳይ የማፋጠን ስራ ይሁን በሌላ ተዛማጅ ጉዳይ የሚታወቅ ነገር የለም። የልዑካን ቡድኑsaudi ethio j4 አባላት በእስካሁን ቆይታቸው አደጋውን ለመከላከል በጅዳ ቆንስል ሃላፊዎች የተቋቋመውን የወገን ለወገን ደራሽ ጊዜያዊ ኮሚቴ እስካሁን ያላነጋገሩ መሆኑ ታውቋል። የልዑካኑ ቡድንን ኮሚቴውን አለማነጋገሩ ቅያሞት የገባቸው አንዳንድ አባላት በበኩላቸው የዜጎች እንግልት በቅንጅት ጉድለት እየተበራከተ በሄደበት በዚህ አጋጣሚ ኮሚቴው ንቁ ተሳትፎ ማድረግ ላልቻለበት ሁኔታ የቆንስሉ እና የአመራሩ ድክመት እንደሆነ በማስረዳት እያደር ለይስሙላ የተቋቋመ እንጅ ወገንን ለመርዳት ከመካዝን ያለውን ውሃ ለማደል እንኳ አቅም አጥቷል በሚል ከማህበረሰቡ ወቀሳ እየቀረበበት መሆኑን በግልጽ አጫውተውኛል።
በሳውዲ አረቢያ የሪያድ ኢንባሲ አምባሳደርን ጨምሮ ሶስት አባላትን የያዘው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ልዑክ በጅዳ ቆንስል የመንግስታችን ተወካዮች ለተጠቀሱትና በከባቢው ላሉ ችግሮች አፋጣኝ እርምጃ ካልወሰዱ አደጋውን መታደግ ከማንችልበት ደረጃ እንዳይደረስ የብዙ ነዋሪዎች ስጋት ሆኗል። የሳውዲ መንግስትን እና የኢትዮጵያ ኢንባሲና ቆንስል በማስታወቂያ ብቻ የተደገፈ ተደጋጋሚ ማስጠንቀቂያ ተከትሎ “ሰነድ የሌላችሁ ዜጎቸወ ከሳውዲ ውጡ!” በሚል ማስተላለፋቸው አይዘነጋም። ያም ሆኖ ነዋሪው በርካታ ያልተሟሉ ቅድመ ሁኔታዎችን በማቅረብ ለመውጣቱ ጥሪ “አሻፈረኝ!”  ያሉትን በሽዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች ሮሮ እና ጥያቄ ለመስማትና አፋጣኝ የመፍየትሔ እርምጃ ለመውሰድም የመንግስት ሃላፊዎች ህዝባዊ አስቸኳይ ጥሪ በመጥራት መፍትሔ ያመላክቱ ዘንድ ደግሜ ደጋግሜ እመክራለሁ!
ዛሬም የመረጃ ክፍተቱ ይዘጋ፣ የምንናገረው ተጨባጭ መረጃ መሆኑን አጣርታችሁ መፍትሔ አፈላልጉ ስል ደጋግሜ “ጀሮ ያለው ይስማ!” እላለሁ !
ቸር ያሰማን!
ነቢዩ ሲራክ